ዓለም አቀፍ ሪፈራል ማዕከል (-አርኤኤ)

ወደ ቬጂታኒ ሆስፒታል ሪፈራል እና አቬሽን ክፍል እንኳን በደህና መጡ

የሪፈራል እና አቬሽን ክፍል የታካሚዎች  እና የአስታማሚያቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ የሆኑ አገልሎቶች  የሚሰጥ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ፡- የመጓጓዣ ቲኬት ማስተካከል ቪዛ የማስረዘም የመሳሰሉት ይገኙበታል

አገልግሎቶቻችን

  • ቪዛ ማራዘም
  • ቲኬት ማስተካከል
  • ሆቴል መያዝ
  • የበረራ ላይ የህክምና አገልግሎት

ቪዛ ማራዘም

  • ይህ ክፍል ከታይላንድ የኢሚግሬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ለታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው ታይላንድ ለመቆየት የሚያስችል ህጋዊ ፍቃድ እንዲያገኙ ይረዳል (ታካሚዎች እና አስታማሚው ቪዛቸው ከሚያበቃበት ቀን ቢያንስ አስር ቀን በፊት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል)
  • የ 90 ቀን አድራሻን የማሳወቅ አገልግሎት  ማንኛውም በታይላንድ የሚኖር የውጪ ሀገር ዜጋ በየ 90 ቀኑ የሚገኝበትን አድራሻ ለኢሚግሬሽን ቢሮ ሪፓርት ማድረግ ይጠበቅበታል ይህን ሪፖርት ከትክክለኛው ቀን 15 ቀናት አስቀድሞ ወይም ከትክክለኛው ቀን 7 ቀናት ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይቻላል

ጉዞን ማመቻቸት

የሪፈራል እና አቬሽን ክፍል የሆስፒታሉን ደህንነት እና የአገልግሎት ጥራት ደረጃ ባማከለ መልኩ ጉዞዎትን ማመቻቸት ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ማስተካከል  እና የጉብኝት ቦታ በቅድሚያ ማስያዝ አገልግሎት ይሠጣል

  • የአየር ቲኬት ማመቻቸት አገልግሎት(የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ)
  • ወደ ኤርፖርትም ሆነ ወደ ሌሎች ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት
  • የጉብኝት አገልግሎት (ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/የእራት እና መዝናኛ )

የሆቴል አገልግሎት

111 Residence, the corporate hotels granted corporate rate for customers of Vejthani Hospital. Please click here to see our service and rates

የ V-Flight አገልግሎት

በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መጓጓዝ ያለባቸውን እንዲሁም እነደአስፈላጊነቱ በህክምና ቡድን መሸኘት ያለባቸውን ታካሚዎች በበረራ ላይ ህክምና ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የህክምና ቡድን አባሎቻችን በቀን ለ 24 ሰዓታት እንዲሁም በሳምንት ለ 7 ቀናት ታካሚዎችን ወደ ተለያዩ ሀገራት የማጓጓዝ አገልግሎት ይሠጣል

አገልግሎቶቻችን

ሀኪሞቻችን በማንኛውም ሰዓት ዝግጁ ሆነው የሚጠብቁ ሲሆን የታካሚውን የህክምና ማስረጃዎች ካጤኑ በኋላ እንደ ጉዳቱ ወይም እንደ ህመሙ አይነት አመቺ የሆነውን መጓጓዣ ይመርጣሉ

  • በአየር ላይ የድንገተኛ የህክምና እርዳታ ለመስጠት የሚያስችሉ እንደ ስትሬቸር ኦክስጂን የህይወት አድን ድጋፍ መስጫ  የመሳሰሉት መሳሪያዎች የተገጠሙለት ነው
  • መሬት ላይ የማጓጓዣ አምቡላንስ አገልግሎት

ለየት ያለ ህከምና

  • ጽኑ ህሙማን ማከሚያ (ICU/CCU)
  • በጨቅላ እንዲሁም ከፍ ባሉ ህጻናት ህክምና ላይ ስፔሻላይዝ ያደረጉ ሀኪሞች
  • የልብ ስፔሻሊስቶች
  • በበረራ ላይ ህክምና የምስክር ወረቀት ያላቸው የ FAA ማረጋገጫ ያለው
  • ደረጃውን የጠበቀ የህክምና ማስረጃ ማዘጋጀት

ጥያቄ ካለዎት

የስራ ሰዓታችን ዘወትር ከሠኞ እስከ እሁድ ከ ጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት

በኢሜይል አድራሻችን ……    v_ [email protected]

የማይቋረጥ የስልክ መስመራችን…+6627340354

እንዲሁም በቬጂታኒ ሆሰፒታል 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮዋችን በአካል በመቅረብ ሊያገኙን ይችላሉ