Orthopedics Center

Orthopedics Center, Vejthani Hospital, 3rd Floor

የቬጂታኒ ሆስፒታል አጠቃላይ የአጥንት ህክምና ማዕከል


የህክምና ማዕከሉ በአከርካሪ አጥንት እንዲሁም ሌሎች የአጥንት ህመሞች የተጎዱ ታካሚዎችን ፍላጎት ለማርካት ዘመናዊ እና ውጤታማ የሆኑ መሳሪያዎችን ይጠቀማል፡፡በክፍሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች፡- በአደጋ ምክኒያት የአጥንት ስብራት ወይም የመገጣጠሚያ ውልቃት ያጋጠማቸው ፤  የመገጣጠሚያ መቆጣት እንዲሁም የሪውማቶይድ አርትራይትስ፤የዲስክ መንሸራተት በዚህም ምክኒያት የነርቭ ጉዳት ያለባቸው ታካሚዎች፤የእግር አረጋገጥ ችግር ያለባቸው ህጻናት፤በተፈጥሮ ወደ ውስጥ የታጠፉ ቸወይም ጠፍጣፋ የሆኑ እግሮች ያሏቸው ህጻናት፤ለጉልበት እና ለትከሻ አካባቢ ጉዳት መጠነኛ ቀዶ ጥገና ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች፤ የዳሌ እና የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች፤የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ችግር ላለባቸው ህጻናት ህክምና፤በእድሜ መግፋት ምክኒያት በሚመጣ የአጥንት መሳሳት የአጥንት ስብራት ላጋጠማቸው ታካሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው አገልግሎት እንደምንሰጥዎ አይጠራጠሩ፡፡

 

የቀዶ ጥገና እና የአጥንት ስፔሻሊስት ቡድን


ቀዶ ጠጋኝ ሀኪሞቹን ጨምሮ በክፍሉ ውስጥ የሚሰሩ መላ ባለሙያዎች የረጅም ጊዜ ልምድ ያካበቱና አለም አቀፋዊ እውቅና ያላቸው ሲሆኑ ለደምበኞች ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጡ ሀብቶቻችን ናቸው፡፡
የቬጂታኒ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ክፍል አጠቃላይ የምርመራ፤የህክምና እና የአጥንት ቀዶ ጥገናን ያሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ነው፡፡አገልግሎቶቻችን በአደጋም ሆነ በተፈጥሮ ምክኒያት የሚመጡ ስብራት እና የውልቃት ችግሮችን ማስተካከል፤የስፖርት ህክምና ማማከር አገልግሎት፤የመገጣጠሚያ መቆጣት ህክምና፤ያልተመጣጠኑ እግሮችን ማስተካከል፤እጅ ላይ የሚፈጠሩ ግድፈቶችን ማስተካከል፤የጀርባ ህመም ህክምና፤የዲስክ መንሸራተት እና ሌሎች ከአጥንት እና ጡንቻ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች ያጠቃልላል፡፡የታካሚዎችንም ችግር ለማወቅ ወይም ለመመርመር እና ለማከም የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን ያሟላ ነው፡፡ሀኪሞቻችንን እንዲሁም አብረዋቸው የሚሰሩት ነርሶች የላቀ እውቀት ያላቸው እና የሀገሩንም ሰው ሆነ ከመላው አለም የሚመጡ አለም አቀፍ ታካሚዎችን በማገልገል ልምድ ያላቸው እንዲሁም  ተወዳዳሪ የሆኑ ናቸው፡፡ ቬጂታኒ ሆስፒታል ከአለም አቀፍ ጥምር ኮሚሽን(JCI) እውቅናን ያገኘ ሲሆን ይህም ማለት በሆስፒታሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
አገልግሎቶቻችን
  • አጠቃላይ የአጥንት ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት
  • በአደጋም ሆነ በስፖርት ምክኒያት የሚመጣ ስብራት እና ውልቃት ህክምና
  • በስፖርት ማማከር
  • በስፖርት ምክኒያት የሚመጣ ጉዳት እና ህመም ህክምና
  • ሪውማቶይድ አርትራይትስ ህክምና
  • የእግር እና ቁርጭምጭሚት ህክምና
  • መጠነኛ የእጅ ቀዶ ህክምና
  • የእጅ ወይም የእግር አለመመጣጠን ችግር ህክምና
  • ስብራት እና ጉዳት ህክምና
  • የትከሻ ቀዶ ህክምና
  • አርትሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና
  • የህጻናት የአጥንት ህክምና ማዕከል
  • በቢሮ አቀማመጥ ችግር የሚመጡ ህመሞች
  • በአደጋ ምክኒያት የሚመጣ የአጥንት ጉዳት ህክምና
የአገልግሎት ሰዓታት፡-
ሰኞ-እሁድ፡-ከጠዋቱ 2፡00-ምሽቱ 2፡00
ቦታ:-
የአጥንት ህክምና ማዕከል ፤ ቬጂታኒ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ
ቀጠሮ ለማስያዝ እና ጥያቄ ለመጠየቅ:-
ስልክ፡-+66(0)2734-0000
ፋክስ፡- +66(0)2734-0044

Promotion & Package

Our Doctors

Patient Stories

Videos

ይደውሉልን
(+66)8-522 38888
እባክዎ ቋንቋ ይምረጡ