ፔሪፈራል የደም ቧንቧ በሽታ (Peripheral Artery Disease) ልንጠነቀቅበት የሚገባ የተለመደ የጤና ሁኔታ ነው
ስለ ፔሪፌራል የደም ቧንቧ በሽታ (PAD)፣ እንደ ክላዲኬሽን (Claudication) ያሉ ምልክቶችን እና ውጤታማ የአኗኗር ዘይቤ አያያዝን ይማሩ። ቀደም ብሎ ማወቅ ለህክምና አስፈላጊ ነው።

ቬጅታኒ ሆስፒታል በአጥንት ክፍል በሚሰጠው ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎቶች ምክንያት “የአጥንት ንጉሥ” በመባል ይታወቃል። ነገር ግን የቬጂታኒ ሆስፒታል የሚሰጠው ቁልፍ አገልግሎት ይህ ብቻ አይደለም ይልቁንም ከብዙዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው “የስኳር በሽታ” በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረ እና አሁንም እየጨመረ ያለ በሽታ ነው። በችግሩ ለሚሰቃዩ እና የህክምና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሕክምናው ማህበረሰብ መፍትሄ እንዲፈልግ እና የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያቀርብ አስቸኳይ ጥሪ ያስፈልጋል። ለዚህም ነው የቬጂታኒ “Diabetic Foot and Wound Center” የተጀመረው።
በዚህ ማእከል ውስጥ የታካሚውን ሁለንተናዊ ጤንነት ለማስጠበቅ የተሟላ ህክምና መስጠት የሚያስችሉ አዳዲስ ዘመኑ ያፈራቸው የሕክምና መሣሪያዎች እና በሳይንስ የተረጋገጡ የህክምና ዘዴዎች እንዲሁም አሰራሮችን ያገኛሉ። እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ከሁሉም ዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ዶክተሮች ጋር በማቀናጀት አገልግሎቱ ይሰጣል። ይህ አይነት አቀራረብ ባለብዙ ዲሲፒሊን በመባል የሚታዎቅ ሲሆን በተቻለ መጠን ጥሩ ውጤት ላይ ለመድረስ እውቀታቸውን እና ሙያቸውን ሳይሰስቱ የሚያጋሩ የዶክተሮች ቡድን ነው።
በቬጂታኒ የስኳር ህመምተኞች እግር እና ቁስል ህክምና ማዕከል የቴክኖሎጂ፣ ቴክኒክ እና አገልግሎቶች ውስጥ ለአብነት የሚከተሉትን ናቸው።
አገልግሎቶቻችን
ለቁስልሕክምናየምንጠቀምባቸውልዩልዩመሣሪያዎችእናየህክምናዘዴዎች — Special Equipment and Techniques for Diabetic Foot Ulcer Treatment
እነዚህን ሁሉ የተዘረዘሩ የአገልግሎት፣ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አንድ ሰው በቀላሉ የሚያስፈልገኝ ይሄ ብቻ ነው ብሎ ሊያስብ ይችላል። ነገር ግን በሰዎች ሕይወት ውስጥ ሁሉንም ነገር ሊቀይሩ የሚችሉ ግን ልንለካቸው የማይንችላቸው ትናንሽ ስውር ነገሮች አሉ።
በቬጅታኒ Diabetic Foot and Wound Center የቫስኩላር ቀዶ ጥገና ሐኪም Dr. Chukij Sritongsathian እንደተናገሩት “ለተሳካ ህክምና ቁልፍ ከሆኑት ነገሮች ዋነኛው ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን ብቻ ሳይሆን ከቴክኖሎጂው በስተጀርባ የሚሰሩ ለስራው ፍቅሩ ያላቸው ሐኪሞች ቁርጠኝነት ነው”። ይህን ሁሉ ማወቃችሁ ቬጂታኒ ሆስፒታል ምን ያክል ጥሩ ቴክኖሎጂዎች እና ልዩ የሆኑ ቴክኒክኮችን አጣምሮ በመያዝ የተሻለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት ምን ያህል ቁርጠኝነት እንዳለው ያሳየዎታል። በተጨማሪም የቫስኩላር ቀዶ ጥገና ሐኪም፣ ኢንዶክሪኖሎጂስት፣ የአጥንት ስፔሻሊስት፣ የተላላፊ በሽታዎች ስፔሻሊስት፣ ፊዚካልቴራፒስት፣ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሃኪም፣ የልብ ሐኪም፣ የኩላሊት ስፔሻሊስት እዲሁም እንደአስፈላጊነቱ የሌሎችም ብዙ የዶክተሮች ቡድን የጋራ ዕውቀት; የቬጂታኒ የስኳር ህመምተኛች እግር እና ቁስል ማዕከልን ያካተተ በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።