የጤና መረጃዎች

Result 64 - of

የመጀመሪያ የጡት ካንሰር ሕክምና
የጡት ካንሰር ሴቶችን ከሚያጠቁ በጣም የተለመዱ የካንሰር አይነቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የጡት ካንሰር እንደሌሎች የካንሰር ዓይነቶች በክብደት ደረጃው ሲለካ 4 ደረጃዎች አሉት፡፡ ከደረጃ 1-3 ያለ ካንሰር ማለት በመጀመሪያወች ደረጃ ያለ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ያልተሰራጨና መታከም የሚችል የካንሰር ደረጃ ነው፡፡

የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ጠቃሚ ነውን?
የማህፀን በር ካንሰር በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በጣም የተለመደ የካንሰር ዓይነት ሲሆን ምልክት ሳያሳይ የሴቶችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ነው፡፡ በቀን ውስጥ 14 የሚያህሉ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ይሞታሉ። ስለዚህ የተሻለ መፍትሄ እና ህክምናን ለማግኘት እንዲሁም ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ለማወቅ የማህጸን ካንሰር ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

የልብ ቫልቭ ደም ወደኋላ መመለስ ችግር – መጠገን ከመቀየር ይሻላል
የልብ ቫልቭ ደም ወደኋላ መመለስ (የልብ ቫልቭ በአግባቡ አለመዘጋት) ችግር በተወሰኑ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡ በዚህ ዘመን የልብ ቫልቭ አለመዘጋት ችግር የሚገጥማቸው ህመምተኞች የቫልቭ ማስተካከል ቀዶ ጥገና ማግኘት ይችላሉ። ይህ ቀዶ ጥገና አጥጋቢ ውጤት የሚያስገኝ እና ከልብ ቫልቭ ቅያሬ ቀዶ ጥገና ጋር ሲነፃፀሩ የጎንዮሽ ጉዳቱ አነስተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም

የጉበት በሽታን (ሄፓታይተስ) እንዴት ማስወገድ ይቻላል?
ጉበት በበሽታ ሲጠቃ እና የጉበት ብግነት ሲከሰት የጉበት በሽታ ይባላል ፡፡ አምስት ዓይነት የጉበት በሽታን ዓይነቶች አሉ ፣ በብዛት የተለመዱት ግን ሄፓታይተስ ኤ ፣ ቢ እና ሲ ናቸው ፡፡ ሁሉም አይነት በሽታዎች ጉበት ላይ በተለያየ ደረጃ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። በጣም የከፋ ጉዳት የሚያመጡት ግን ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ናቸው ፡፡

ኢንዶስኮፒን ( Esophagogastroduodenoscopy ) ለምርመራ እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል?
በዚህ ዘመን ያሉ የኢንዶስኮፒ( Esophagogastroduodenoscopy ) መሳሪያወች ድሮ ከነበሩት ግዙፍ ለአያያዝ አስቸጋሪ ከነበሩት ኢንዶስኮፒዎች የተለዩ ናቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ በሰፊው ጥቅም ላይ የዋሉት ኢንዶስኮፒዎች የፋይበር ኦፕቲክስ (fiber-optics) ቴክኖሎጅን በመጠቀም ብርሃን ለመስጠት እና ሰውነት ውስጥ ያለውን ምስል ሃኪሙ ወደሚመለከትበት ሌንስ በመላክ የበሽተኛው ችግር ምን እንደሆነ ለመመርመር ይጠቀማሉ ፡፡

የልብ ቫልቭ በሽታ እድሜያቸው 40 አመት እና በላይ የሆኑ ሰወች ሊጠነቀቁት የሚገባ በሽታ ነው::
የልብ ቫልቭ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ በሆኑ ሰወች ላይ ነው ለዚህም ምክንያቱ የህብረ ህዋሳት (tissue) እንደፈለጉ አለመተጣጠፍ ችግር ሲሆን በጊዜ ሂደትም የልባችን ቫልቭ ትክክለኛ ቅርፁን በማሳጣትና የልብ በር በትክክል አልዘጋ እንዲል በማድረግ ደም ወደኋላ ተመልሶ እንዲፈስ ያደርጋል::

ስር የሰደደ የሆድ ህመም፣ ችላ ልንለው የማይገባ በሽታ ነው
ኢንዶስኮፕ ማለት ትንሽ ፣ ተጣጣፊ ፣ የብርሃን ጨረር የሚያስተላልፍ ትቦ ሲሆን በላይኛው የስርአተ ልመት ክፍል ውስጥ በማስገባት ጨጓራን፣ ጉሮሮን እና የላይኛው የቀጭን አንጀት ክፍል ላይ ያለ በሽታን ለመመርመር የሚያገለግል መሳሪያ ነው፡፡ ለምሳሌ፦

የኪንታሮት /ሄሞሮይድ/ ሌዘር ህክምና
የኪንታሮት /ሄሞሮይድ/ ሌዘር ህክምና ዘዴ በአሁኑ ጊዜ 2ኛ እና 3 ኛ ደረጃ ላይ ለደረሰ እና ምልክቶች ለሚያሳይ የኪንታሮት በሽታ የሚመከር ውጤታማ የህክምና ዘዴ ነው:: ለ1ኛ ደረጃ ለሚገኝና ምልክቶችን ለሚያሳይ የኪንታሮት በሽታ የህመም ምልክቶቹ በጣም ከባድ ስላልሆኑ እና በቀዶ ጥገና ቢወገድም ተመልሶ ስለሚተካ ቀዶ ጥገና ማድረግ አይመከርም፡፡ ሐኪም በሚያዩበት ወቅትም በፊንጢጣ የሚገቡ የሰገራ ማለስለሻ መድኀኒቶችን (laxative)

የዲስክ መንሸራተት ፣ የተለመደ የጀርባ ህመም መንስኤ ነው
ከ 2 ሰዓታት በላይ ኮምፒዩተር እየተጠቀሙ መቀመጥ የጀርባ ህመም እና እግሮቻችን ላይ የመደንዘዝ ስሜትን ያስከትላል ፡፡ ብዙ ሰዎች ህመሙ ከፍቶ ወደ ዲስክ መንሸራተት እስከሚቀየርበት ጊዜ ድረስ ህመሙን ተቋቁመው ይቆያሉ። የዲስክ መንሸራተት
7297