የጤና መረጃዎች

የደረት ላይ ህመም (Chest Pain) – አደገኛ የልብ ድካም ምልክት ነው

Share:

ብዙ ሰዎች የደረት ህመም ወይም ጭምድድ አድርጎ የመያዝ ስሜት ለብዙ ጊዜያት አጋጥሟቸው ይሆናል፡፡ ይህ አይነት ሁኔታ የተወሰኑ የሳንባ እና የልብ በሽታዎች የማስጠንቀቂያ ምልክት መሆኑን ያውቃሉ? እንዲሁም “የልብ ድካም – Heart Attack” ካሉት አደገኛ ምልክቶች አንዱ ነው፡፡

የልብ ድካም (Heart Attack) የደም ፍሰት ሲዘጋ የልብ ጡንቻዎች በበቂ ሁኔታ እንዳይሠሩ በማድረግ የሚከሰት በጣም ከባድ ድንገተኛ የጤና ችግር ነው፡፡ ህመምተኛው ህክምናውን በሰዓቱ ካላገኘ ወደ ድንገተኛ የልብ ድካም ወይም ወደ ሞት ያደርሳል፡፡

የሚከተሉት ምልክቶች ካስተዋሉ ወዲያውኑ ህክምና ማግኘት አለብዎት፡-

 • የደረት ህመም (Chest pain) እና / ወይም ጭምድድ ማድረግ(ታካሚው በትከሻቸው ፣ በአንገታቸው እና በመንጋጋቸው አካባቢም ህመም ሊኖረው ይችላል)
 • የደረት አጥንት ታችኛው ጫፍ ላይ በሚኖር ጉዳት ምክንያት የሚከሰት ህመም (Xiphoid process pain)
 • ድካም እና ለመተንፈስ መቸገር
 • ላብ እና ማቅለሽለሽ
 • ፈጣን የልብ ምት
 • ራስ ማዞር እና ራስን መሳት

ከ20-30 ደቂቃዎች እነዚህ ምልክቶች ይስተዋላሉ ነገር ግን ሁሉ ጊዜ ምልክቶች ካሉዎት የልብ ድካም (Heart Attack) ችግር ስለሚኖር ወዲያውኑ ህክምና ማግኘት ይኖርብዎታል፡፡

ምንም እንኳን አደገኛ በሽታ ቢሆንም ራስዎን በመጠበቅ መከላከል ይቻላል፡፡ ሰዎች ጥሩ ምግብ መመገብ፣ ተደጋጋሚ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ዓመታዊ የጤና ምርመራ ማድረግ አለባቸው ፡፡ እንደ ስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ ከፍ ያለ ኮሌስትሮል፣ ወዘተ ያሉ ለችግሩ ተጋላጭ ሊያደርጉን የሚችሉ በሽታዎችን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ በቬጂታኒ ሆስፒታል የልብ ህክምና ክፍልን ያነጋግሩ; በስልክ ቁጥር +66(0)2-734-0000 ext. 5300, 5301 ያነጋግሩ።

 • Readers Rating
 • Rated 2.9 stars
  2.9 / 5 (28 )
 • Your Rating