



የቀዶ ጥገና እና የአጥንት ስፔሻሊስት ቡድን
ቀዶ ጠጋኝ ሀኪሞቹን ጨምሮ በክፍሉ ውስጥ የሚሰሩ መላ ባለሙያዎች የረጅም ጊዜ ልምድ ያካበቱና አለም አቀፋዊ እውቅና ያላቸው ሲሆኑ ለደምበኞች ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጡ ሀብቶቻችን ናቸው፡፡
የቬጂታኒ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ክፍል አጠቃላይ የምርመራ፤የህክምና እና የአጥንት ቀዶ ጥገናን ያሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ነው፡፡አገልግሎቶቻችን በአደጋም ሆነ በተፈጥሮ ምክኒያት የሚመጡ ስብራት እና የውልቃት ችግሮችን ማስተካከል፤የስፖርት ህክምና ማማከር አገልግሎት፤የመገጣጠሚያ መቆጣት ህክምና፤ያልተመጣጠኑ እግሮችን ማስተካከል፤እጅ ላይ የሚፈጠሩ ግድፈቶችን ማስተካከል፤የጀርባ ህመም ህክምና፤የዲስክ መንሸራተት እና ሌሎች ከአጥንት እና ጡንቻ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች ያጠቃልላል፡፡የታካሚዎችንም ችግር ለማወቅ ወይም ለመመርመር እና ለማከም የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን ያሟላ ነው፡፡ሀኪሞቻችንን እንዲሁም አብረዋቸው የሚሰሩት ነርሶች የላቀ እውቀት ያላቸው እና የሀገሩንም ሰው ሆነ ከመላው አለም የሚመጡ አለም አቀፍ ታካሚዎችን በማገልገል ልምድ ያላቸው እንዲሁም ተወዳዳሪ የሆኑ ናቸው፡፡ ቬጂታኒ ሆስፒታል ከአለም አቀፍ ጥምር ኮሚሽን(JCI) እውቅናን ያገኘ ሲሆን ይህም ማለት በሆስፒታሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
የአገልግሎት ሰዓታት
ሰኞ - እሁድ : 08.00 am - 08.00 pm
ቦታ
የአጥንት ህክምና ማዕከል፣ 2ኛ ፎቅ የአጥንት ንጉስ ህንፃ ፣ ቬጅታኒ ሆስፒታል
ቀጠሮዎች እና ጥያቄዎች
ይደውሉ: (+66)2-734-0000 ext. 2298,2299
አገልግሎቶቻችን
- አጠቃላይ የአጥንት ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት
- በአደጋም ሆነ በስፖርት ምክኒያት የሚመጣ ስብራት እና ውልቃት ህክምና
- በስፖርት ማማከር
- በስፖርት ምክኒያት የሚመጣ ጉዳት እና ህመም ህክምና
- ሪውማቶይድ አርትራይትስ ህክምና
- የእግር እና ቁርጭምጭሚት ህክምና
- መጠነኛ የእጅ ቀዶ ህክምና
- የእጅ ወይም የእግር አለመመጣጠን ችግር ህክምና
- ስብራት እና ጉዳት ህክምና
- የትከሻ ቀዶ ህክምና
- አርትሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና
- የህጻናት የአጥንት ህክምና ማዕከል
- በቢሮ አቀማመጥ ችግር የሚመጡ ህመሞች
- በአደጋ ምክኒያት የሚመጣ የአጥንት ጉዳት ህክምና








































