የጤና መረጃዎች

እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ምልክቶችን ከመታየታቸው በፊት የኮሎኖስኮፒ (Colonoscopy) ምርመራ የሚያደርጉባቸው 3 ምክንያቶች

Share:

የኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) በታይላንድ ዜጎች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የተለመደ የካንሰር ዓይነት ነው። ለካንሰር ምርመራ የሚደረግ የኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) ምርመራን የማያደርጉ አብዛኞች ሕመምተኞች ላይ ብዙውን ጊዜ በሽታው ከባድ ደረጃ ላይ ደርሶ ይገኛል። በዋናነት ምርመራው አሳማኝ ሆኖ ስለማይታያቸው፣ ወይም ምርመራውን ማድረግ የሚወስኑት ያልተለመደ የሆድ ህመም መታየት ሲጀምር ወይም በሚፀዳዱበት ወቅት ደም ከታየ በኋላ ብቻ መሆኑ። ለኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) የሚደረግ የኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) ምርመራ በሚከተሉት 3 ምክንያቶች እድሜያቸው 40 እና ከዚያ በላይ ሲሆኑ መደረግ አለበት።

  1. የኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ በሰፊው ይከሰታል። ስለዚህ በየ5 ዓመቱ በኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) አማካኝነት የኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) ምርመራን ማድረግ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) ተይዞ የሚያውቅ የቅርብ ዘመድ ካለዎት ከ40 ዓመት ጀምሮ የኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) ምርመራ ማድረግ እና ምርመራውን በየ3-5 ዓመቱ በየጊዜው መድገም አለብዎት።
  2. ደም የቀላቀለ ሰገራ፣ ተቅማጥ ከደም ጋር፣ የሆድ ድርቀት፣ ሁል ጊዜ ሰገራ ሲወጣ ማስማጥ ፣ወይም ሰገራ ትንሽ መሆን እና መሰል ያልተለመዱ ምልክት እስኪታዩ ድረስ ከጠበቁ እርስዎ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆንዎትን ያሳያል። ብዙ ጊዜ ​​እነዚህ ምልክቶች ያሏቸው ህመምተኞች ቀድሞውኑ ከባድ የኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) ደረጃ ላይ ያሉ እና ለሞት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
  3. ኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) ለኮሎሬክታል ካንሰር (Colorectal cancer) ጥሩ የምርመራ ዘዴ ነው። ምክንያቱም የኮሎሬክታል ካንሰርን (Colorectal cancer) ሊያስከትል የሚችል ፖሊፕ (እባጭ) ከተገኘ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ መታከም ስለሚችል ሙሉ በሙሉ የመዳን እድሉ ከፍተኛ ነው።

ኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) የኮሎሬክታል ካንሰርን (Colorectal cancer) ለመመርመር ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ሌሎች ከአንጀት ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለመመርመርም ሊያገለግል ይችላል። በተጨማሪም እንደ ሐኪምዎ ውሳኔ የጨጓራና የአንጀት ኢንዶስኮፒ (endoscopy) በየጊዜው እንዲደርጉ እና ትክክለኛ የምርመራ ውጤት እና ፈጣን ሕክምና ለማግኘት በኢንዶስኮፒክ ቴክኖሎጂ ስፔሻሊስት በሆነ ባለሙያ ምርመራውን እንዲያደርጉ ይመከራል።

  • Readers Rating
  • Rated 3 stars
    3 / 5 (2 )
  • Your Rating