የጤና መረጃዎች

የቬጅታኒ ሆስፒታል ዘመናዊ የሪሃብሊቴሽን ማዕከል – Vejthani Hospital’s Advanced Rehabilitation Center

Share:

ሙሉ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ሰውነት ለጤናማ ሕይወት መኖር ቁልፍ ነገር ነው። ያሰብናቸውን ነገሮች ለመፈፀም ያስችለናል እንዲሁም ቤተሰባችን እና የምንወዳቸውን ሰዎች ድጋፍ ማድረግ እንድንችል ያግዘናል፡፡ የሰውነት እንቅስቃሴ መዛባት የምንላቸው ለምሳሌ የጡንቻ ድክመት ወይም በአግባቡ መራመድ አለመቻልን ሲሆኑ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እና በአእምሮ ጤንነታችን ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡

የሰውነት እንቅስቃሴ መታወክን የሚያስከትሉ ዋነኛ ምክንያቶችን በ2 ከፍለን ማየት እንችላሉ፦፦

 • እርጅና፦ የማርጀት በሽታዎች የሰውነት እንቅስቃሴን መገደብ ወይም የሰውነት ሚዛን መዛባትን ያስከትላሉ፡፡ ለምሳሌ ለመራመድ መቸገርን አብዛኛውን ጊዜ ችላ ሲባል ይስተዋላል ምክንያቱ ደግሞ ብዙ ሰዎች ከባድ የጤና ችግር ምልክት መሆኑን ሳይረዱ ተፈጥሯዊ የእርጅና ሂደት አድርገው ስለተቀበሉት ይመስላል ለምሳሌ በአረጋውያን ላይ የመውደቅ አጋጣሚዎችን ሊያስከትሉና ያነን ተከትሎ ወደ አልጋ ቁራኛነት ሊያመራቸው ይችላል፡፡
 • በሽታ፦ የሰውነት እንቅስቃሴ መዛባትን ሊያስከትሉ ከሚችሉ በሽታዎች ውስጥ በአንድ ጎን የሚከሰት ፓራላይዝ (Hemiparesis) ይህ በስትሮክ ወይም በአንጎል ጉዳት ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው፣ ከወገብ በታች ያለው የሰውነት ክፍል ፓራላይዝ መሆን(Paraplegia) ይህ በአከርካሪ አጥንት መጎዳት ወይም የዲስካችን የውስጠኛው ዝልግልግ ክፍል በአንድ በኩል አፈንግጦ ሲወጣ ይከሰታል፣ ፓርኪንሰን የሚባለው የጭንቅላት በሽታ እና Multiple sclerosis የሚባሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ሪሃብሊቴሽን እና ፊዚካል ቴራፒ (Rehabilitation & Physical Therapy) የሰውነት እንቅስቃሴ የሚገድቡ ችግሮች ሲያጋጥሙ ሰውነትን ወደነበረበት ለመመለስ እንዲሁም እጅና እግሮቻችን ተግባራቸውን በጥሩ ሁኔታ ማከናዎን እንዲችሉ የሚያግዙ ዘዴዎች ናቸው፡፡የሪሃብሊቴሽን እና ፊዚካል ቴራፒ (Rehabilitation & Physical Therapy) ህክምና በመደበኛነት ህመምተኛው ወደ ቀደመ ህይወቱ እንዲመለስና የተሻለ ነገ እንዲኖረው ይረዳሉ፡፡

ይሁን እንጂ ባህላዊ የሪሃብሊቴሽን ዘዴ (Traditional Rehabilitation) የነርቭ ሥርዓትን እና የጡንቻዎችን ማገገም ሊያደናቅፉ የሚችሉ በርካታ ውስንነቶች አሉት፡፡ በዋናነት ከባድ የጡንቻ ድክመት ያለባቸውን ህመምተኞች የፊዚዮቴራፒ ባለሙያው በእንቅስቃሴ ጊዜ አካላዊ ድጋፍ ማድረግ እና ሙሉ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ የሰውነታቸውን ክብደት መሸከም ይኖርበታል፡፡ የጡንቻቸው ድክመት ከስልጠናው ድካም ጋር ተደምሮ በስልጠና ክፍለ-ጊዜው ወቅት ታካሚውን ለረዥም ጊዜ በተከታታይ ማሠልጠን የማይቻል ይሆናል፣ ስልጠናውን በበቂ ድግግሞሽ ባለመሰራቱ  ቅደም ተከተሉ የሚዛባና አቋሙን የሚጎዳ በመሆኑ ነርቮችን ወደነበሩበት የመመለሳቸውን ወይም neuroplasticity የሚገድብ ይሆናል፡፡ እነዚህ ድክመቶች ፕሮግራሙን ውጤታማ እንዳይሆን ያደርጉታል፡፡

ውስንነቶችን “በሮቦት-በተደገፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ሚዛንን የመጠበቅ ስልጠና” ያሸንፉ

ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች የሚከናወኑ በሮቦት የታገዙ የሪሃብሊቴሽን (Robotic-Assisted Rehabilitation) ህክምናዎች ውጤታማነታቸው ከተለመዱት የፊዚዮቴራፒ መንገዶች ጋር ሲነፃፀር እጅግ የላቀ ነው፡፡

በሮቦት የታገዘ ሪሃብሊቴሽን ጥቅሞች፡-

 • በተሻለ መልኩ የሰውነት አቋምና-አረማመድን መቆጣጠር፦ ችግሩ ላይ ያተኮረ እና በጣም ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን በመስጠት የነርቭ ሥርዓት እንዲነቃቃ በማድረግ በተሻለ መልኩ የሰውነታችን አቋም ለመጠበቅና-አረማመዳችን ለመቆጣጠር ይረዳናል፡፡
 • የተሻለ የሰውነት ሚዛን አጠባበቅ፦ ህመምተኞች የተሻለ መራመድ እና የሰውነት ሚዛናቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችላቸውን የመገጣጠሚያዎችን እንቅስቃሴን እንዲያሻሽሉ ያግዛቸዋል፡፡
 • የተሻለ ጡንቻዎች ማገገም፦ ፈጣን እና የተሻለ የመራመድ ችሎታ እንዲኖር የሚያደርጉትን የእግሮቻችን ጡንቻዎች ያጠነክራቸዋል።
 • በተሻለ ወደነበረበት የመመለስ እድል፦ በጌሞች ወይም ቪዲዮዎች የሚያዙንን በመከተል የምናከናውናቸው እውነተኛ ቨርቹዋል ልምምዶች በመስራት የብዙ የሰውነት ህዋሳትን እንዲነቃቁ በማድረግ የነርቭ ስርዓትን ወደነበረበት ለመመለስ ያግዛል፡፡
 • የተሻለ ውጤት፦ ታካሚዎች ምን ያክል ደረጃ ድረስ ሰውነታቸው ማከናዎን ይችላል የሚለውን እንዲያውቁት ይፈቅድላቸዋል ይህም ፕሮግራሙን ያለማቋረጥ እንዲያከናውኑና የተሻለ ውጤት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡

የቬጂታኒ ሆስፒታል ዘመናዊ የሪሃብሊቴሽን ማዕከል (Vejthani Hospital’s Advanced Rehabilitation Center) ሁሉን አቀፍ የሪሃብሊቴሽን አገልግሎቶችን ለማቅረብ አቅዶ በሮቦት የታገዙ የሪሃብሊቴሽን ፕሮግራሞችን ከፍተኛ ልምድና ክህሎት ባለው ቡድን አማካኝነት ማለትም physical medicine እና የሪሃብሊቴሽን ሐኪሞች፣ የፊዚዮቴራፒ ባለሙያዎችን እንዲሁም የእያንዳንዱን ታካሚ አላማ እና ፍላጎት ለማሳካት “በሰዎች እንቅስቃሴ ሪሃብሊቴሽን” ከፍተኛ ልምድን የተካኑ occupational therapists ቡድኖች ያካተተና የእርስዎን ህመም ማከም ዋነኛ አላማው አድርጎ እየሰራ ይገኛል። 

በዘመናዊ የሰዎች እንቅስቃሴ ሪሃብሊቴሽን ፕሮግራም በመታገዝ የቀጣይ ሕይወትዎን የተሻለ ያድርጉ ምክንያቱም ሕይወት እንቅስቃሴ ነው።

ቬጂታኒ የህይወትወ ዋስትና – Vejthani, Victory for life.

 • Readers Rating
 • Rated 5 stars
  5 / 5 (1 )
 • Your Rating