የጤና መረጃዎች

በቬጂታኒ ሆስፒታል የሚሰጡ የካንሰር ህክምና አይነቶች

Share:

አንድ ታካሚ ህመሙ ካንሰር መሆኑ ሲታወቅ የሚያስተናግደው የሞራል ጉዳት እንዲሁም የስነልቦና ጫና ይህ ነው የሚባል አይደለም የህክምናው ጠበብቶችም በየእለቱ ለህሙማኑ የተሻለ ህክምናን ለማቅረብ ደፋ ቀና ከማለታቸውም በላይ በዘርፉ አዳዲስ የህክምና ግኝቶች እየታዩ ሲሆን ዋናው ቁም ነገር የሚታከሙበትን የህክምና ማዕከል መምረጡ ላይ ነው

በቬጂታኒ ሆስፒታል ያለውን የካንሰር ህክምና አገልግሎት ስናይ አንድ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የማስተማሪያ ሆስፒታል ሊያሟላ የሚገባውን ቅድመ ሁኔታዎች ያሟላ ከመሆኑም በላይ በዘርፉ ልምድ ባላቸው ስፔሻሊስት ሀኪሞች የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ነው

እንደሚታወቀው ለካንሰር ህመም የሚሰጠው ህክምና እንደ በሽታው ደረጃ የሚለያይ ሲሆን በቬጂታኒ ሆስፒታል የሚሰጡ የካንሰር ህክምናዎችን ስንመለከት

የቀዶ ህክምና፡–  ይህ ህክምና ካንሰሩ ሳይባባስ ባለበት ቦታ እያለ ለማከም የሚያስችል ሲሆን ይህም ካንሰሩ ያለበትን የሰውነት ክፍል ቆርጦ በማውጣት የሚከናወን ነው በተለይም ደግሞ ካንሰሩ ሳይባባስ አንድ ቦታ ላይ እንዳለ በማውጣት ታካሚውን ከካንሰር ነጻ የማድረግ ህክምና ነው

የጨረር ህክምና   ይህ ህክምና የካንሰር ህዋሱን ለማጥፋት እና ለመግደል ጨረርን የመጠቀም ዘዴ ነው የጨረር ህክምና ብዙ አይነት ካንሰር ህመሞችን በተለይም ደግሞ ያልተሰራጨ ከሆነ ለማጥፋት ወሳኝ ሲሆን አሁን የሳይንሱ ዘርፍ የደረሰበት IMRT(Intensity-Modulated Radiation Therapy) የሚባል ሲሆን ይህም ህክምና ከሌሎቹ ከተለመደው ህክምና የሚለየው ጨረሩ የሚያርፈው ቦታ ለይቶ ሲሆን ህዋሶቹን ብቻ መርጦ የሚያጠቃ መሆኑ ነው ይህም በጨረር ህክምና ምክኒያት የሚከተለው ጉዳት የቀነሰ እንዲሆን በማድረግ ታካሚው የቀነሰ ጉዳት እንዲያስተናግድ እንደሚያደርገው ይታወቃል

ኬሞቴራፒ

ከዚህ በፊት በስፋት እንዳስነበብናችሁ ኬሞቴራፒ ማለት አንድን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ መድሃኒቶችን በመጠቀም የካንሰር ህመምን የማከም መንገድ ነው ኬሞቴራፒም በመላ ሰውነት ውስጥ የመሰራጨት እና ለውጥ የማምጣት እድሉ ከፍተኛ ነው ኬሞቴራፒ ከቀዶ ጥገና በፊትም በሽታውን ለመቆጣጠር በሚል በ’’Neoadjuvant chemotherapy’’ የካንሰር ህዋሱ በቀዶ ጥገና መውጣት እስኪችል ድረስ በቅድሚያ እንዲሟሽሽ በማድረግ ይሰጣል

የሆርሞን ህክምና

ይህ ህክምና ደግሞ የሰውነት ሆርሞኖች እንዲጨምሩ በማድረግ የካንሰር ህዋሶቹ ማደግ እንዲያቆሙ ወይም እድገታቸውን የመግታት ህክምና ነው ይህ ህክምናም እንደ የጡት ካንሰርን፤ፕሮስቴት ካንሰርን እና የእንቅርት ካንሰር የመሳሰሉትን የካንሰር አይነቶች ለማከም ህክምና ነው

ታርጌትድ ህክምና ወይም ሞለኪውላር ታርጌትድ ህክምና

የታርጌትድ ህክምና ማለት የካንሰር ሴሎች ለማደግ የሚያስፈልጓቸውን ሞሎኪውሎች ማዕከል ያደረገ የካንሰር ሴሎችን እድገት የማቆም ህክምና ነው ይህም ህክምና በአፍ የሚሰጥ እንዲሁም በደም ስር የሚሰጥ ህክምና ሊሆን ይችላል አንድ የካንሰር ስፔሻሊስት ሀኪም ሞሎኪውላር ታርጌትድ ቴራፒን ለታካሚው ከማዘዙ በፊት ታካሚው ታርጌትድ ህክምናን ቢወስድ ይጠቅመዋል ወይስ ብዙም ለውጥ አያመጣም የሚለውን ለማረጋገጥ የደም ወይም የህዋስ ምርመራ ይደረጋል

ኢሚውኖቴራፒ

ኢሚውኖቴራፒ ማለት የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል ስርዓት በማጎልበት የካንሰር ሴሎችን በራሱ መዋጋት እንዲችል የማስቻል ህክምና ነው የኢሚውኖቴራፒ ህክምና በክትባት መልክ የሚሰጡ ማለትም T-cell engineering monoclonal antibodies በሚባሉ መድሃኒቶች በመታገዝ በሰውነታችን ውስጥ T-cell የተባሉ ንጥረ ነገሮች ተመርተው የካንሰር ህዋሱን እንዲያጠቁ የማድረግ ህክምና ነው

የመቅኔ ቅየራ ህክምና ወይም የስቴም ሴል ንቅለ ተከላ

በዚህ ህክምና ላይ ከራሱ ከታካሚው ወይም ከለጋሽ ህዋስ በመውሰድ ማስተላለፍ የጎደለውን ለመሙላት መሞከር ነው አሁን ባለው ህክምና ይህንን በመጠቀም ሊታከሙ የሚችሉ የካንሰር አይነቶችን ስንመለከት ፡- የደም ካንሰር (Leukaemia) ሊምፎማ እና መልቲፕል ማይሊኖማ ይገኙበታል

ስለ ኬሞቴራፒ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (3 )
  • Your Rating