የጤና መረጃዎች

3 መደበኛ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴዎች

Share:

ጥቅምት ወር የጡት ካንሰር (Breast Cancer)ግንዛቤን ያከብራል። በታይላንድ ውስጥ ሴቶች ላይ የጡት ካንሰር (Breast Cancer)በጣም የተስፋፋ የካንሰር አይነት ሲሆን ከ 100,000 ሴቶች ውስጥ 28.6 የሚሆኑት በበሽታው ይያዛሉ።

የጡት ካንሰር (Breast Cancer)በመስፋፋቱ ምክንያት ከካንሰር ጋር በተያያዙ በሽታዎች ከፍተኛ የሞት መጠን ካላቸው መካከል ይጠቀሳል። የጡት ካንሰር (Breast Cancer) ምርመራ በማድረግ ቀደም ብሎ ማግኘቱ ዘላቂ የመፈወስ እድልን ስለሚያሳድግ የሞት መጠንን ለመቀነስ ጠቃሚ መሳሪያ ነው።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የጡት ስፔሻሊስት እና ኦንኮፕላስቲክ የጡት ቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ፒያሳክ ታሃራቫኒች መደበኛው የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast Cancer Screening) የሚከተሉትን ሶስት ደረጃዎች ያካተተ ነው ብለዋል:-

 1. በሐኪም የሚወሰድ የታካሚ የህክምና ታሪክ እና በጡት ቀዶ ጥገና ሐኪም የሚደረግ የጡት ምርመራ: ከ 40 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች በአመት አንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast Cancer Screening) እንዲያደርጉ ይመከራሉ።
 2. ማሞግራም (Mammogram) እና አልትራሳውንድ፡ በተለምዶ የምርመራ ውጤቶቹ በቢራድስ (BIRADS) ነጥብ (የጡት ምስል ቀረጻ እና ዳታ ሲስተም) ይታያሉ። ቁጥሮቹ ከ0-6 ይደርሳሉ:-
  • BIRADS 0 ማለት የተገኘው መረጃ ለምርመራ በቂ አይደለም ማለት ነው ፤ተጨማሪ ምርመራዎች ያስፈልጋሉ።
  • BIRADS 1 እና 2 ማለት ምንም አይነት የጡት ካንሰር (Breast Cancer) ስጋት አልተገኘም ማለት ነው ፤ ታካሚዎች ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶችን ለመፈለግ በዓመት አንድ ጊዜ የክትትል ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ።
  • BIRADS 3 ማለት የጡት ካንሰር (Breast Cancer) አደጋ መገኘቱን ያመላክታል ፤ ነገር ግን በሽታው የመከሰት እድሉ ከ 2% ያነሰ ነው ፤ በየ 6 ወሩ የክትትል ምርመራ እንዲደረግ ይመከራል።
  • BIRADS 4 ማለት የካንሰር አደጋ ከ2-95% እድል ተገኝቷል ማለት ነው ፤ ለማረጋገጫ ባዮፕሲ ይመከራል።
  • BIRADS 5 ማለት የካንሰር አደጋ ከ95 በመቶ በላይ እድል ሲኖረው የተገኘ ነው ማለት ነው ፤ ለማረጋገጫ ባዮፕሲ ይመከራል።
  • BIRADS 6 ማለት በባዮፕሲ ውጤቱ የተሰበሰበው ህዋስ ካንሰር እንደሆነ ያሳያል።
 1. ባዮፕሲ የጡት ካንሰርን (Breast Cancer) ለመመርመር እና ለማረጋገጥ አስፈላጊ ሂደት ነው። ይህ ዘዴ ጥቅም ላይ የሚውለው አንድ ታካሚ 3D ማሞግራም (Mammogram) እንዲሁም አልትራሳውንድ ሲደረግ እና ውጤቶቹ የ BIRADS ከ 4 ወይም 5 በላይ ሲያሳዩ ነው። ሶስት ዓይነት ባዮፕሲዎች ሲኖሩ እንደሚከተለው ናቸው:-
  • ፋይን ኒድል አስፓየሬሽን (Fine Needle Aspiration) ወይም ኤፍ.ኤን.ኤ (FNA)፡- ባለ 22-መለኪያ (ቦዶ) መርፌ ወደ እብጠቱ ውስጥ በማስገባት እና ከተጠረጠረው አካባቢ ህዋሶችን በማውጣት የካንሰር ህዋሳትን ለማግኘት ይረዳል። የዚህ ዘዴ ጠቀሜታው ከ1-2 ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚወስደው። የBIRADS ውጤታቸው 5 ለሆነ ወይም ለጡት ካንሰር (Breast Cancer) ከፍተኛ ተጋላጭነት ላለባቸው ሴቶች ተስማሚ ነው። የምርመራው ውጤት በሴሉላር ፓቶሎጂስት መተርጎም አለበት።
  • ኮር ኒድል ባዮፕሲ (Core Needle Biopsy) ፡ አንድ ትልቅ መርፌ በተጠረጠረው እብጠት ውስጥ ተመርቶ ከ 3-4 ህዋሶች ይቆርጣል። የዚህ ዓይነቱ ባዮፕሲ የሕዋስ አወቃቀሮችን እና ጉዳቶችን በበለጠ ዝርዝር ማየት ስለሚያስችል ለሕዋስ ምልከታ የበለጠ ትክክለኛነትን ይሰጣል። ኮር ኒድል ባዮፕሲ ወደ 30 ደቂቃ አካባቢ ሲወስድ ከሂደቱ በፊት የማደንዘዣ መርፌ ይሰጣል።
  • ቫክዩም አሲስት (Vacuum Assist) ፡ ትልቅ መርፌ ወደ እብጠቱ ይገባል። መርፌው ህዋሶችን በመምጠጥ በተደጋጋሚ እየቆራረጠ ወደ ቫክዩም ያስገባል። ይህም የሚጠቅመው ሙሉውን እብጠት ለማስወገድ ያስችላል። ሆኖም ግን ሙሉውን እብጠት ማስወገድ የሚመከረው ዶክተሩ እብጠቱ ካንሰር አለመሆኑን ሲተማመን ብቻ ነው። መርፌው ከመግባቱ በፊት አካባቢው ላይ ማደንዘዣ ይደረጋል። እንደ ቁስለቱ ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ሂደቱ ወደ 40 ደቂቃዎች ያህል ይወስዳል።

ትክክለኛው የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast Cancer Screening) የጡት ቀዶ ጥገና ሃኪም በማማከር እና ለበለጠ ትክክለኛ የምርመራ ውጤት ከማሞግራም (Mammogram) እና ከአልትራሳውንድ ጋር የታገዘ ጡት ምርመራን ያካትታል።

የምርመራ ውጤቶቹ BIRADS 4 ወይም 5 ነጥብ ከሆኑ ለታካሚው ከቀዶ ጥገናው በፊት ውጤታማ የሆነ ህክምና ለማቀድ ባዮፕሲ መደረግ ይኖርበታል ፤ ይህም ለበሽታው እና ላለበት የካንሰር ደረጃ በጣም ተስማሚ መሆን አለበት።

“ቀዶ ጥገና ሲባል ብዙ ታካሚዎች ሙሉውን ጡት ማስወገድ ያሳስባቸዋል። ግን እውነታው ለአንዳንድ ታካሚዎች በተለይም የመጀመሪያ ደረጃ ጡት ካንሰር (Breast Cancer)ላለባቸው ፤ እብጠቱ ትንሽ ከሆነ አጠቃላይ ጡትን ማስወገድ አያስፈልግም። በአሁኑ ጊዜ የጡት ማቆያ ቴክኒክ ቀዶ ጥገና አለ ፤ ነገር ግን ጡቱ ከሌላኛው ጋር ተመሳሳይነት ያለው መዋቅር እና መልክ እንዲኖረው ይጠይቃል። ሙሉውን ጡት እንዲወገድ ለሚያስፈልገው ሁኔታ ማስቴክቶሚም አለ ፤ ነገር ግን የጡት ቆዳን፣ የጡት ጫፍንና የአካባቢውን ቆዳ ሳይነካ እንዳለ ይጠብቃል። የማስቴክቶሚ ቀዶ ጥገና ከተደረገ በኋላ የጡት መልሶ መገንባት የሴትን ማንነት እና መተማመንን ለመጠበቅ ሊደረግ ይችላል።”

ዶክተር ፒያሳክ

ለበለጠ መረጃ እባክዎን የካንሰር ማዕከልን፣ በቬጅታኒ ሆስፒታል ያነጋግሩ።
ይደውሉ፡ 02-734-0000 Ext. 5500
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66) 0- 90-907-2560
ኢሜል፡ [email protected]

 • Readers Rating
 • Rated 5 stars
  5 / 5 (1 )
 • Your RatingRelated Posts