የልብ በፍጥነት መምታት (Heart palpitations) ችግር ወደ ልብ ክፍክድ (ቫልቭ) ጥገና ሊያመራ ይችላል - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

የልብ በፍጥነት መምታት (Heart palpitations) ችግር ወደ ልብ ክፍክድ (ቫልቭ) ጥገና ሊያመራ ይችላል

Share:

የልብ ምት ችግር (Heart palpitations) ባህሪዎች የሚከተሉት ናቸው; የልብ ምቶችን መዝለል፣ በጣም በፍጥነት ሲመታ፣ ወይም ደረታችን ላይ በፍጥነት ሲርገበገብ እና ድው ድው የሚል ድምፅ ሲሰማን። ከነዚህ ውስጥ በየትኛውም ምክንያት ሊሆን ይችላል እነሱም; ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ እንደ ቡና እና ኒኮቲን ባሉ አነቃቂዎች፣ አልኮል መጠጥ፣ ወይም በጣም ከባድ እንቅስቃሴ ስንሰራ። በአጋጣሚ በጣም አሳሳቢ ከሆኑት የልብ ምት ችግር ምክንያቶች አንደኛው የልብ ክፍክድ (ቫልቭ) ደም ወደ ኋላ የመመለስ ችግር ሊሆን ይችላል።

የሰው ልብ አራት ክፍክድ (ቫልቮች) አሉት፡ ደም ወሳጅ ክፍክድ፣ ግራ ክፍክድ፣ ደም መላሽ ክፍክድ፣ እና ቀኝ ክፍክድ ይባላሉ። እነዚህ ክፍክዶች እያንዳንዳቸው የሚከፈቱና የሚዘጉ እንዲሁም ወደሰውነት የሚሄደውን ደም የሚቆጣጠሩ መዝጊያወች አሏቸው። የልብ ክፍክድ ደም ወደ ኋላ መመለስ (የልብ ክፍክድ በአግባቡ አለመዘጋት) ችግር የሚከሰተው በልብ በሽታ ምክንያት በተጎዱ ወይም በተረበሹ የልብ ክፍክዶች አልፎ ደም ወደ ልብ ክፍሎች ልቀት ሲኖረው ነው። ይህ በትክክል ያለመስራት ችግር የደም ፍሰትን ይቀንሳል እንዲሁም የልብ ጡንቻዎች ላይ የስራ ጫና ይጨምራል።

መጠነኛ የሆነ የልብ ምት ችግር (Heart palpitations) ሲኖር ዶክተሩ የአኗኗር ዘዴን እንድንቀይር ወይም እንደ መጀመሪያ ደረጃ ህክምና መድሃኒቶችን ሊያዝ ይችላል። የተመረጠው የህክምና ዘዴዎች የልብ ችግሩን መቅረፋቸውን ለማወቅ በየጊዜው ክትትል ይደረጋል። የአኗኗር ዘዴ መቀየሩም ሆነ የመድሃኒት ህክምናው የልብ ምት መፍጠን ችግሩን ማስቀረት ካልቻሉ ወይም ምልክቶቹ ከተባባሱ ግን የልብ ክፍክድ ቀዶ ጥገና ሊያስፈልጋቸው ይችላል; የክፍክድ ጥገና ህክምና ከክፍክድ ቅየራ ህክምና ተመራጭ ነው።

መጠገን ከመቀየር ይሻላል

የልብ ክፍክድን መጠገን ከልብ ክፍክድ ቅየራ የተሻለ አማራጭ እና በጣም ተፈላጊ የሚያደርጉት በጣም ብዙ ጥቅሞች አሉት። የልብ ክፍክድ ጥገና በተፈጥሮ ያለውን ተንቀሳቃሹን ክፍክድ ለመተካት አርቴፊሻል የልብ ክፍክድ (prosthetic valve) ማለትም ከእንስሳት ወይም ከሰው የሚወሰድ ህብረ ህዋስ ወይም  ከሌላ ነገር የተሰራ መሳሪያ ማስገባት አያስፈልገውም። እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የሆነ አመላካቾች፣ ጥሩ ጎን እና ውስንነት አላቸው። ባዮሎጂያዊ ክፍክድ፣ እድሜያቸው ለገፋ ህመምተኞች ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ቢሆንም፣ ለወጣቶች ግን ሰውነት በሚኖረው ምላሽ መሰረት በፍጥነት በመበላሸቱ እና የክፍክድ መተካት በድጋሜ ማድረግ በማስፈለጉ አይመከርም፡፡ ሜካኒካል ክፍክድ የተገጠመላቸው በሽተኞች ቀሪ ህይወታቸውን የደም መርጋትን ለመከላከል የደም ማቅጠኛ መድሃኒት መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህ ውስንነቱ ልጅ በመውለጃ እድሜ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ልጁ ላይ ያልታሰበ ተፅዕኖ ሊያስከትል ስለሚችል እርግዝና እንዳይቻል ያደርጋል። በተጨማሪም መድማትና እንዲሁም መድሃኒቱ በተገቢው ሁኔታ ባለመቆጣጠሩ ምክንያት የሚከሰት የጭንቅላት ደም መፍሰስ በጣም ከባድ የሚባሉና እስከሞት የሚያደርሱ ችግሮች ናቸው። የልብ ክፍክድ ጥገና የሚያደርጉ በሽተኞች፣ የተሻለ ጊዜ የመኖር፣ የተሻለ የልብ ተግባር እና የቫልዩላር ኢንፌክሽን የመከሰት እድሉ አነስተኛ በመሆኑ የክፍክድ ጥገና ከልብ ክፍክድን መተካት ተመራጭ የሚሆንበት ዋነኛ ጥቅሞቹ ናቸው፡፡ በረዥም ጊዜ ክትትል የልብ ክፍክድ ህክምና ቀድመው ያገኙ በሽተኞች ዘግይተው ካገኙት ጋር ሲነጻፀር በሽተኛው ረዥም ጊዜ የመኖር እድል እንዳለው ማረጋገጥ ተችሏል። ይህ የሚያረጋግጠው ቀድመው የሚደረጉ ምርመራዎች እና ህክምናዎች የሚሰጡበት ጊዜ ምን ያክል የበሽተኛውን በህይት የመኖር እድል ለመመለስ ጥቅማቸው የጎላ እንደሆነ ነው።

የሁሉም በሽተኞች ችግር የተለያየ ነው እንዲሁም የየራሳቸው የሚያስጨንቃቸውም ችግር አላቸው። የቀዶ ጥገና ሀኪሙ ከሌሎች የህክምና ቡድኑ አባላት ጋር በመሆን የተሻለ  ስለሚለው የህክምና አማራጭ ከበሽተኛው ጋር ይወያያል። ውይይቱ ስለ ህክምና ምርጫው፣ የቀዶ ጥገና ሂደቱ፣ አማራጭ ህክምናወችን እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ላይ ሁሉ ይወያያሉ። የልብ ክፍክድ ጥገና በሙያው ልዩ ክህሎት ባለው የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪም እና የህክምና ቡድን መከናወን አለበት በቬጂታኒ ሆስፒታል እንዳለው በDr. Taweesak Chotivatanapong እንደሚመራው ልምድ ያለው የህክምና ቡድን ማለት ነው። ይህ የህክምና ቡድን በጣም ብዙ የልብ ቀዶ ጥገናዎችን በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። ከልብ ዶክተርወት ጋር በቅርብ በመሆን ከቀዶ ጥገና በኋላ በሚኖረው የማገገም ሂደት ላይ እንዲሁም ወደ ቀደመ ጤናማና ውጤታማ ህይወት እንዲመለሱ  ምን መደረግ እንዳለበት በጋራ በመሆን እቅዶችን በማውጣት፣ በመተግበር፣ እንዲሁም አቅጣጫዎችን በመስጠት ያግዛሉ። ዶክተርዎት ልብወትን ለመከታተል እና ጥሩ ውጤት መምጣቱንለማረጋገጥ በየቀኑ ክትትል እንዲያደርጉ ይመክራል። ይህ የዶክተር ክትትል የልብ ሪሀቢሊቴሽን እና የክትትል ምርመራወች ይከናወናሉ። በዚህ ቅርብ ክትትል እና መመሪያዎችን በአግባቡ በመከታተልት ለልባችን ጤና አስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን፣ የሰውነት እንቅስቃሴወችን እና ጭንቀትን በማስወገድ የታቀደውን ሁሉን አቀፍ ውጤቶችን በጥሩ ሁኔታ ማሳካት ይቻላል።

የልብ ክፍክድ ደም ወደኋላ የመመለስ ችግር ምልክቶችን ለይቶ ማወቅ ተማሩ

የልብ ክፍክድ ደም ወደኋላ የመመለስ ችግር ምልክቶችን ማወቅ መቻል ህይወትወን ያስረዝምልዎታል። ፈጣን የልብ ምት (Heart palpitations)፣ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ እንዲሁም የጫማና ቁርጭምጭሚት ማበጥ ምልክቶቹ ናቸው። እንዚህን ምልክቶች ካስተዋሉ በተለይ ደግሞ  እየተባባሰ የሚሄድ ከሆነ ወደ ቬጂታኒ ሆስፒታል መምጣት በልብ ሃኪም ምርመራ ማድረግ ይኖርብዎታል። አግባብነት ያለውና ጊዜውን የጠበቀ የልብ ህክምና በማድረግ የልብ ክፍክድ ደም ወደኋላ የመመለስ ችግርን በአግባቡ ማከምና ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ችግሮችን መከላከልና ማዳን ይቻላል።

  • Readers Rating
  • Rated 2.1 stars
    2.1 / 5 (10 )
  • Your Rating