ከስኳር ነጻ የለስላሳ መጠጦች እውን ለጤና ጠቃሚ ናቸውን?

የጤና መረጃዎች
Featured Image

ከስኳር ነጻ ለስላሳ መጠጦች ስኳርን የሚተካ ንጥረነገር ወይም aspartame ይይዛሉ ፣ይህ ንጥረነገር እንደ ስኳር ጣፋጭ ጣዕም የሚሰጥ ሲሆን ስኳር ካላቸዉ ጣፋጮች ይልቅ በጣም አነስተኛ የምግብ ኃይል ይይዛል ስለሆነም ዜሮ-ካሎሪ ያደርገዋል:: ይሁን እንጂ ከስኳር ነፃ የሆኑ ለስላሳ መጠጦችን መጠቀም ክብደታቸውን መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች ጥሩ ምርጫ ላይሆኑ ይችላሉ፣ ምክንያቱም ብዙ በጠጣን ቁጥር የረሃብ ስሜታችን እየጨመረ ይሄዳል:: ከስኳር ነፃ ለስላሳ መጠጦች ዓላማቸው ከመጠን ያለፈ ውፍረትንና የስኳር በሽታን ለማስቀረት በምግብ እና በመጠጥ ውስጥ የሚጨመረውን ስኳር ለመተካትና ጣፋጭነቱን ለማስጠበቅ ነው::  እዉነታዉ ግን እነዚህ ስኳርን የሚተኩ ማጣፈጫወች ወይም aspartame መጠቀም ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት እና የስኳር በሽታ መንስኤ መሆናቸው ነው:: ምክንያቱም aspartame መጠቀም የሆርሞኖች መዛባት ስለሚያስከትሉ ሰውነታችን በጣም ስኳር ያለባቸው ምግቦችን እንዲፈልግ ያደርገዋል፣ይሄም ብዙ ምግብ እንድንመገብና የስኳር አጠቃቀማችን ወደነበረበት እንዲመለስ ያደርጋል::  የሰውነት ክብደትዎን ለመቀነስ ወይም ጤናዎትን ለመጠበቅ ከፈለጉ ከስኳር ነፃ ለስላሳ መጠጦች ምርጫወ ሊሆኑ አይገባም::  ስለዚህ ፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፣ የማዕድን ውሃ ፣ ወይም የተለያዩ ፍራራፍሬወች የተቀላቀሉበት ውሃ መጠቀም የተሻሉ ምርጫዎች ሊሆኑ ይችላሉ:: 

ምናልባትም “ጨጓራ ውስጥ የሚገባ ፊኛ(Gastric balloon insertion)”   ሊረዳዎት ይችላል::  

ጨጓራ ውስጥ ስለሚቀመጥ ፊኛ የበለጠ ለማንበብ ይሄን ይጫኑ::

ስለ ጨጓራ ውስጥ የሚገባ ፊኛ(Gastric balloon insertion) መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

Readers’ Rating

0.0 out of 5 stars (based on 0 reviews)