የጤና መረጃዎች

የዲስክ መንሸራተት (Herniated Disc) ሕክምና ለማግኘት ቬጂታኒ ሆስፒታል ይጎብኙ

Share:

የአከርካሪ አጥንታችን ዲስኮች እንደ ትናንሽ ትራሶች በአከርካሪ አጥንቶች መካከል የሚገኘውና የአጥንቶቹን ንክኪ ለመከላከል ወይም ሃይልን ለማመቅ ያገለግላሉ፡፡ ዲስኮች ኒውክሊየስ ፐልፖሰስ (nucleus pulposus) ተብሎ ከሚጠራው ለስላሳ ውስጣዊ ቲሹ በላይ ጠንካራ ጎማ የሚመስል (rubbery covering) አኑሉስ ፋይብሮስስ (annulus fibrosus) የተባለ ሽፋን አላቸው፡፡

የዲስክ መንሸራተት (Herniated Disc) የምንለው ከእነዚህ ዲስኮች ውስጥ አንዱ የውጨኛው ሽፋን (አኑለስ) በማንጠባጠብና ፈሳሽ በማስወጣት (Annulus tearing or rupturing) ወይም በመበሳቱ ምክንያት ውስጣዊው ቲሹ ከአኑለስ ተገፍቶ ሲወጣ ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን አንድ ድንገተኛ እንቅስቃሴ ዲስክ እንዲፈነዳ ሊያደርግ ቢችልም ዕድሜያችን እየገፋን ሲሄድ ዲስኮች በጊዜ ሂደት ሊጎዱ ይችላሉ፡፡

የዲስክ መንሸራተት (Herniated Disc) እጅግ በጣም ህመም ሊኖረውና መደበኛ እንቅስቃሴያችን ሊገድበን ይችላል። የጀርባ ህመምዎ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎን የሚገድብ ሆኖ ከተሰማዎት የዲስክ መንሸራተት ችግር እንደሆነ ለማረጋገጥና ምርመራ ለማድረግ ዶክተርዎን ያማክሩ፡፡ በአከርካሪዎ ውስጥ ባሉ ነርቮች ላይ ጉዳት ደርሶ እንደሆነ ለማወቅ የነርቭ ምርመራ ሊያደርጉልዎት ይችላሉ፡፡ የነርቭዎን ምላሽ (reflexes)፣ ለትንንሽ ንክኪዎች እና ንዝረት የሚሰጡት ምላሽ እንዲሁም የጡንቻ ጥንካሬን እና የመራመድ ችሎታዎን ያረጋግጣሉ።

ከቀዶ ጥገና ውጭ ያሉ የዲስክ መንሸራተት ሕክምናዎች : Conservative Treatment for Herniated Disc

የሕመም ማስታገሻ መድሃኒት በሚታዘዙበት ጊዜ በዲስክ ላይ የሚከሰተውን ጫና ለመቀነስ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ላይ ማድረግ የሚችሏቸው ማስተካከያዎች አሉ፡፡ እነዚህ ማሻሻያዎች በቀናት ወይም በሳምንታት ውስጥ ቀለል ያለ የዲስክ መንሸራተት ህመምን ማስታገስ ይችላሉ፡፡

የተወሰኑ ዓይነት እንቅስቃሴዎችን እንዲያስወገዱ እንዲሁም በጣም ከባድ የሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን እንዲቀንሱ ማድረግ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ቀላል ያለ ፊዚካል ቴራፒን ያካትታሉ። ፊዚካል ቴራፒስቶች ህመሙን ሊያስታግሱልን የሚችሉ የሰውነት አቋሞችን እንዲሁም የጀርባ ጡንቻዎችን ለመገንባት እና ከአከርካሪው ላይ አንዳንድ ውጥረቶችን ለመቀነስ የሚረዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ሊያሳዩዎት ይችላሉ፡፡

መድሃኒቶች : Medication Treatment for Herniated Disc

መለስተኛ የዲስክ መንሸራተት ችግር ሲኖር ህመም በሚያጋጥምበት ወቅት እንደ acetaminophen እና ibuprofen ያሉ በብዛት የሚታዘዙ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች ይታዘዛሉ በተጨማሪ የተወሰኑ የሰውነት እንቅስቃሴዎች እንድንርቅ የሚሰጡ ምክሮች ያካትታል።

በጣም ከባድ እና ህመም ያለው በሚሆበት ጊዜ ኮርቲሶን (cortisone) መርፌዎች ህመምን የሚያስከትሉ የነርቭ ሥር ብግነትን ለመቀነስ ይረዳሉ:: እነዚህ መርፌዎች ሲሰጡ የመርፌውን አቅጣጫ ለመምራት የአከርካሪ ምስሎችን (spinal imaging) በመታገዝ ይከናወናሉ፡፡ ዲስኩ ባፈነገጠበት አካባቢ የጡንቻ መሸማቀቅ ላጋጠማቸው ታካሚዎች ሀኪሙ የጡንቻ ማፍታቻዎችን ሊያዝዝ ይችላል፡፡ በጣም ከባድ ለሆኑ ጉዳዮች ላይ ኦፒዮይድ (opioids) ይታዘዛል ነገር ግን ሰውነታችን ሊለምደው ስለሚችል የሚሰጠው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

የቀዶ ጥገና ሕክምና አማራጮች : Surgical Treatment for Herniated Disc

በጣም በከፋ እና በጣም የተዳከመ ሁኔታ ሲያጋጥም ቀዶ ጥገና ዋነኛ አማራጭ ይሆናል፡፡ ዲስኩ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ምንም ዓይነት የመሻሻል ምልክት ካላሳየ ወይም የመደንዘዝ ወይም የሰውነት መዛል ካሳየ፣ የመቆም ወይም የመራመድ ችግር ካለብዎት ወይም ሰገራ እና ሽንት መቆጣጠር ካጋጠመው ሐኪምዎ ቀዶ ጥገና እንዲያደርጉ ሊመክረዎ ይችላል፡፡

የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ብዙውን ጊዜ አፈንግጦ የወጣውን የዲስኩን ትንሽ ክፍል ማስወገድ ከዚያም ከቀዶ ጥገና ውጭ ያሉ ሕክምናዎችን መቀጠል ይመርጣሉ። በጣም ትንሽ ቁጥር ያላቸው ኬዞች ላይ ግን የተጎዳውን ዲስክ ሙሉ በሙሉ በማስወገድ ከዛም ሁለቱን አከርካሪዎች በአጥንት ግራፍት ማጣበቅ (ሁለቱን ባንድ ላይ ማያያዝ) ይኖርባቸዋል፡፡

የቀዶ ጥገና ሕክምና ሁልጊዜም የመጨረሻ አማራጭ ነው፡፡ የአከርካሪ አጥንቶችን የማገናኘት (የማጣበቅ) ሂደት ወራትን ይወስዳል፡፡ የመዋሃድ ሂደት በሚከናወንበት ጊዜ የብረት ድጋፍ በመላ አከርካሪው በኩል እንዲደረግ ይሆናል፡፡ ሐኪሙ የአጥንቶች ውህደት ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሆነ እና የሰውነት ክብደትን በአግባቡ መሸከም የሚችልበት ደረጃ ላይ መሆኑን ካረጋገጠ የብረት ድጋፉ ይወገዳል፡፡

ቬጅታኒ ሆስፒታል እፎይታን ይሰጣል : Vejthani Hospital provides Relief

ቬጅታኒ ሆስፒታል ማንኛውንም አይነት ከቀዶ ጥገና ውጭም ይሁን ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው የዲስክ መንሸራተት ሕክምናዎችን ውጤታማ በሆነ ረገድ በማቅረብ ልምድ ያካበቱ ዶክተሮችና የቀዶ ጥገና ሐኪሞች አሉት፡፡ የጀርባ ህመም የሚሰማዎት ከሆነ ወደ ቬጂታኒ ሆስፒታል በመደወል ከአጥንት ሐኪም ጋር ቀጠሮ ይያዙ፡

  • Readers Rating
  • Rated 2.7 stars
    2.7 / 5 (7 )
  • Your Rating



Related Posts