የጉበት ፣ ጣፊያ እና ሀሞት ህክምና ክሊኒክ (ኤች.ፒ.ቢ ክሊኒክ)

በአሁኑ ጊዜ የታይላንድ ዋና ዋና የጤና ችግሮች የጉበት፣ የጣፊያ እና ሀሞት በሽታዎች ናቸው። አገሪቷ በእስያ ውስጥ በሄፐታይተስ ቢ እና ሲ በስፋት የተስፋፋ ሲሆን ይህም የጉበት ካንሰር ዋነኛ መንስኤ ነው። የሀሞት ቱቦ ካንሰር መጠን በዓለም ላይ ካሉ ሌሎች የካንሰር ዓይነቶች ከፍተኛው ነው። እንደ አለመታደል ሆኖ ብዙ ሕመምተኞች ምልክቶቹ ሊታከሙ በማይችሉበት ጊዜ ከዶክተር ጋር ለመመካከር ይመጣሉ፤ ይህም የህክምናውን ውጤታማነት ያነሰ ያደርገዋል። ከእነዚህ በሽታዎች ውስጥ የታካሚውን ሕይወት የተሻለ ለማድረግ የቬጅታኒ ሆስፒታል የጉበት ፣ ጣፊያ እና ሀሞት ሐኪሞችን ፣ በጣፊያ እና ሀሞት ቱቦ ላይ የተካኑ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ፣ ራዲዮሎጂስቶች ፣ ማደንዘዣ ሐኪሞች እና ነርሲንግ ስፔሻሊስቶችን ጨምሮ የጉበት ፣ ጣፊያ እና ሀሞት ቱቦ ልዩ ባለሙያዎችን አቋቋመ። ይህ ቡድን የተገነባው የዚህ አይነት በሽታን ገና በመጀመርያ ደረጃ ለመመርመር እና ለማከም ነው።

የአገልግሎት ሰዓታት

ሰኞ ፣ ረቡዕ ፣ ሐሙስ ፣ ቅዳሜ እና እሑድ: 08.00am - 08.00pm
ማክሰኞ ፣ አርብ: 08.00 am - 7.00pm

ቦታ

የጉበት ፣ ጣፊያ እና ሀሞት ህክምና ክሊኒክ (ኤች.ፒ.ቢ ክሊኒክ)፣ የጨጓራ ህክምና እና የጉበት ህክምና (ሄፓቶሎጂ) ማዕከል ፣ 2ኛ ፎቅ ፣ ቬጅታኒ ሆስፒታል

ቀጠሮዎች እና ጥያቄዎች

ይደውሉ: (+66)2-734-0000 Ext. 2960,2961,2866
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66)90-907-2560

አገልግሎቶች

የጨጓራ ፣የጉበት ፣የጣፊያ እና የሀሞት ቱቦ ችግሮች ላይ ምክክር፡

የእኛ የጋስትሮኢንተሮሎጂ እና ሄፓቶሎጂ ስፔሻሊስት ሀኪሞች እና የቀዶ ጥገና ሀኪሞች የጉበት፣ የጣፊያ እና የሀሞት ቱቦ በሽታዎችን በከፍተኛ የጥራት ደረጃዎች ለማከም ቁርጠኛ ናቸው።

የጨጓራ ፣የጉበት ፣የጣፊያ እና የሀሞት ቱቦ ምርመራ እና ሕክምና። ቀዶ ጥገና በሚያስፈልግበት ጊዜ እንደ ኤንዶስኮፒክ ቀዶ ጥገና (ላፓሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና) ያሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ከቀዶ ጥገና በኋላ በተደረጉ ማገገሚያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ።

የምግብ መፍጫ ሥርዓት በሽታዎች፣ ጉበት፣ የጣፊያ እና የሀሞት ቱቦ በሽታዎች:-

  • ሄፓቶማ
  • ኮላንጂዮካርሲኖማ (Cholangiocarcinoma)
  • የጣፊያ ካንሰር
  • ሄፓታይተስ
  • የአልኮል ጉበት በሽታ
  • የጉበት ኮምትሬ (ሲሮሲስ)
  • የጣፊያ በሽታ
  • የሐሞት ጠጠር፣ ኮላንጃይተስ

Our Doctors

ASST. PROF. DR. PIPIT BURASAKARN

Hepatobiliary Surgery

Surgery
DR. JADE SUPHAPOL

Hepatobiliary Surgery

Surgery

ሌላ መረጃ

ጥቅሎች እና ቅናሾች

ተጨማሪ አሳይ

የታካሚ ታሪኮች

ተጨማሪ አሳይ

የጤና ጽሑፎች

ተጨማሪ አሳይ

የጤና ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ቪዲዮዎች)

ተጨማሪ አሳይ