ቬጅታኒ ሆስፒታልን ምን ተመራጭ ያደርገዋል?

ለእርስዎ ፍላጎቶች ቅድሚያ በመስጠት አስፈላጊውን እንክብካቤ እና አገልግሎቶችን እናቀርባለን።

ቬጅታኒ የህክምና ጉዳዮችዎን በትኩረት የሚያዳምጡ፣ የህክምና አላማዎችዎን የሚገነዘቡ እና የጤና ሁኔታዎን በትክክል ለመመርመር እና እርስዎን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከም በአንድ ቡድን በመቀናጀት የሚተባበሩ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የህክምና ባለሙያዎች እና ስፔሻሊስቶችን ያጠቃልላል። አላማችን በፍጥነት የሚያገግሙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሲሆን ይህም የዕለት ተዕለት ኑሮዎን ቀልጣፋ በሆነ መልኩ እንዲቀጥሉ ያስችልዎታል።

የሕክምና ዕቅድዎን ለመገንባት በእያንዳንዱ የሕክምና ዘርፍ ውስጥ ያለ የባለሙያተኞች ቡድን ሃላፊነት አለበት።

ቬጅታኒ ለተወሳሰቡ የጤና ጉዳዮች ዘመናዊ የሕክምና አማራጮችን መስጠቱን ያረጋግጣል። ከመሰረቱ ትክክለኛ ምርመራዎችን ማድረግ ገና ከጅምሩ የህክምና ስኬታማነት እድልን ይጨምራል። በእያንዳንዱ የጤና እንክብካቤ ጉዞዎ ላይ ተስፋ እና አነቃቂ ተሞክሮዎችን በማቅረብ እጅግ በጣም የላቁ የሕክምና አቀራረቦችን ቀጣይነት ባለው መልኩ እናካትታለን።

ርኅራኄ በተሞላው እና ግላዊ በሆነ እንክብካቤ እናስተናግዳለን

ለደህንነትዎ ተስማሚ የሆነ አቀራረብ ለማዘጋጀት ቁርጠኛ ነን፣ የእኛ የህክምና ስፔሻሊስቶች የእርስዎን ልዩ ፍላጎት የሚያሟላ እቅድ ለማውጣት ትልቅ አትኩሮት ይሰጣሉ። የእርስዎን ሁኔታ በሰፊው ለመገምገም እና ተሞክሮዎን ለማቃለል ከህክምና ዓላማዎ ጋር የተጣጣመ ግላዊ እቅድ ለመንደፍ ይተባበራሉ፣ ይህም እርስዎ በማገገም ጉዞዎ ላይ እንዲያተኩሩ ያስችልዎታል።

ዓለምአቀፋዊ ደረጃዉን የጠበቀ የታካሚ እንክብካቤ እንሰጣለን። አስጨናቂ የሆኑ የጤና እንክብካቤ ጉዞዎችን ከምንጊዜውም በላይ ቀላል እናደርጋለን።

ወደ ባህር ማዶ ህክምና ለማድረግ ከሀገር ውጭ መጓዝ ውጥረት እንደሚፈጥር እንረዳለን። የእኛ ዓለምአቀፍ ታካሚ ድጋፍ ሰጪዎች ግላዊ የሆነ እና ርህራሄ የተሞላበት እንክብካቤን ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው። እኛን ካገኙን ከመጀመሪያው ቅጽበት ጀምሮ እስከ መድረሻዎ ድረስ፣ በህክምናዎ፣ በመነሻዎ እና ወደ ቤትዎ ከተመለሱ በኋላም ቢሆን በእያንዳንዱ የጉዞ እና የጤና እንክብካቤ ሂደትዎ ውስጥ እርስዎን በማገዝ ዋና ረዳትዎ ይሆናሉ።

ዓለም አቀፍ የታካሚ እንክብካቤ አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-

  • ጥያቄዎችዎን መመለስ
  • የዶክተር ቀጠሮዎችን ማስያዝ
  • በትውልደ ኢትዮጵያዊ የጤና አጠባበቅ ድጋፍ ሰጪዎች የቋንቋ እርዳታ መስጠት
  • የሆስፒታል ትራንስፖርት ማመቻቸት
  • የማረፊያ ቦታ ማስያዝ
  • የዓለም አቀፍ ኢንሹራንስ ማስተባበር
  • ቪዛ ማራዘም
  • የቪ-በረራ የአየር አምቡላንስ አገልግሎት