የጤና መረጃዎች

ኢንዶስኮፒን ( Esophagogastroduodenoscopy ) ለምርመራ እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል?

Share:

የላይኛው ኢንዶስኮፒ ( Esophagogastroduodenoscopy )  ጨጓራ፣ ዶደነም እና የአንጀታችን አካባቢ ኢንዶስኮፒን በመጠቀም የሚደረግ የምርመራ ሂደት ነው። 

በዚህ ዘመን ያሉ የኢንዶስኮፒ( Esophagogastroduodenoscopy ) መሳሪያወች ድሮ ከነበሩት ግዙፍ ለአያያዝ አስቸጋሪ ከነበሩት ኢንዶስኮፒዎች የተለዩ ናቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ በሰፊው ጥቅም ላይ የዋሉት ኢንዶስኮፒዎች የፋይበር ኦፕቲክስ (fiber-optics) ቴክኖሎጅን በመጠቀም ብርሃን ለመስጠት እና ሰውነት ውስጥ ያለውን ምስል ሃኪሙ ወደሚመለከትበት ሌንስ በመላክ የበሽተኛው ችግር ምን እንደሆነ ለመመርመር ይጠቀማሉ ፡፡ 

ዘመናዊ የኢንዶስኮፒ( Esophagogastroduodenoscopy ) ዓይነቶች በጣም ቀጭን እና ለታካሚው ብዙም ምቾት የማይነሱ ናቸው፣ በተጨማሪም ለዶክተሩም ለአጠቃቀም ምቹ ናቸው፡፡ የዛሬዎቹ ኢንዶስኮፒዎች በቱቧቸው ጫፍ ላይ በተገጠመላቸው አነስተኛ ካሜራ በመጠቀም ተንቀሳቃሽ ምስልን ወደ ማሳያ ስክሪኑ ይልካሉ ፡፡ 

ሁለቱም ማለትም የመጀመሪያዎቹም ሆነ ዘመናዊ ስሪት ኢንዶስኮፒወች ተጣጣፊ ትቦዎች አሏቸው፣ የትቦው ጫፉ ወዴት አቅጣጫ መንቀሳቀስ እንዳለበት ምርመራውን (esophagogastroduodenoscopy ) የሚያከናውነው ሃኪም በሪሞት ይቆጣጠረዋል ፡፡

የላይኛው ኢንዶስኮፒ ( Esophagogastroduodenoscopy ) አሰራር ቅደምተከተል 

የኢንዶስኮፒ ምርመራ የሚያደርግ ታካሚ በምርመራ ሂደቱ ወቅት የታካሚውን vital signs ማለትም እንደ ሙቀት፣ የልብ ምት፣ የደም ግፊት፣ የኦክስጅን መጠን፣ ወዘተ መከታተል ያስፈልጋል ፡፡ በምርመራ ሂደቱ ወቅት ታካሚው ዘና እንዲል ለማድረግ ታካሚው መድሃኒት ይወጋል ፡፡  ትቦው ሲገባ ጉሮሮው እንዳያስቸግር ሐኪሙ ማደንዘዣ (local anesthetics) በታካሚው አፍ እና ጉሮሮ ላይ ይረጫል፣ እንዲሁም የታካሚውን ጥርሶች እና የኢንዶስኮፒ ትቦውን ከጉዳት ለመጠበቅ በታካሚው ጥርሶች ላይ የጥርስ መሸፈኛ ይደረግለታል ፡፡ 

የኢንዶስኮፒ ትቦውን በቀላሉ ለማስገባት እንዲመች ማንኛውም አርቴፊሻል ጥርስ (dentures) ከአፉ ይወገዳል ፣ እንዲሁም በሽተኛው በምርመራ ሂደቱ ወቅት በግራ ጎኑ እንዲተኛ ይደረጋል ፡፡ 

የጠበበ ወይም ሊዘጋ ያለ ጉሮሮ በሚያጋጥምበት ወቅትም ችግሩን ሊያስተካክል የሚችል ህክምና ይከናወናል ። 

የኢንዶስኮፒ ትቦው በጉሮሮ በኩል አልፎ ወደ ሆድ እና ዶደነም ይደርሳል ፡፡ የጨጓራ ግድግዳ ካሜራውን እንዳይሸፍን እና ምስሉ አልታይ እንዳይል አየር ወደ ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል ፡፡ 

በቅድሚያ ትቦው በሚገባበት ወቅት ምርመራውን ከጉሮሮ ይጀምራል ፡፡ ከዛም የጨጓራ ግድግዳ እና የላይኛውን የዶደነም ክፍል ካሜራው በቦታው ሲደርስ ይመረምራል ፡፡  ኢንዶስኮፒውን በመጠቀም የቲሹ ናሙና (biopsies) ይወሰዳል ፡፡

የኢንዶስኮፒ ጥቅም

ኢንዶስኮፒ(Esophagogastroduodenoscopy) በርካታ የጨጓራና የስርአተ ልመት ችግሮችን ለመመርመር ያገለግላል ፡፡  እንደ የሆድ ህመም ፣ የመዋጥ ችግር ፣ ደረታችን ላይ የማቃጠል ስሜትና የጨጓራ አሲድ መርጨት ፣ የማያቋርጥ ትውከት እና ደም የቀላቀለ ሰገራ ያሉ ምልክቶች በስተጀርባ ያለውን መንስኤ ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ዶክተሮች የሚጠቀሙበት እና በአንጻራዊነት ፈጣንና ህመም የሌለው መመርመሪያ መሣሪያ ነው ፡፡

በሽተኛው ቀጣይ የሆነ የጨጓራ ​​ወይም የምግብ መፈጨት ችግር ካለበት የታካሚውን ሁኔታ በየጊዜው ለመቆጣጠር እንደ minimally-invasive procedure ማለትም ሰውነቱ ላይ መቅደድ ሳያስፈልግ ለመከታተል ያገለግላል ፡፡  አጠቃላይ የምርመራ ሂደቱ ከአንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የሚከናወን በመሆኑና ታካሚው ሆስፒታል መተኛት ስለማያስፈልገው የምርመራ ሂደቱን በአንድ ቀን ውስጥ ማጠናቀቅ ይችላል ፡፡ 

በተጨማሪም ኢንዶስኮፒ (Esophagogastroduodenoscopy) ወደ ሆድ ውስጥ የገቡ ባዕድ ነገሮችን ለማስወገድ ያገለግላል ፡፡  በቀዶ ጥገና ወቅት የደም መፍሰስን ለመቆጣጠርም ኢንዶስኮፒን እንጠቀማለን ፡፡ 

ማንኛውም የጨጓራ ​​ወይም  የስርአተ ልመት ችግር ካለብዎ በቬጅታኒ ሆስፒታል የጨጓራ አንጀት እና ጉበት ምርመራ ክፍል (Gastroenterology and Hepatology) ጋር ቀጠሮ ይያዙ ፡፡  ዶክተሮቻችን ኢንዶስኮፒን ጨምሮ ሌሎች ዘመናዊ የምርመራ ቴክኒኮችን በመጠቀም ፈጣን ምርመራ እና ውጤታማ ህክምናዎችን  ያሰጣሉ ፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 4.4 stars
    4.4 / 5 (4 )
  • Your Rating



Related Posts