የጤና መረጃዎች

የጉልበት አንጓ ብግነት (Knee osteoarthritis) ችግርዎን በእነዚህ 3 የሕክምና አማራጮች ያስተካክሉ

Share:

ሶስት አይነት የጉልበት አንጓ ብግነትን (Knee osteoarthritis) የምናክምባቸው መንገዶ  አሉ። ይሁን እንጂ ለያንዳንዱ ታካሚ እንደህመሙ ክብደት የትኛው ህክምና የተሻለ ያስፈልገዋል የሚለውን የሚወስነው ዶክተሩ ነው።

  • ያለመድሃኒት የሚደረግ ህክምና (Non-Medical Treatment): ለአብዛኛዎች ቀላል ለሆኑ ችግሮች ያለመድሃኒት የሚደረጉ ህክምናዎች በቂ ናቸው። እነሱም ለጉልበት ብግነት መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችን መቀነስ; የሰውነት ክብደትን በመቀነስ፣ በተደጋጋሚ የጉልበት ማሳሳቢያዎችን ከሌሎች ቀዶ ጥገና ካልሆኑ ህክምናወችን ማለትም የጨረር (laser) ህክምና ወይም ህመም ማስታገሻ ደረቅ መርፌ(acupuncture) እያፈራረቁ መውሰድ መፍትሄ ማግኘት ይቻላል።
  • የመድሃኒት ህክምናዎች (Medical Treatment): ከፍ ያለ የህመም ስሜት ላላቸው ህመምተኞች ዶክተሩ የሚዋጡ ወይም የሚቀቡ መድሃኒቶች ለምሳሌ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችና ክሬሞች ሊያዝ ይችላል።
  • የቀዶ ጥገና ህክምና (Surgical Treatment): የጉልበት አርተሮስኮፒ (Knee Arthroscopy) ማለት በጉልበት መገጣጠሚያወች መካከል የሚገኘውን ሲኖቫል ፈሳሽ (synovial fluid) ለማፅዳት፣ የተጎዳ አጥንት፣ ለስላሳ ተጣጣፍ አጥንቶች(cartilage) እና የአጥንት ቲሹዎችን ለማፅዳት፣ እንዲሁም ጤናማ ያልሆነውን የመገጣጠሚያ ካርቲሌጅ አጥንት አስወግዶ በአርቴፊሻል መሸፈን (resurface) እና አዲስ የካርቲሌጅ ህዋሳት እንዲነቃቁ ማድረግ (stimulate) እና ሌሎች ህክምናዎችን ለማከናወን ያገለግላል። ሌላኛው ለጉልበት አንጓ ብግነትን (knee osteoarthritis) የሚደረግ ህክምና የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ቀዶ ጥገና ህክምና ሲሆን ይህ ህክምና የሚመከረው በጣም ከባድ የጉልበት አንጓ ብግነትን (knee osteoarthritis) ችግር ላለባቸው በሽተኞች ነው። በዚህ የህክምና ሂደት የተጎዳው የጉልበት አጥንት ተፍቆ ይነሳና (resurface) በአርቴፊሻል ይተካል። ለጠቅላላ የጉልበት አንጓ ብግነት ህክምና (Total Knee Replacement – TKA) አዳዲስ በመጡ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት ማለትም በኮምፒውተር የታገዘ ቀዶ ጥገና እና በሮቦት በታገዘ ቀዶ ጥገናዎች በመታገዝ ሃኪሙ ውጤታማና የተሻለ ህክምና ለታካሚው እንዲያደርግ ያግዘዋል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚደረገው ህክምና በተለምዶ ከሚደረገው ቀዶ ጥገና ጋር ሲነፃፀር በሽተኛው በቶሎ የሚያገግምና ከህክምና በኋላ የሚፈጠሩ ችግሮችም (complications) ይቀንሳሉ።
  • Readers Rating
  • Rated 4 stars
    4 / 5 (2 )
  • Your Rating