የጤና መረጃዎች

የዲስክ መንሸራተት (Herniated Disc) በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች ላይ ይከሰታል

Share:

ከጀርባ ተነስቶ ወደታች ወደ እግር እና ጫማ የሚወርድ ህመም አንዳንዴም እግር መደንዘዝና ሃይል ማጣት ሊኖረው ይችላል; እነዚህ ምልክቶች የተለመዱ የዲስክ መንሸራተት (Herniated Disc) ምልክቶች ናቸው። እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ወጣቶችም በዚህ በሽታ ሊጋለጡ ይችላሉ።

የጀርባ አጥንት እርስበርሳቸው ከተጣበቁ ቨርተብሬ ከሚባሉ አጥንቶ የተሰራ ነው። እያንዳንዱ ቨርተብሬዎች መካከል ክብ ራበር ዲስክ ይገኛል። ዲስኮች የጀርባ አጥንት ከፍተኛ ሃይል ሲያስተናግድ ሃይል በማመቅ (shock absorbers) በመሆን ያገለግላሉ እንዲሁም ሰውነታችን ሲንቀሳቀስ እንደፈለገ እንዲተጣጠፍ ያግዙታል። ዲስክኮች ክብ እና ለስላሳ ሲሆኑ የውጨኛው ክፍላቸው የተሰራው አኑለስ (annulus) ከሚባል ነገር ሲሆን የውስጠኛው ክፍል ደግሞ ዝልግልግ ከሆነ ኑክሌስ (nucleus) ከሚባል ነገር የተሰራ ነው።

የዲስክ መንሸራተት (Herniated Disc) በሌላ አጠራሩ የፈነዳ ዲስክ የሚፈጠረው ኑክለስ (nucleus) የሚባለው የዲስኩ የውስጠኛው  ክፍል ሸፍኖ የያዘውን አኑለስ (annulus) የሚባለውን ሽፋን ገፍቶ ወጥቶ ወደ ስፓይናል ካናል ሄዶ ስፓይናል ነርቭ ላይ ጫና ሲያሳድርና ከባድ የወገብ ህመም፣ የእግር መዛል፣ ጫማችን ነጠብጣባማ የመወጋጋትና የመደንዘዝ ስሜት ሲሰማን ነው።

የዲስክ መንሸራተት (Herniated Disc) እድሜያቸው በገፋ ሰወች ላይ በጊዜያት ሂደት ይከሰታል። ይሁን እንጂ በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችም በተለያየ ምክንያት ለችግሩ ይጋለጣሉ ለምሳሌ የጀርባ አጥንትን ሊጎዱ በሚችሉና የዲስክ ቦታ መዛባትን በሚያስከትሉ አደጋዎች ምክንያት ለዲስክ መንሸራተት ችግር ይጋለጣሉ።

የተለያየ አይነት ለዲስክ መንሸራተት የሚሰጡ ህክምናወች ያሉ ሲሆን ከፊዚዮቴራፒ እና ወገብ ላይ ከሚሰጡ መርፌዎች ማለትም ወደ እግር ወርዶ የሚሄደውን ህመም ለመቀነስ ከሚሰጡ መርፌዎች እስከ ቀዶ ጥገና። ቀዶ ገና ሌላኛው የዲስክ መንሸራተት የህክምና አማራጭ ነው; ይሁን እንጂ ህክምናው እንደ ችግሩ ክብደት ይወሰናል።

የኢንዶስኮፒክ ቀዶ ጥገና ለዲስክ መንሸራተት ችግር አብዛኛውን ጊዜ ተግባራዊ የሚደረግና ሰውነት ብዙ መቀደድ ሳይኖር (minimally invasive surgery) የሚከናወን እና በተለምዶ ከሚደረገው ቀዶ ጥገና በፍጥነት የሚያገግም እና የህመሙ ስሜቱም የሚቀንስ ነው። ከባድ የወገብ ህመም ከተነሳብዎት እና በጊዜ ሂደት የመደንዘዝ እና የእግር መዛል ችግሮችን ካስከተለና በዚያ ምክንያት የየእለት ተግባርወን ማከናወን ካልቻሉ ተገቢውን ምርመራ ለማድረግ እና አስፈላጊውን ህክምና ለማቀድ ስፔሽያሊስት ማየት እንዳለብዎት ይመከራል።

ለበለጠ መረጃ በቬጂታኒ ሆስፒታል የሚገኘውን የጀርባ አጥንት ክፍል ያነጋግሩ ወይም በስልክ ቁጥር +66(0)2-734-0000 ext. 5500.

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (1 )
  • Your Rating