የጤና መረጃዎች

በ3 ዳይሜንሽናል ዲጂታል ሞግራም (3D Digital Mammogram) እና በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረግ ባዮፕሲ አማካኝነት የሚደረግ የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast cancer screening)

Share:

ታይላንድ ለብዙ ተከታታይ ዓመታት በሴቶች የጡት ካንሰር (Breast cancer) ሞት መጠን የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ ቀጥላለች፡፡ በማሞግራም (Mammogram) ማሽን የሚደረግ የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast cancer screening) ከጡት አልትራሳውንድ ምርመራ ጋር በጋራ በመሆን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስሎችን ስለሚሰጥ የጡት ካንሰር ቀድሞ ለማዎቅ ይረዳል። የበሽተኛውን ሙሉ በሙሉ የመዳን እድሉን ይጨምራል፡፡በቬጅታኒ ሆስፒታል ዘመናዊ የጡት ምስል ምርመራ እና ኢንተርቬንሽን ባለሙያ የሆኑት Dr. Pornporm Thungkatikajonkit, እንደሚሉት የጡት ካንሰርን ለመመርመር መደበኛ ዘዴዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

  1. ጡትን በራስን መመርመር (Breast self-exam); የወር አበባዎ ከተከሰተ ከ5-10 ቀናት በኋላ በወር አንድ ጊዜ በእጃችን እየተጫንን መመርመር፡፡
  2. የጡት ካንሰር ምርመራ (Breast cancer screening); እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ ለ1ሆኑ ሴቶች በዓመት አንድ ጊዜ የማሞግራፊ እና የአልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ፡፡

ማሞግራፊ በእጃችን በመነካካት ወይም በአልትራሳውንድ መለየት የማንችላቸውን በጡት ውስጥ የሚገኙ መጠናቸው በሚሊሜትር ደረጃ ትንሽ የሆኑ ጤናማ ያልሆኑ የካልሲየም ጥርቅም (calcifications) ጭምር እንድናይ ያግዛል። ስለሆነም ማሞግራም(Mammogram) ገና በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለ የጡት ካንሰርን ለመለየት ጠቀሜታው ከፍ ያለ ሲሆን የሞት መጠንን እስከ 30% ይቀንሳል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጠርዝ በሚቆርጡ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የዲጂታል ማሞግራም (Mammogram) ማሽን እያንዳንዱን የራጅ ምስል ለማንሳት 3.7 ሴኮንድ ብቻ የሚወስድ የ3 ዳይሜንሽናል ዲጂታል የጡት ራጅ ምስል (3D Digital Breast Tomosynthesis) ሆኖ የተሠራ ነው፡፡ የ3 ዳይሜንሽናል ዲጂታል ማሞግራም ማሽን በተለይ ትልቅ ጡት ላላቸው ሴቶች በስብ እና በስጋ ተሸፍኖ ተደራርቦ በጡት ውስጥ የሚገኝ እባጭን ነጣጥሎ ለየብቻ ለማየት ያስችላል; ይህም ጤናማ ያልሆኑ እባጮች ወይም የካልሲየም ስብስቦች ካሉ ጥርት አድርገን ማየት እንድንችል ያግዘናል፡፡ በዚህ ምክንያት ከ2 ዳይሜንሽናል ማሞግራም (Mammogram) ማሽን ጋር ሲነፃፀር የጡት ካንሰርን በተሻለ ለመለየት ያስችላል፡፡

አልትራሳውንድ በጡት ውስጥ የሚገኙ እባጮች ወይም ፈሳሽ የቋጠሩ ችግሮችን በግልፅ ያሳያል፡፡ እባጮች ከተገኙ መደበኛ እጢ መሆናቸውን ወይም ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ መሆናቸውን ለመለየት መጠኖቻቸውን እና ዲያሜትራቸውን ያሳየናል፡፡ ይህ ለጡት ካንሰር የምናደርገውን ምርመራ አረጋጋጭ እና ትክክለኛ እንዲሆን ያስችለዋል።

በጡቶች ውስጥ ማንኛውም ያልተለመደ ሁኔታ ከተገኘ ለፈጣን ምርመራ ባዮፕሲ ይወሰዳል፣ በሂደቱ ወቅት በደም ስር የሚሰጥ የሰመመን መርፌ ሳያስፈልግ ቦታው ላይ ብቻ ማደንዘዣ መርፌ በመውጋት ይከናወናል፡፡ ሂደቱ በመርፌው መጠን የሚሆን ትንሽ ጠባሳ ብቻ ስለሚያስቀር መተኛት ሳያስፈልግ በተመላላሽ ህክምና ሂደት መከናወን ይችላል። ኮር ኒድል ባዮፕሲ ሊከናወን የሚችልባቸው ሁለት መንገዶች አሉ፦

  • በአልትራሳውንድየታገዘኮርኒድልባዮፕሲ (Ultrasound-guided core needle biopsy) ማለት በጡት ውስጥ ወዳለው እብጠት በቆዳ ውስጥ መርፌ ማስገባት የሚከናዎን ማለት ነው፡፡ ሐኪሙ በአልትራሳውንድ ማሳያ ስክሪኑ ላይ መርፌውን እና እብጠቱ በግልጽ ማየት ይችላል ይህም የእጢውን ትክክለኛ ቦታ ለማዎቅ ይረዳል፡፡
  • ቦታውን ለማዎቅ በኮርዲኔት ቴክኖሎጂ የሚመራና በቫኪውም የሚታገዝ ኮር ኒድል ባዮፕሲ (Stereotactic-guided vacuum-assisted core needle biopsy) በጡት ውስጥ በማሞግራም(Mammogram) ምርመራ ወቅት ያልተለመዱ ነገሮች ሲታዩ ለምሳሌ እንደ ትናንሽ የካልሲየም ስብስቦች ሲኖሩ የታየው ነገር ላይ መርፌ በማስገባት ህብረ ህዋስ ናሙና ለማውጣት የሚደረግ ሂደት ነው፡፡ ባለ 3ዳይሜንሽናል ኮምፒተርን መጠቀሙ ችግሩ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ እንድናውቅ ያግዛል እንዲሁም በቫኪውም የታገዘው መሳሪያ አንዴ ባስገባነው መርፌ ብዙ የሕብረ ሕዋሳት ናሙናዎችን ለመሰብሰብ ያግዛል፡፡

በቶሎ የተደረሰበት የጡት ካንሰር በቶሎ ህክምና ለመጀመር ያስችላል፡፡ በቬጅታኒ ሆስፒታል የጡት ምርመራ ሪፖርቶች ምርመራውን ባደረግንበት ተመሳሳይ ቀን ውስጥ ይደርሳሉ፡፡ ለታካሚዎች ምቾት ሲባል ፈጣን የባዮፕሲ ምርመራ ያለ ሲሆን ይህም የምርመራ ውጤቶችን በመጠባበቅ የሚፈጠርን ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳል፡፡

የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ የሚከሰት በጣም የተለመደ የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ እንደሌሎች የካንሰር ዓይነቶች ምንም ዓይነት የመከላከያ ዘዴዎች የሉትም፡፡ በቬጂታኒ ሆስፒታል ዘመናዊ የጡት ምስል ምርመራ እና ኢንተርቬንሽኒስት ስፔሻሊስት የሆኑት Dr. Pornporm Thungkatikajonkit እንደተናገሩት የተሻለው የመከላከያ መንገድ መደበኛና ጊዜውን የጠበቀ ምርመራ ማድረግ ነው፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (1 )
  • Your Rating




Related Posts