የጤና መረጃዎች

ኬሞቴራፒ እና የካንሰር ህክምና

Share:

ኬሞቴራፒ ወይም በተለምዶ ‘’ኬሞ’’ ማለት መድሀኒቶችን በመጠቀም በሰውነት ወስጥ የሚገኙ የካንሰር ሴሎችን ማጥቃት ነው፡፡ይህ ህክምና እንዴት ይሰራል ወደሚለው ስንመጣ ከተፈጥሮ ቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ የተራቡትን ሴሎችን እድገት በማቆም እንዲሁም ዝግ በማድረግ ነው፡፡

የኬሞቴራፒ ህክምና እንዴት ይሰጣል

የኬሞቴራፒ ህክምና አንድ ወይም ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ መድሃኒቶችን በሚዋጥ እንክብል መልክ ወይም በመርፌ መልክ በመስጠት ሊከናወን ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ የኬሞቴራፒ ህክምና የሚሰጠው በዙር ተከፋፍሎ ሲሆን የህክምናው ርዝመት የሚወሰነው እንደ ካንሰሩ አይነት እንዲሁም በሚወስደው የመድሃኒት ብዛት ነው፡፡አንድ የኬሞቴራፒ ዙር በአማካይ ከ2-4 ሳምንት ሊወስድ ሲችል እንደህመሙ አይነት ደግሞ ከዚህ ሊያንስም ሆነ ሊበልጥ ይችላል፡፡

የኬሞቴራፒ የጎንዮሽ ጉዳቶች

የኬሞቴራፒ ህክምና በባህሪው የሚያጠቃው ፈጣን እድገት ያላቸውን እንዲሁም ቶሎ የሚራቡትን ህዋሳት ነው በዚህም ምክኒያት በተፈጥሮ በፍጥነት የመራባት ባህሪ ያላቸውን እንደ ቆዳ ጸጉር አንጀት እንዲሁም መቅኔ ያሉ የሰውነታችን ጤነኛ ህዋሳትን ሊያጠቃ ይችላል፡፡በዚህም ተፅዕኖ ምክኒያት እነዚህ ምልክቶች ይከሰታሉ

 • የከንፈር መድረቅና መሰነጣጠቅ
 • የሰውነት መበለዝ
 • የአፍ መቁሰል
 • ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
 • የምግብ ፍላጎት መቀነስ
 • ተቅማጥ
 • የጸጉር መነቃቀል

የጎንዮሽ ጉዳቱ መባስ ወይም አለመባስ የሚወሰነው እንደ ታካሚው አጠቃላይ የጤና ሁኔታ እና የሚወስዳቸው የመድሃኒት አይነቶች ነው፡፡በኬሞቴራፒ የሚሰጠው ህክምና ውጤታማ እንዲሆን ታካሚዎች የሚሰጠውን ህክምና ተከታትለው ከመውሰድ ባሻገር ጤናማ የኑሮ ዘይቤን መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ይህም አመጋገብን ማስተካከል፤ንጽህናን መጠበቅ እና በቂ እንቅልፍ ማግኘትን ያጠቃልላል፡፡

ተያያዥ የካንሰር መረጃዎች ለምሳሌ ስለ ሊምፎማ መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

 • Readers Rating
 • Rated 2.6 stars
  2.6 / 5 (5 )
 • Your Rating