የጤና መረጃዎች

በጉልበት መገጣጠሚያዎች ላይ ያለ ፈሳሽ(Knee Joint Effusion) ምልክቶችን በቀላሉ ማወቅ እንችላለን

Share:

በጉልበት መገጣጠሚያዎች ላይ ያለ ፈሳሽ  (Knee joint effusion) ወይም ውሃ መጠራቀም በጉልበት መገጣጠሚያዎች ውስጥ የሚገኘው የሲኖቪያል ፈሳሽ (synovial fluid) ላይ ችግር መኖሩን የሚያሳይ ነው። ይህ አይነቱ ችግር በጉልበት መቆጣት ወይም ሌሎች ጉዳቶች ምክንያት የሚከሰት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ የጉልበትን መገጣጠሚያዎች በቀጥታ የሚጎዳ ችግር ሲከሰት፣ መገጣጠሚያዎች ላይ መቆጣት ወይም ብግነት በሚያስከትሉ በሽታዎች ሲከሰቱ፣ ወይም እያረጀ ወይም እየተጎዳ ያለ የሰውነት አካል ሲኖርና ያንን ተከትሎ መገጣጠሚያዎች ላይ ባሉ ካፕሱሎች መካከል የሚገኙ አያያዥ ሕብረ ሕዋሳትን ከልክ በላይ የሆነ የሲኖቪያል ፈሳሽ (synovial fluid) እንዲያመርቱ ሲያደርጋቸውና በጊዜ ሂደትም የጉልበት መገጣጠሚያዎች ላይ የፈሳሽ መጠራቀም ችግር ሲያስከትል ነው። እያንዳንዱ ህመምተኛ የየራሱ ልዩ የሆኑ ምልክቶች ይኖሩታል።

  • ህመም መኖር እና የሚታይ የጉልበት ክዳን እብጠት
  • እግራችን ሲታጠፍ ወይም ሲዘረጋ ጉልበት ላይ መጠነኛ እብጠት እና ህመም መኖር
  • በጉልበት ክዳን ወይም አከባቢው ላይ መቅላት
  • ከጉልበት ክዳን ጀርባ ላይ ዕጢ የመሰለ እብጠት ወይም ፈሳሽ የቋጠረ አይነት ስሜት ሊሰማ ይችላል

በጉልበት መገጣጠሚያዎች ላይ ያለ ፈሳሽ  (Knee joint effusion) ሕክምናው የግድ ቀዶ ጥገና ወይም አርትሮሴንተሲስ መሆን ላይጠበቅበት ይችላል፥ ማለትም የተጠራቀመውን ፈሳሽ ለማፍሰስ የጉልበት መገጣጠሚያን መቅደድ ላያስፈልግ ይችላል። ይልቁንም ህክምናው የበሽታውን መንስኤ በማከም ላይ ያተኮረ ይሆናል። በጉልበት መገጣጠሚያዎች ላይ ያለ ፈሳሽ  (Knee joint effusion) ምልክቶች ጋር የሚመሳሰሉ ያልተለመዱ ምልክቶች ካስተዋሉ ትክክለኛውን የችግሩን መንስኤ ለማወቅ እና ተገቢውን ህክምና ለማድረግ በአስቸኳይ የህክምና ባለሙያ ማማከር ይኖርብዎታል።

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (2 )
  • Your Rating