የጤና መረጃዎች

የጉበት ካንሰር (Liver cancer) ምልክት የሌለው ገዳይ በሽታ ነው

Share:

አብዛኛወቹ የጉበት ካንሰር (Liver cancer)ያለባቸው በሽተኞች ምንም አይነት የበሽታ ምልክት አያሳዩም። ነገር ግን  የተወሰኑ አጠራጣሪ የሆኑ ምልክቶች ይኖራሉ ለምሳሌ የሆድ ህመም፣ ሆዳችን ሙሉ የመሆን ስሜት፣ ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የአይናችን ቀለም ቢጫ መሆንና ከበድ ያለ ደረጃ ላይ ከደረሰ ሆድ ላይ ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ መጠራቀም (ascites) ምልክቶችን ያሳያል። በዋናነት በአልትራሳውንድ፣ ኤምአርአይ (MRI)፣ ሲቲ ስካን (CT scan) እንዲሁም የጉበት ተግባርን ለመመርመር የደም ምርመራ ወይም ባዮፕሲ በመውሰድ ምርመራ ይደረጋል።

የጉበት ካንሰር (Liver cancer) የምርመራ ቅደም ተከተል፦

  • ስላለውና ስለነበረው የህመምና የህክምና ታሪክ ታካሚውን በመጠየቅ መረጃ መውሰድ
  • የጉበትን ተግባርና የካንሰር ተጋላጭነትን ለማወቅ የደም ምርመራ ማድረግ። እንዲሁም በሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ተጋላጭ መሆን አለመሆናችን በደም ምርመራ ማረጋገጥ
  • የሲቲ ስካን (CT scan) ወይም ኤምአርአይ (MRI) ምርመራ ማድረግ

የጉበት ካንሰር (Liver cancer)እና Cholangiocarcinoma (bile duct ካንሰር) መከላከያ መንገዶች፡

  • ጥሬ ስጋ ወይም ከሃይቅ እና ወንዝ የሚወጡ አሳወችን ስጋ በጥሬው አለመመገብ
  • የአልኮል መጠጦችን ማስወገድ
  • በሄፓታይተስ ቢ እና ሲ በሽታ ላለመያዝ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እነዚህ በሽታወች ለጉበት ካንሰር (Hepatocellular Carcinoma) ተጋላጭ ያደርጋሉ።
  • Readers Rating
  • Rated 3.8 stars
    3.8 / 5 (3 )
  • Your Rating




Related Posts