ለህክምና ወደ ታይላንድ ሲመጡ ማዘጋጀት ያለብዎትን ነገሮች ያውቃሉ

ለህክምና ወደ ታይላንድ ሲመጡ ማዘጋጀት ያለብዎትን ነገሮች ያውቃሉ

የህክምና ጉዞዎን የተሳካ ለማድረግ የሚከተሉትን የማረጋገጫ ዝርዝሮች አዘጋጅተናል
 1. ፓስፖርትዎ ጊዜ ያላለፈበት መሆኑን ማረጋገጥ እና የሚሄዱበት ሀገር ያለ ቪዛ መግባት መቻልዎን ወይም ቪዛ እንደሚያስፈልግዎ ማረጋገጥ
 2. የጉዞ ኢንሹራንስ መግዛት ይህ የሚጠቅመው ካልታሰቡ አጋጣሚዎች ለምሳሌ የበረራ መሰረዝ የበረራ መዘግየት እንዲሁም የሻንጣ መጥፋት የመሳሰሉ ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት ነው
 3. አንዳንድ ታካሚዎች ጉዞዋቸውን ይበልጥ የተሳካ እና ምቹ ለማድረግ የጤና መድህን ዋስትና ይገባሉ ነገር ግን የገቡት የህክምና መድህን የህክምና ወጪዎን እንደሚሸፍን እርግጠኛ ይሁኑ
 4. ገንዘብን በተመለከተ አከፋፈሉን የሚፈፅሙት በጥሬ ገንዘብ ወይም በካርድ ሊሆን ይችላል ስለዚህ በቂ ገንዘብ መያዝዎን (ሂሳብዎ ላይ በቂ ገንዘብ መኖሩን )እንዲሁም የታይላንድ ሀገር ብር መዘርዘርዎን እንዳይረሱ
 5. ከህመምዎ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጠቃሚ የህክምና ማስረጃዎች ለምሳሌ ሀገርዎ የተሰራልዎት ምርመራ ካለ የራጅ ምርመራ የደም ምርመራ ውጤቶች በሀኪም የተጻፈልዎት የህክምና ማስረጃ ቢይዙ እዚህ ለሚያደርጉት ህክምና ጠቃሚነት ይኖረዋል
 6. የሚሄዱበትን የጤና ተቋም በህክምና ወቅት የሚረዳዎትን ሰው እንዲሁም መጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎን አድራሻ ማወቅዎን እርግጠኛ ይሁኑ
 7. ለጉዞዎ ቆይታ ሙሉ የሚበቃዎትን መድሀኒት መያዝዎን ያረጋግጡ
 8. የሚጓዙበትን ሀገር የአየር ሁኔታ ምን አንደሚመሰል ያጣሩ
 9. ከመጓዝዎ በፊት ክትባት ሊያስፈልግዎ ስለሚችል አስፈላጊውን ክትባት መውሰድዎን ያረጋግጡ
 10.  በጉዞዎ ወቅት አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎች ቢጠፋብዎ እንኳን ይህን ችግር ለማስተካከል ፓስፖርትዎን እና የክትባት ወረቀቶችዎን ኮፒ አድርገው ማስቀመጥዎን አይርሱ
 11. ትክክለኛውን የመጓጓዣ ትኬት መቁረጥዎን እንዲሁም አየር መንገድ ከደረሱ በኋላ የሚቀበልዎ ሰው መኖሩን ያረጋግጡ
 12. በተጨማሪም እነዚህን ነገሮች ቢያዘጋጁ መልካም ነው
  ለህክምና የሚሆኑ ምቹ የሆኑ ልብሶች እና ጫማዎች
  በመጨረሻም ተንቀሳቃሽ ስልክዎን እና ቻርጀር መያዝዎን አይርሱ

Vejthani Hospital เวชธานี