ስንገለገልበት የቆየ እና አሁንም ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ መሠረታዊ የሕክምና ዘዴ ነው። በተለይም ካንሰሩ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲሆን እና ከተጠቃው አካባቢ ላይ ብቻ የተገደበ ማለትም የካንሰር ሕዋሳት መስፋፋት ባላደረገበት ሁኔታ ካንሰርን ከሰውነት ለማስወገድ የሚያገለግል መደበኛ ሕክምና ነው።
የካንሰር ሴሎችን ለመቆጣጠር ወይም ለመግደል ጨረርን የምንጠቀምበት የሕክምና ዘዴ ነው። የጨረር ሕክምና ካንሰሩ ያልተሰራጨ እና አንድ የአካል ክፍል ላይ ብቻ ያለ ከሆነ በርካታ የካንሰር ዓይነቶችን ለማዳን ሊያገለግላል ይችላል። አዲሱ የጨረር ሕክምና ዘዴ Intensity-Modulated የጨረር ሕክምና (IMRT) ነው። IMRT በታቀደው የካንሰር ህዋስ ላይ አስፈላጊውን የጨረር መጠን በመመጠን ለማድረስ የኮምፒውተር ቁጥጥርን የሚጠቀም ዘመናዊ ትክክለኛ የራዲዮቴራፒ ሕክምና ዘዴ ነው። በዚህ አዲስ ዘዴ (IMRT) የጨረሩ የጎንዮሽ ጉዳት ዝቅተኛ ነው።
– አንድ ወይም ከዚያ በላይ መድኃኒቶችን እንደ መደበኛ የኪሞቴራፒ ሕክምና አካል የሚጠቀም የሕክምና ዓይነት ነው። ኪሞቴራፒ በመላው ሰውነት ውስጥ ሊሠራ ይችላል። ከቀዶ ጥገና በፊት ዓላማው በሽታውን ለማዳን ሆኖ ሊሰጥ ይችላል። “Neoadjuvant Chemotherapy” የተባለው የኪሞቴራፒ አይነት ካንሰሩ በቀዶ ጥገና መወገድ እስከሚችልበት ደረጃ ድረስ የካንሰር እጢውን መጠን ለመቀነስ ያገለግላል። አዲስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት neoadjuvant chemotherapy የወሰደ ማንኛውም ሰው የተሻለ ውጤት ይኖረዋል እንዲሁም ህይወቱን ሊያራዝም እና ምልክቶችንም ሊቀንስ ይችላል።
አንዳንድ ሆርሞኖች የካንሰሮችን እድገት የሚያባብሱ በመሆናቸው የበሽታውን እድገት ወይም መስፋፋት ለማስቆም ወይም ለማዘግየት በሰውነት ውስጥ የሆርሞኖችን መጠን ዝቅ ወይም ከፍ የሚያደርግ ሕክምና ነው። ይህ ዘዴ የጡት፣ የፕሮስቴት እና የታይሮይድ ካንሰርን ለማከም ያገለግላል።
የካንሰር ሕዋሳት ለማደግና ለመኖር ከሚያስፈልጓቸው የተወሰኑ ሞለኪውሎችን ውስጥ ላይ ጣልቃ በመግባት የካንሰር ሕዋሳትን እድገትን ለመገደብ ከሚጠቀሟቸው መድኃኒቶች ውስጥ molecular targeted therapy አንዱ ነው። Molecular Targeted Therapy በአፍ የሚወሰዱ አነስተኛ ሞለኪውላር ኢንሂቢተር ወይም በደም ሥር የሚሰጡ ሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ አካላት ሊሆን ይችላል። ሐኪሙ ታርጌትድ ህክምናን ከማዘዙ በፊት ሕብረ ሕዋሱን ወይም ደም ለሞለኪውላዊ ምርመራ ይላካል።
ያለንን የበሽታ መከላከያ አቅም በማሻሻል ሰውነታችን የካንሰር ሴሎችን በራሱ ለመዋጋት ወይም ለመግደል እንዲችል የሚያደርግ የተለያዩ የፈጠራ ሕክምናዎች ስብስብ ነው። ኢሚውኖቴራፒ ምናልባት ክትባት፣ ቲ-ሴል ኢንጂነሪንግ (T-Cell engineering) ወይም በሽታን ለመዋጋት የሚያስችሉን T-Cell የሚያነቃቁ ሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ አካላት (monoclonal antibodies) ሊሆኑ ይችላሉ።
እነዚህ ሁለት የካንሰር ህክምና ዓይነቶች ከታካሚው አካል ተለይተው ወይም ከለጋሾች ሊወሰዱ ይችላሉ። አሁን ላይ ባሉ ጥናቶች መሰረት stem cell ንቅለ ተከላ ብዙውን ጊዜ እንደ ሉኪሚያ፣ ሊምፎማ እና መልቲፕል ማይሎማ ባሉ ጥቂት የካንሰር ዓይነቶች ላይ ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል።