የክፍያ አይነቶች

በተገልጋዩ በቀጥታ የሚከፈል በጤና ኢንሹራንስ አማካኝነት ወይም በኤምባሲ ስፖንሰርነት ሊከፍል ይችላል ስለእያንዳንዱ የአከፋፈል ዝርዝር አይነት ከታች ያለውን መረጃ ማየት ይችላሉ

ሐኪምዎን ለማናገር ቀጠሮ ሲያሲዙ የትኛውን አይነት የአከፋፈል ሁኔታ መከተል እንዳለብዎ በመጠቆም እንረዳዎታለን

በቀጥታ የሚከፈል

ክፍያው የሚፈጸመው በባለቤቱ በቀጥታ ከሆነ ሀኪሙን ለማግኘት ቀጠሮ ሲያሲዙ ህክምናዎ የሚፈጀውን ግምታዊ ወጪ እንሠጥዎታለን

ይህ ግምታዊ ወጪ የሚሰጠውን ህክምና እና አገልግሎቶች የሚያጠቃልል ሲሆን በግምት ውስጥ ከሚካተተው ውጪ ተጨማሪ ህክምና ቢያስፈልግዎ የአከፋፈል ሁኔታውንም እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከል ይኖርብዎታል

በግምቱ ላይ የተቀመጠውን ጠቅላላ ወጪ ማንኛውንም የህክምና አገልግሎት ከማግገኘትዎ በፊት የተጠቀሰውን ክፍያ ተቀማጭ ማድረግ ይኖርብዎታል

በዋናነት በሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ‹ ታይ ባህት› መክፈል የሚችሉ ሲሆን ያንን ማድረግ ካልተቻለ እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ምንዛሪዎችን በመጠቀም ክፍያውን መፈጸም ይችላሉ

የክፍያውን ሁኔታ ስንመለከት በጥሬ ገንዘብ ክሬዲትካርድ ዴቢት ካርድ ወይም በአለም አቀፍ ባንክ ማስተላለፍ ይቻላል

ይዘው የመጡት ገንዘብ እኛ ከምንቀበላቸው የገንዘብ አይነቶች ውስጥ መካተቱን እንዲሁም በሆስፒታላችን ምንዛሪው ምን ያክል እንደሆነ ያረጋግጡ

ቬጂታኒ ሆስፒታል ክፍያ የሚቀበለው፡-

በጥሬ ገንዘብ፡-በታይ ባህት ወይም ሆስፒታላችን በሚቀበላቸው ሌሎች አለም አቀፍ መገበያያዎች

በሀዋላ ማስተላለፍ ፡-ደረሰኙን ማረጋገጥ ይረዳን ዘንድ ከ 5 የስራ ቀን በፊት ቢፈጸም መልካም ነው

ክሬዲት ካርድ/ዴቢት ካርድ

በሚከተሉት አለም አቀፍ የክፍያ መረቦች መክፈል ይቻላል፡-ቪዛ ካርድ ማስተር ካርድ አሜሪካን ኤክስፕረስ ዲነርስ ክለብ ኢንተርናሽናል ጄሲቢ እንዲሁም ቻይና ዩኒየን ፔይ

ማሳሰቢያ ፡- ተኝተው የሚታከሙ ከሆነ ህክምናው የሚፈጀውን ወጪ በተሠጥዎ ግምታዊ ዋጋ መሰረት ሙሉ በሙሉ በቅድሚያ ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል

በቬጂታኒ ሆስፒታል ተቀባይነት የማይኖራቸው የክፍያ አይነቶች

  • ማንኛውም አይነት ቼክ
  • የታይላንድ ያልሆነ ወይም ከላይ የተገለጹትን ሲስተሞች የማይጠቀም ዴቢት ካርድ ለበለጠ መረጃ በሀገርዎ የሚገኙትን ሪፈራል ቢሮ  የጉዞ አስተባባሪዎን ወይም ሆስፒታላችንን ያነጋግሩ

የጤና መድህን ኢንሹራንስ የገቡ እንደሆነ የኢንሹራንስ ድርጅቱ ምን ያክል ወጪዎን እንደሚሸፍን እና ከሆስፒታላችን ጋር ውል እንዳለው ያረጋግጡ

ቀጠሮ ለማሲያዝ እኛ ጋር ከመደወልዎ በፊት የኢንሹራንስ ካርድዎን የኢንሹራንስ ድርጅትዎን ስም እና ፖሊሲ ቁጥሮን ማዘጋጀትዎን እርግጠኛ ይሁኑ

ቬጂታኒ ሆስፒታል ከኢንሹራንስ ድርጅትዎ ጋር ውል ካለው የአከፋፈል ሁኔታው በስምምነቱ ላይ እንዳለው የሚፈጸም ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ለህክምናዎ ወጪ በቀጥታ ይከፍሉና የኢንሹራንስ ድርጅትዎ ብሩን እንዲመልስልዎት አስፈላጊው መረጃ ይዘጋጅሎታል

የጥቅል አገልግሎቶችን እንዲሁም ፕሮሞሽኖችን በተመለከተ ይህን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት ክፍያቸውን በቀጥታ(ታካሚው) ለሚከፍሉ ታካሚዎች ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን

የትገኛዎቹን የኢንሹራንስ አይነቶች እንደምንቀበል ለማወቅ ‹የኢንሹራንስ አገልግሎት አጋር ድርጅቶች› የሚለውን ገጽ ይመልከቱ

የኤምባሲ ስፖንሰርሺፕ

የህክምና ወጪዎ የሚሸፈነው በመንግስት ከሆነ በቅድሚያ ክፍያ ሳያስፈልግ ከኢምባሲዎ ይህን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ይዘው በመቅረብ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ