የጤና መረጃዎች

የጉበት በሽታን (ሄፓታይተስ) እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

Share:

ጉበት በበሽታ ሲጠቃ እና የጉበት ብግነት ሲከሰት የጉበት በሽታ ይባላል ፡፡  አምስት ዓይነት የጉበት በሽታን ዓይነቶች አሉ ፣ በብዛት የተለመዱት ግን ሄፓታይተስ ኤ ፣ ቢ እና ሲ ናቸው ፡፡ ሁሉም አይነት በሽታዎች ጉበት ላይ በተለያየ ደረጃ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።  በጣም የከፋ ጉዳት የሚያመጡት ግን ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ናቸው ፡፡

ቫይረሱ በበርካታ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን ማለትም በምግብ ፣ በውሃ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ይተላለፋል በመሆኑም ክትባት በመውሰድ በሽታውን በተሻለ መልኩ መከላከል ይቻላል ፡፡

ህፃናት እድሜቸው አንድ ዓመት ሳይሞላ ለቫይረሱ የመከላከያ ክትባት መውሰድ ይችላሉ ።  አዋቂዎች ደግሞ ክትባቱን በማንኛውም ጊዜ መከተብ ይችላሉ ፣ አብዛኛውን ጊዜ የመጀመሪያው ክትባት ከተሰጠገ ከአንድ እና ከስድስት ወር በኋላ የክትባቱን አቅም ከፍ ለማድረግ ቀጣይ ዙር  ክትባቱ ይሰጣል ፡፡ 

የንጽህና አጠባበቃቸው ጥሩ ወዳልሆኑ አካባቢዎች የምንጓዝ ከሆነ ወይም የውሃ እና የምግብ አቀራረባቸው ብዙም የማያስተማምኑ አካባቢዎች የምንጓዝ ከሆነ ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግና ክትባት መውሰድ ይኖርብናል ፡፡ በየትኛውም ዓለም ላይ ሆነው በሄፓታይተስ ሊያዙ ስለሚችሉ የተለመዱ ጥንቃቄዎችን የማድረግ ልምድዎትን ማዳበር አለብዎት።

የሄፕታይተስ በሽታን ለመከላከል የተለመዱ ቅድመ ጥንቃቄዎች

የተወሰኑት ቅድመ ጥንቃቄዎች ከባድ መስሎ ሊሰማዎት እና የአኗኗር ዘይቤዎት ጋር አብረው ላይሄዱ ይችላሉ ፡፡ ለቫይረሱ መከላከያ ክትባት ከአሁን በፊት አግኝተው ከነበረ የተወሰኑት ቅድመ ጥንቃቄዎች ላያስፈልጉ ይችላሉ ፡፡ ይሁን እንጂ ከጉዞዎ በፊት ክትባት ማግኘት ካልቻሉ እነዚህን የጥንቃቄ እርምጃዎች ማድረግዎ በበሽታውን የመያዝ እድልዎትን ሊቀንሱ ይችላሉ። 

ቫይረሱ በምንነካቸው ነገሮች እዲሁም በምግብነት ወደ ሰውነታችን በምናስገባቸው ነገሮች ሁሉ ሊተላለፍ ይችላል ፡፡ ቀኑን ሙሉ እጆችዎን በደንብ የመታጠብ ልምድ ይኑርዎት ፡፡ የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሽ አልኮል ወይም የእጅ ሳሙና ይጠቀሙ።  ከቤት ውጭ በሚወጡበት እና የመገልገያ ዕቃዎች ከነኩ በኋላ አይኖችዎን ፣ አፍዎን ወይም አፍንጫዎን ከመንካት ይቆጠቡ ወይም ከመንካትዎ በፊት እጅዎትን ይታጠቡ ፡፡ 

ለመጠጥ እና ጥርሶችዎን ለመቦረሽ የታሸገ ውሃ ብቻ ይጠቀሙበት ፡፡  ታይላንድ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ በረዶ በነጋዴዎች ይቀርባል ይሁን እንጂ በረዶው ለማምረት የተጣራ ውሃ ስለሚጠቀሙ በረዶውን ለመጠቀም ምንም አይነት ስጋት አይኖርም ፡፡ ነገር ግን የማያውቁት አካባቢ ሄደው ባር ወይም ሬስቶራንቶች ውስጥ ገብተው የበረዶን አመጣጥ ካላዎቁ በረዶ ያለበት መጠጥ ከማዘዝ ይታቀቡ ፡፡ 

የጎዳና ላይ ምግቦች እንዲሁ ቫይረሱን ሊያሲይዙን ይችላሉ ፡፡ ጎዳና ላይ የሚሸጡ የወተት ተዋፆችን እንዲሁም ማንኛውም በደንብ ያልበሰለ ሥጋ ፣ ዶሮ ወይም ዓሳ መጠቀም ያስወግዱ ፡፡ 

አትክልቶች እና ፍራፍሬዎችን ለማጠቢያነት የሚጠቀሙት ውሃ ቆሻሻ ስለሚሆን ቫይረሱን ሊይዙ ይችላሉ ፡፡ ያልቀቀሉ አትክልቶችን ባለመመገብና  የማይላጡ ፍራፍሬዎችን ከመመገብ በመቆጠብ በበሽታው የመያዝ እድላችን መቀነስ ይቻላል ፡፡

የሄፕታይተስ በሽታ ምልክቶች እና ህክምናው

የሽንት ቀለም መጥቆር ፣ መጠነኛና የማያቋርጥ ትኩሳት ፣ የሆድ ህመም ፣ የቆዳ ወይም አይኖቻች ቀለም ቢጫ መሆን ፣ ግራጫ ቀለም ያለው ሰገራ ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ድካም ምልክቶችን ካስተዋሉ ወደ ቬጅታኒ ሆስፒታልን ይጎብኙ ። 

የቬጂታኒ ሆስፒታል ዶክተሮች የጤና ምርመራዎችን እንዲሁም ሰውነትዎ የሄፓታይተስ ቫይረስ መከላከያ (hepatitis antibody) ማዘጋጀቱን ለማረጋገጥ የደም ምርመራ ያደርጋሉ ፡፡  ሄፓታይተስ A ካለብዎ በሽታው ቀላል የሚባል ነው ፡፡  በሁለት ወራት ውስጥ በሽታው ከሰውነት ይጠፋል ምግብ በጥሩ ሁኔታ እስከተመገቡ እና በቂ ውሃ እከጠጡ ድረስ ጉበትዎ ላይ ዘላቂ ጉዳት አያስከትልም ፡፡

ነገር ግን ሄፓታይተስ B ወይም C ካለብዎ ለስድስት ወር ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ይቆያል እንዲሁም ቫይረሱ ስር የሰደደ ሊሆንብዎ ይችላል ፡፡ ለረዥም ጊዜ የሚወሰድ መድሃኒት ሊያስፈልግ ይችላል። ሄፓታይተስ ቢ እና ሲን ለማከም የሚያገለግሉት መድኃኒቶች የተለያዩ ናቸው ስለሆነም ምርመራዎ በሚያደርጉበት ወቅት ልምድ ያለው ዶክተር ማየት አለብዎት ፡፡ 

የመድሃኒት ሕክምና ሄፕታይተስ ሲን በማከም ከ90 እስከ 100% ያህል ውጤታማ እንደሆነ ታይቷል ፣ አብዛኛዎቹ ህክምናዎች በቀጥታ ቫይረሱ ላይ የሚተገበሩ የፀረ-ቫይረስ መድሃኒቶች (DAAS) ላይ ያተኮሩ ናቸው።  ሕክምናው ከ 8 እስከ 12 ሳምንታት ሊወስድ ይችላል ፡፡  ባንኮክ ውስጥ የተሻለ የሄፓታይተስ የምርመራ እና ህክምና አገልግሎት ለማግኘት እንዲሁም በበሽታው ተጋልጫለሁ ብለው ከተጠራጠሩ ቬጅታኒ ሆስፒታልን ይጎብኙ።

  • Readers Rating
  • Rated 3.2 stars
    3.2 / 5 (46 )
  • Your Rating