የጤና መረጃዎች

የጉበት በሽታ አይነቶች ምልክቶች እና ህክምናው

Share:

የጉበት በሽታ በአሁኑ ሰኣት ብዙ ሰዎችን እያጠቃ የሚገኝ እና መፍትሄ ያልተገኘለት መሆኑ ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ 5 አይነት የጉበት በሽታ ቫይረስ አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም ሄፓታይተስ ኤ፤ቢ፤ሲ፤ዲ እና ኢ ይባላሉ፡፡ከእነዚህ ውስጥ ግን በሽታን በማምጣት የሚታወቁት ቢ እና ሲ የተባሉት ሲሆኑ ሄፓታይተስ ቫይረስ ዲ እና ኢ ደግሞ ብዙም የተለመዱ አይደሉም፡፡

ያልጠናበት ህመምተኛ የሚያሳያቸውን ምልክቶች ስናይ ትኩሳት፤ ድካም ድካም የማለት ስሜት ፤ማቅለሽለሽ፤የምግብ ፍላጎት ማጣት፤የሰውነት ሽፍታ እንዲሁም የመገጣጠሚያ ህመም ሲሆኑ ትኩሳቱ በጊዜ ሂደት እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን በስተመጨረሻም የታካሚው ሰውነት እና አይኖች ቢጫ መሆን ሊኖር ይችላል፡፡የጠና የጉበት ህመም በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ግን በአብዛኛው የሚታዩ ምልክቶች ባይኖሩም እንደ ድካም እና የመዛል ስሜት ይስተዋልባቸዋል፡፡በሽታው ሳይታከም ከቆየ ወደ Cirrhosis እና የጉበት ካንሰር ሊለወጥ ይችላል፡፡ታማሚው ያለበትን የጉበት ቫይረስ አይነት ለመለየት ቀለል ያለ የደም ምርመራ ማድረግ ይቻላል፡፡የእያንዳንዱን አይነት የጉበት በሽታ በዝርዝር ስናይ

ሄፓታይተስ ኤ፡-ይህ አይነቱ የጉበት ህመም የሚተላለፈው በቫይረሱ የተበከለ ምግብ እና መጠጥ በመውሰድ ነው፡፡ህጻናት ላይ ምንም አይነት ምልክት የማያሳይ ሲሆን አዋቂዎች ላይ ግን ከላይ የተገለጡትን ምልክቶች እንደ የአይን እና ሰውነት ቢጫ መሆን፤ድካም፤ማቅለሽለሽ የመሳሰሉትን ምልክቶች ይስተዋላሉ፡፡

ሄፓታይተስ ቢ፡-ሄፓታይተስ ቢ እንደ ሲርሆሲስ እና የጠና የጉበት ህመም በማምጣት ይታወቃል፡፡መተላለፊያ መንገዶቹን ስናይ እንደ መርፌ እና ምላጭ የመሳሰሉ የተበከሉ ስለታማ ነገሮች፤ከእናት ወደ ልጅ እና የገብረ ስጋ ግንኙነት ይጠቀሳሉ፡፡ወደ ህክምና አማራጮቹ ስናይ የጠና ህመም የሌለባቸውን ታካሚዎች እንደሚያሳዩት የህመም ምልክቶች ሆስፒታል መተኛትም ቢያስፈልግ አስተኝቶ በማከም ህክምናውን መስጠት ሲቻል የጠና ህመም ያለባቸውን ግን በደም ውስጥ የሚገኘውን የቫይረሱን ቁጥር (viral laod) እንዲሁም የጉበት መቆጣትን የሚቀንሱ በመርፌ እና በሚዋጥ እንክብል መልክ የሚሰጡ ሲሆኑ ይህም የበሽታውን ወደ ሲርሆሲስ እና የጉበት ካንሰር መቀየር እድሉን ይቀንሳል፡፡

ሄፓታይተስ ሲ ፡- ልክ እንደ ሄፓታይተስ ቢ ሁሉ ሄፓታይተስ ሲም ለጉበት ካንሰር እና ሲርሆሲስ ለሚባለው የጠና የጉበት ህመም የሚዳርግ ሲሆን መተላለፊያ መንገዶቹም ተመሳሳይነት አላቸው፡፡እስከዛሬ ድረስ ሄፓታይተስ ሲ ን ለመከላከል፤ የሚያገለግል ክትባት ያልተገኘ ሲሆን ሄፓታይተስ ሲ በሽታ ታማሚዎችም የተለየ የሚያሳዩት ምልክት የለም በሽታው መኖሩን ለማወቅም የደም ምርመራ ማድረግ የሚቻል ሲሆን ወደ ህክምና አማራጮቹ ስንመለከት በሳምንት አንድ ጊዜ የሚሰጥ የመርፌ ህክምና እና ለ24-48 ሳምንታት የሚዋጥ መድኃኒት ይገኙበታል፡፡

ጠቃሚ ምክሮች

 • የአልኮል መጠጥን እና ሲጋራ ማጨስ ማቆም
 • ማንኛውንም አይነት መድኃኒት ከመውሰዳችን በፊት ለጉበት ጉዳት የሚያጋልጥ መሆኑን ማረጋገጥ
 • የባህል መድኃኒቶችን ከመውሰድ መቆጠብ
 • በቂ እረፍት ማድረግ
 • ጫና የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ መቆጠብ
 • እንደ ሲርሆሲስ እና የጉበት ጮማ መኖራቸውን ለማረጋገጥ በየጊዜው ክትትል ማድረግ
 • ከታማሚው ጋር በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ካሉ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ መኖሩን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ማድረግ እንዲሁም ክትባት መውሰድ

ህክምና ጀምረው ከሆኑ ደግሞ ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ህክምናዎትን በሚገባ መከታተል ያስፈልጋል

የጉበት በሽታን (ሄፓታይተስ) እንዴት ማስወገድ እንደምንችልና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የGastroenterology እና Hepatology ማዕከልን ያነጋግሩ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

 • Readers Rating
 • Rated 2.5 stars
  2.5 / 5 (24 )
 • Your Rating
Related Posts