የጤና መረጃዎች

የጡት ህመም (Breast Pain)- ጡታችን ላይ ችግር ስለመኖሩ የማስጠንቀቂያ ምልክት ነው

Share:

በሴቶች ላይ የሚከሰት የጡት ህመም የጡት ካንሰር (Breast cancer) ተጋላጭ መሆናችን አመላካች ከሆኑ ምልክቶች አንዱ ነው፡፡ ምልክቶች በሚከሰቱበት ጊዜ ህመምተኛው የህመሙን መንስኤ ለማዎቅ በአስቸኳይ ወደ ህክምና መሄድ አለበት፡፡ የጡት ህመም በሁለት ይከፈላል እነሱም:-

  1. ዙር ጠብቆ የሚመጣ የጡት ህመም (Cyclical breast pain) ከወር አበባ ዑደት ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ይህ በአብዛኛው ሴቶች ላይ የሚከሰት የጡት ህመም አይነት ነው፡፡ በሰውነት ውስጥ የሆርሞኖች መዛባት በሚኖርበት ወቅት የሚከሰት ሕመም ሲሆን በውፃት (ovulation) ወቅት ጀምሮ የወር አበባው እስኪጀምር ድረስ ይቆያል፡፡ ሕመሙ አንዳንድ ጊዜ በመላው የጡታችን ክፍል፣ በአንደኛው በኩል ወይም በሁለቱም ጡቶች ላይ ሊከሰትና ህመሙ ብብታችን ድረስ ይወርዳል፡፡
  2. ዙር ጠብቆ የማይመጣ (Noncyclical breast pain) የጡት ህመም ከወር አበባዎ ዑደት ጋር የማይገናኝ ነው፡፡ ሕመሙ ብዙውን ጊዜ የማያቋርጥ ወይም በተወሰነ አካባቢ በጣም የሚከብድ ሲሆን የሚከሰተውም:-
    • ጤናማ ያልሆነ ጡት ሲኖረን; ለምሳሌ የጡት ካንሰር (Breast cancer)፣ ጡት ውስጥ ዕጢ ወይም እብጠት ሲኖር፣ ጡት ላይ ፈሳሽ የቋጠረ ነገር ሲኖር፣ ጡት ላይ ጉዳት ሲከሰት፣ ጡት ላይ ብግነት ሲከሰት (Mastitis)፣ መግል የያዘ ጡት (breast abscess)፣ ጡት ከማጥባት ጋር የተያያዙ ምልክቶች፣ እንዲሁም የጡት መጠንን ለመጨመር በሚደረግ ቀዶ ጥገና የሚከሰት የጎንዮሽ ጉዳቶች ሳቢያ ሊሆን ይችላል፡፡
    • በውጫዊ ተፅዕኖዎች ምክንያት የሚከሰቱ የጡት ችግሮች; ለምሳሌ የደረት ጡንቻ ውጥረት ወይም ጉዳት፣ የጎድን አጥንቶቻችን ከደረታችን የሚገናኙበት ለስላሳ አጥንት ላይ የሚከሰት ብግነት (Costochondritis)፣ በደረት እና የጎድን አጥንቶች ላይ የሚከሰት አደጋ ወይም ጉዳት።

ጡትን በራስን የመመርመር ተግባር (Breast self-examination) ከወር አበባዎ ዑደት ከሰባት ቀናት በኋላ በወር አንድ ጊዜ መከናወን አለበት፡፡ የጡትዎት ቆዳ ላይ ስርጉድ ያለ ነገር ወይም እብጥ ብሎ የወጣ ነገር መኖሩን ለማዎቅ የጡትዎን አካላዊ ገጽታ በመስታወት እያዩ መመርመር በጣም አስፈላጊ ነው። በቅርጽ፣ በመጠን፣ በይዘቱ ወይም በቀለም፣ ወይም ያልተለመደ ደም ወይም መግል መሰል ፈሳሽ የሚፈስ ከሆነ ወይም ከጡትዎት ጫፍ ወተት እንኳን የሚፈስ ከሆነ ይመልከቱ፡፡ ምርመራውን በሚያደርጉበት ወቅት እንደዚህ ያሉ ያልተለመዱ ሁኔታዎች ከተገኙ ወይም ያልተለመደ የጡት ህመም ካጋጠመዎት ለበለጠ ምርመራ ወዲያውኑ ዶክተርዎን ያማክሩ። በአሁኑ ጊዜ የ 3ዳይሜንሽናል ዲጂታል ማሞግራም ቴክኖሎጂ አለን (3D digital mammogram technology)። እንደ አልትራሳውንድ ካሉ ተጨማሪ ምርመራዎች ጋር በማቀናጀት የምርመራውን ትክክለኛነት ከፍ ያደርገዋል፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 2.9 stars
    2.9 / 5 (30 )
  • Your Rating



Related Posts