በጊዜ ከታወቀ መታከም የሚችለው ሊምፎማ
እንደሚታወቀው የካንሰር በሽታ በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ሰዎች በመግደል ቀዳሚ መሆኑ ይታወቃል፡፡ሊምፎማ በታይላንድ ሀገር ከሚታዩት የካንሰር ህመሞች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ ህመሙም በማንኛውም እድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል፡፡ይህ የካንሰር አይነት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ የበሽታ መከላከያ ህዋሶቻችንን የሚያጠቃ ሲሆን አንዳንዴም ከሊምፍ ኖዶች ውጪ ወደ ሌላ የሰውነታችን ክፍል ሊሰራጭ ይችላል፡፡ነገር ግን ይህ የካንሰር አይነት በጊዜው ከታከመ የበሽታው ደረጃ ከፍተኛ ቢሆንም እንኩዋን የመዳን እድል ይኖረዋል፡፡