የጤና መረጃዎች

ላፓራኮስኮፒ ኮሌክቶሚ (ካንሰራማውን ክፍል ቆርጦ የማስወገድ ህክምና) ለትልቁ አንጀትና ሽለላአንጀት
(ኮሎሬክታል) ካንሰር ህክምና አማራጭ ነው – Colorectal Cancer Treatment

Share:

የትልቁ አንጀትና ሽለላአንጀት (ኮሎሬክታል) ካንሰር (Colorectal cancer) በሴቶችም ሆነ በወንዶች ላይ የሚከሰት በጣም የተለመደ የካንሰር አይነት ነው፡፡ የትልቁ አንጀት ካንሰር ያለባቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በመጀመርያ ደረጃ ላይ እያለ ምልክቶችም ሆነ የህመም ስሜት ስለማያሳይ በሽታውን ልንነቃበት ይገባል፡፡ ስለሆነም በትልቁ አንጀት ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች የኮሎኖስኮፒ (በፊንጢጣ በኩል የሚገባ ካሜራ) ምርመራ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ቀድሞ ካንሰሩ በአንጀት ውስጥ መኖሩ ከታወቀ ለታካሚዎች ላፓራስኮፒክ ኮሌክቶሚን ጨምሮ ብዙ የሕክምና አማራጮች አሉ ይህ የህክምና አማራጭ በፍጥነት የማገገም እድላችን ይጨምራል፡፡

በቬጅታኒ ሆስፒታል የኮሎሬክታል የቀዶ ጥገና ሀኪም የሆኑት(Colorectal Surgeon) Dr. Narain Santikulanont እንደገለፁት የትልቁ አንጀትና ሽለላአንጀት ካንሰር የሚከሰተው በአንጀት ውስጥ ባሉ ህዋሳት ያልተለመደ እድገት ምክንያት ነው፡፡ ከ90% በላይ የሚሆኑት የአንጀት ካንሰር በሽተኞች ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ ነው፡፡ የትልቁ አንጀትና የሽለላአንጀት ካንሰር በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ምልክቶችን አያሳይም፡፡ ነገር ግን በኮሎኖስኮፒ (በፊንጢጣ በኩል በሚገባ ካሜራ) አማካኝነት መለየት ይቻላል። ጤናማ ያልሆነው ህዋስ የዘረመል ለውጥ ከማድረጉና የካንሰር ህዋስ ከመፍጠሩ በፊት ፖሊፕ የሚባሉ ቀስ በቀስ ወደ ትልቁ አንጀት እና ሽለላአንጀት ካንሰርነት የሚቀየሩ በብዛት በትልቁ አንጀት ውስጥ የሚገኙ እባጮች ይገኛሉ

የትልቁ አንጀት እና የሽለላአንጀት ካንሰር ህክምናው ውጤታማነት ግምት እንደ በሽታው ደረጃ የሚለያይ ሲሆን እንደሚከተለው ተቀምጧል – The estimated success rate of treating colorectal cancer

  • ደረጃ 1 (Stage 1 Colorectal cancer): ይህ የካንሰሩ የመጀመሪያው ደረጃ ነው። በአቅራቢያው ወደሚገኙ ሕብረ ሕዋሳት አድጎ አልተስፋፋም፡፡ ይህ ደረጃ በቀዶ ጥገና ሊታከም የሚችል ስለሆነ ውጤታማነቱ በአንፃራዊነት ከፍተኛ ነው፡፡
  • ደረጃ 2 (Stage 2 Colorectal cancer): የካንሰር ሕዋሱ በአንጀት ግድግዳው ላይ በጥልቀት ወደሚገኙ የጡንቻዎች ሽፋን ውስጥ አድጎ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ሕብረ ሕዋሳት እና ወደ ሌሎች አካላት ሊዛመት ይችላል፡፡
  • ደረጃ 3 (Stage 3 Colorectal cancer)- የካንሰር ሕዋሱ ወደ ሊምፍ ኖዶች (ንፍፊት) መሰራጨት የጀመረ ሲሆን በቀዶ ጥገና መወገድ ያለበትና የካንሰሩን ከንደገና መመለስ ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ሲባል በሽተኛው ኬሞቴራፒ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  • ደረጃ 4 (Stage 4 Colorectal cancer): ይህ የበሽታው ከባድ ደረጃ የሚባለው ነው፡፡ ካንሰሩ በደም እና በሊንፍ ኖዶች አማካኝነት ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ተሰራጭቷል፡፡ ሕክምናው በካንሰር የተጎዱትን የአካል ክፍሎች በቀዶ ጥገና ማስወገድና ኬሞቴራፒን በማቀናጀት ይከናወናል፡፡

የትልቁ አንጀት እና የሽለላአንጀት ካንሰርን ለማከም ዶክተሮች የቀዶ ጥገና ሕክምናን ፣ የጨረር ሕክምናን ፣ ኬሞቴራፒን እና የታርጌትድ ቴራፒን ጨምሮ የተለያዩ የሕክምና ዘዴዎችን በጥምረት ይጠቀማሉ። ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር የሚወሰነው ታካሚው የተሻለ ጥሩ ሕይወት እንዲያገኝ ተገቢውን ህክምና በሚያቅደው የህክምና ቡድን አማካኝነት ነው።

ለትልቁ አንጀት እና ለሽለላአንጀት ካንሰር ዋነኛው የሕክምና አማራጭ የቀዶ ጥገና ሕክምና ነው፡፡ ባህላዊው የቀዶ ጥገና ሕክምና ብዙውን ጊዜ እንደ ካንሰር እጢው መጠን እና ቦታ በግምት ከ15 – 30 ሳ.ሜ ርዝመት የሚሆን ሰውነታችን ተቀዶ የሚከናወን ህክምና ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እገዛ፣ የላፓራኮስኮፒ ኮሌክቶሚ የትልቁ አንጀት እና የሽለላአንጀት ካንሰርን ለማከም የሚያገለግል የታወቀ የቀዶ ጥገና ዘዴ ሆኗል፡፡ ላፓራኮስኮፕ ኮሌክቶሚ ብዙም ሰውነት መቅደድ ሳያስፈልገው (minimal invasive) የሚከናወን የህክምና ሂደት ነው፡፡ ካንሰራማውን የአንጀት እና የሊምፍ ኖድ (ንፊፊት) ክፍል ለማስወገድ ትንሽ ከፍተኛ ጥራት ያለው ካሜራ ወደ ሆድ ይገባል፡፡ የላፓራስኮፒክ ኮሌክቶሚ ህክምና ጥቅሞች በዋናነት አነስተኛ የሰውነት መቀደድ፣ ዝቅተኛ ህመም፣ በቶሎ ማገገም እንዲሁም በሽተኞች ወደ መደበኛ እና ጤናማ ህይወታቸው እንዲመለሱ ያስችላቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የላፓራስኮፒ ኮሌክቶሚ ህክምና ውጤት እንደ ክፍት ኮሌክቶሚ ጥሩ ላይሆን ይችላል። ታካሚዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረገው የቀዶ ጥገና ዘዴ መሰረት የሚያደርገው በዶክተሮቹ ምርመራ እና በታካሚው ላይ በጣም ጥሩ እና ውጤታማ ህክምና ዘዴ የትኛው እንደሚሆን በሚወሰነው ውሳኔ መሠረት ነው ፡፡ቀጠሮ ማስያዝ እባክዎ የኮሎሬክታል ቀዶ ጥገና ክሊኒክን ያነጋግሩ። ስልክ ቁጥር: +66(0)2-734-0000 ext. 4500 or 4501.

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (1 )
  • Your Rating




Related Posts