የታይሮይድ በሽታ (Thyroid Disease) ለሕይወት አስጊ የሆነ በሽታ ነው
ያልተለመደ የምግብ መፈጨት (metabolism) ችግር ፣ የስሜት መለዋወጥ እና የፀጉር መነቃቀል ያጋጥሙዎታል? እነዚህ የታይሮይድ በሽታ (Thyroid disease) ምልክቶች ናቸው። ለወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል አሁንኑ ምርመራ ማድረግና የሕክምናን አገልግሎት ማግኘት አለብዎት፡፡
ታይሮድ በፊት ለፊት አንገታችን ላይ የሚገኝ እጢ ሲሆን ሰውነታችን በሁሉም መልኩ የተስተካከለ አሰራር እንዲኖረው የሚያደርጉ ሆርሞኖችን ያመርታል ይህ እንዲሆን ደግሞ “አዮዲን” የተባለ ንጥረ ነገር ያስፈልገዋል፡፡የአዮዲን መጠን አነስተኛ ወይም ከመጠን ማለፍ ደግሞ አጠቃላይ የሰውነታችንን ስርዓት ያውካል፡፡
የታይሮድ እጢ በፍጥነት የሚሰራ ከሆነ ብዙ ሆርሞን በማምረት የሰውነታችንን ጤነኛ አሰራር እንዲታወክ ሊያደርግ ይችላል
ይህም ችግር “ሀይፐርታይሮይዲዝም” በመባል ይታወቃል፡፡ይህ ችግር ሲያጋጥም በእያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል ላይ የሚያሳየው ምልክት ከሰው ሰው ይለያያል፡፡
ሀኪሙ የታካሚውን እድሜ የሰውነት ሁኔታ እንዲሁም የበሽታውን ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊውን የህክምና አይነት የሚመርጥ ሲሆን ታካሚውም የታዘዘለትን መድሃኒት በአግባቡ በመውሰድ የአዮዲን መጠኑ ከፍ ያለ ምግብን በመቀነስ እና ሲጋራ ባለማጨስ ህክምናውን ማገዝ ይኖርበታል
ዶ/ር አሩን ኮንግቾ (በቬጂታኒ ሆስፒታል ኢንዶክሪኒሎጂስት)
[doctor_blog doctor_code=”91972″]
ዶ/ር አሩን ኮንግቾ (በቬጂታኒ ሆስፒታል ኢንዶክሪኒሎጂስት)