የጤና መረጃዎች

የሪዩማቲክ (Rheumatic) የልብ በሽታን ለማዳን የሚወሰዱ የሕክምና ዘዴዎች

Share:

የስትሬፕ (strep) ኢንፌክሽንን ተከትሎ በሽተኛው የሪዩማቲክ ትኩሳት ሲኖረው ሁል ጊዜ የሚያሳስብው ነገር ቢኖር የሪዩማቲክ የልብ በሽታ ነው። የልብ ሚትራል ቫልቮች እንዲጠቡ ወይም ልቀት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ከባድ በሽታ ነው። ችግሩ በጣም ከባድ በሚሆንበት ወቅት ማለትም ቫልቮቹ በትክክል ተግባራቸውን ለማከናዎን በማይችሉበት መልኩ ሲጎዱ ለሪዩማቲክ የልብ በሽታ የሚደረግ የቀዶ ጥገና ሕክምና አስፈላጊ ነው። የሪዩማቲክ የልብ በሽታ ሕክምናን ለማስቀረት ሁል ጊዜም የተሻለው መንገድ ችግሩን ቀድሞ መከላከል ነው። እርስዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል በስትሬፕ (strep) ኢንፌክሽን በሚያዙበት ወቅት ወደ ሪዩማቲክ ትኩሳት እያደገ እንዳይሄድ ሐኪምዎ አንቲባዮቲኮችን በቶሎ ማዘዝ አለበት።

የሪዩማቲክ የልብ በሽታ ምልክቶች

የሪዩማቲክ ትኩሳት ከአሁን በፊት አጋጥሟቸው የሚያውቁ ሰዎች በየጊዜው የልባቸውን ጤንነት በጥንቃቄ መከታተል አለባቸው። ይህ ማለት በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ አመታዊ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል ማለት ነው። በተጨማሪም የሪዩማቲክ ትኩሳት ካለብዎት ለሐኪምዎ ማሳወቅ አለብዎት። ከአሁን በፊት የሪዩማቲክ ህመምተኛ ከነበሩና ተደጋጋሚ የትንፋሽ ማጠር፣ አዲስ የደረት ህመም፣ ደረት ላይ ምቾት አለመሰማት ወይም እብጠት ካጋጠማቸው ወዲያውኑ ወደሕክምና መሄድ ያስፈልጋል።

የሪዩማቲክ የልብ በሽታ ምርመራ እና ሕክምና

የሪዩማቲክ ትኩሳት ያጋጠማቸው እና ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች የሚያሳዩ ሕመምተኞች ሐኪም የችግሩን ምንነት ይህ ነው ከማለቱ በፊት የኤኮካርዲዮግራም፣ የኤሌክትሮካርዲዮግራም፣ የደረት ራጅ፣ የልብ ኤምአርአይ ወይም የተወሰኑ የደም ምርመራዎች ማድረግ ያስፈልጋል።

ለሪዩማቲክ የልብ በሽታ የሚሰጠው ሕክምና በልብ ላይ በደረሰው ጉዳት መጠን ላይ የተመሠረተ ነው። ጉዳቱ በወቅቱ ለሕይወት አስጊ ካልሆነ የልብ ሐኪምዎ የልብ ምት መዛባት እና የልብ ድካም ምልክቶች ለማከም የሚያስችሉ መድሃኒቶችን ሊያዝልዎት ይችላል። የደም መርጋትን ለመከላከል የደም ማቅጠኛ መድኃኒቶችም ሊታዘዙ ይችላሉ።

ዶክተሩ የልብ ቫልቮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ካገኘ የተበላሹትን ቫልቮች መጠገን ወይም መተካትን ሊመርጥ ይችላል።

በልብ ቫልቭ ጥገና ሂደት ወቅት የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሙ እንደ ቫልቭ ፓቶሎጂው እና እንደ ጉዳቱ መጠን ጥንቃቄ የተሞላበት የቫልቭ ምርመራና እናግምገማዎችንካደረገበኋላ ውጤቶች ላይ ተመርኩዞ ብዙ ዓይነት ጥገናዎችን ሊያደርግ ይችላል። የመጨረሻው የቀዶ ጥገናው ሂደት በቀዶ ጥገና ሀኪሙ ውሳኔ እና ልምድ ላይ የተመሠረተ ነው።

የልብ ቫልቭ ጉዳቱ ከባድ ሲሆንና ቫልቩን ሙሉ በሙሉ መተካት አማራጭ የሌለው መንገድ ሲሆን የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ሁለት ምርጫዎች አሉት እነሱም ከእንስሳት ሕብረ ሕዋስ (ከላም ወይም አሳማ) የሚሰራ ባዮሎጂካል ቫልቭ (bioprosthetic ቫልቭ ይባላል) ወይም ሜካኒካል ቫልቭ ናቸው። በታካሚው ዕድሜ እንዲሁም ሌሎች አመላካቾችን ጨምሮ የታካሚው አካላዊ ሁኔታ ላይ በመመስረት ውሳኔው ይወሰናል። ባዮፕሮስተቲክ (Bioprosthetic) ቫልቮች በጊዜ ሂደት ሊበላሹ ይችላሉ እንዲሁም ሜካኒካል ቫልቮችን ያስገጠሙ በሽተኞች ደግሞ ቀሪ ሕይወታቸውን የደም ማቅጠኛ መድኃኒቶችን መውሰድ ይኖርባቸዋል።

በቬጅታኒ ሆስፒታል ከልብ ሐኪም ጋር ቀጠሮ ይያዙ

ቀደም ሲል የሪዩማቲክ ትኩሳት ከነበረብዎት እና የሪዩማቲክ የልብ በሽታ ይይዘኝ ይሆን ብለው የሚጨነቁ ከሆነ የቬጅታን ሆስፒታልን ያነጋግሩ በሆስፒታላችን ካሉ የልብ ሐኪሞቻችን ከአንዱ ጋር ቀጠሮ ይያዙ። አስፈላጊውን ምርመራ ሁሉ በማድረግ ያለብዎትን ችግር ያገኙልዎታል። እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እርስዎ ላሉበት ሁኔታ ተስማሚ የሆነውን ህክምና ያደርጉልዎታል።

  • Readers Rating
  • Rated 4.3 stars
    4.3 / 5 (3 )
  • Your Rating