የጤና መረጃዎች

የልብ ቫልቭ ደም ወደኋላ መመለስ ችግር – መጠገን ከመቀየር ይሻላል

Share:

የልብ ቫልቭ ደም ወደኋላ መመለስ (የልብ ቫልቭ በአግባቡ አለመዘጋት) ችግር በተወሰኑ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል በሽታ ነው፡፡ በዚህ ዘመን የልብ ቫልቭ አለመዘጋት ችግር የሚገጥማቸው ህመምተኞች የቫልቭ ማስተካከል ቀዶ ጥገና ማግኘት ይችላሉ። ይህ ቀዶ ጥገና አጥጋቢ ውጤት የሚያስገኝ እና ከልብ ቫልቭ ቅያሬ ቀዶ ጥገና ጋር ሲነፃፀሩ የጎንዮሽ ጉዳቱ አነስተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም የቫልቭ ማስተካከል ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ህመምተኞች የልብ ቫልቭ ቅያሬ ቀዶ ጥገና ከተደረገላቸው ህመምተኞች የተሻለ ረዥም ህይወት ይኖራቸዋል፡፡  

የቬጅታኒ ሆስፒታል የልብና የደረት ቀዶ ጥገና ሐኪም (cardiothoracic surgeon) የሆኑት ዶክተር ታኒሳክ ቾንቲቫንታናፓንግ እንደተናገሩት የልብ ቫልቭ በአግባቡ አለመዘጋት ችግር ማለት የልባችን ቫልቭ ላይ ቀዳዳ ሲኖረው ወይም ቫልቮቹ በትክክል ባለመዘጋታቸው ምክንያት የደም ልቀት ሲኖር ነው፡፡  ይህ ችግር ልብ ተግባሩን በትክክል እንዳያከናውን ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ ልባችን 5 ሊትር አካባቢ የሚሆን ደም የሚረጭ ቢሆን ነገር ግን ቫልቮቹ በትክክል ባለመዘጋታቸው ምክንያት 2 ሊትር ደም ወደኋላ ተመልሶ ይፈስሳል ይሄን ለማስተካከል ልብ መስራት ከሚገባው በላይ መሥራት ይኖርበታል። በመሠረቱ ልቀቱ ትንሽ ከሆነ ምንም አይነት የሕመም ምልክቶች አይታይም ነገር ግን ከባድ በሚሆንበት ጊዜ ህመምተኛው የሚከተሉትን ምልክቶች ይኖሩታል፦

  • በቀላሉ የመድከም ስሜት
  • የመፍዘዝ
  • ራስን መሳት
  • የደረት ህመም
  • የልብ ምት መፍጠን 
  • በእግር ጫማ እና ቁርጭምጭሚት ላይ እብጠት (Edema) 

የልብ ቫልቭ በአግባቡ አለመዘጋት ችግር በተለያዩ የእድሜ ደረጃዎች ሲከሰት የተለያዩ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡ ለምሳሌ በልጆች ላይ ሲከሰት በአብዛኛውን መንስኤው ከውልደት ጀምሮ በሚከሰት የልብ ችግር (congenital heart disease) እና በrheumatic በሽታ (streptococcal በሚባል ባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጣ በሽታ) ምክንያት ነው።  እንዲሁም በአረጋውያን ላይ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ በሚከሰት የውስጣዊ አካላት ማርጀት (body’s deteriorates) ወይም በኢንፌክሽን ምክንያት ነው። በልብ ቫልቭ በአግባቡ አለመዘጋት ችግር ምክንያት ከባድ የህመም ምልክት ያላቸውን ህመምተኞች በመድሃኒትና በቀዶ ጥገና ማዳን ይቻላል፡፡  ሁለት ዓይነት የልብ ቫልቭ ቀዶ ጥገና ዓይነቶች አሉ እነሱም እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፦

  • የልብ ቫልቭን የማስተካከል ቀዶ ጥገና፦ ይህ ቀዶ ጥገና የተፈጥሮ የልብ ቫልቭ ህብረ ህዋስ (tissue) ስለሆነና የልብ ቫልቩን መደበኛ ተግባር ስለሚመልስ፣ እንዲሁም በልብ ውስጥ የሚከሰት የደም መርጋት እና የደም መፍሰስ ተጋላጭነትን ስለሚቀንስ ለታካሚው ያለው የጎንዮሽ ጉዳት የቀነሰ ነው፡፡ 
  •  የልብ ቫልቭ ቅያሬ ቀዶ ጥገና፦ የልብ ቫልቭን መደበኛ ተግባር መመለስ ካልተቻለ የቫልቭ ቅያሬ ቀዶ ጥገና ይመከራል፡፡ የታካሚውን የልብ ቫልቭ ለመተካት ሰው ሰራሽ ቫልቭ ፣ ከብረት የተሰራ የልብ ቫልቭ ወይም የእንስሳት (የአሳማ / ከብት) የልብ ቫልቭ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡  ይሁን እንጂ የቫልቭ ቅያሬ ቀዶ ጥገና የልብ ቫልቭን ለማስተካከል ከሚደረግ ቀዶ ጥገና ጋር ሲነፃፀር ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም ሰው ሰራሽ የልብ ቫልቭ (mechanical heart valve) የተገጠመለት ህመምተኛ ቀሪ ሕይወቱን የደም ማቅጠኛ መድሃኒት መውሰድ አለበት፡፡

ከቀዶ ጥገናው በኋላ ልብ ያለምንም ችግሮች መደበኛ ተግባሩን ማከናወን እስከሚጀምርበት ጊዜ ድረስ ሐኪሙ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ መከታተል አለበት፡፡ ሊመጡ የሚችሉ ያልተጠበቁ ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል ታካሚው በየቀኑ ሐኪሙን ማየት ይኖርበታል፡፡

ከቀዶ ጥገናው በኋላ የልብን ተግባር ለመጨመር ታካሚው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዘውትሮ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ይሁን እንጂ ስለምሰራው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ከዶክተሩ ጋር መመካከር ይኖርበታል ፡፡  የልብ ቫልቭ በአግባቡ አለመዘጋት ችግር በምርመራ ማረጋገጥ እና ታክሞ መዳን ይችላል፡፡ በመሆኑም አጠራጣሪ ምልክቶችን ካስተዋሉ ወይም ማናቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት ለጥንቃቄ እና ለወደፊት ደህንነትዎ ባስቸኳይ ዶክተር ማየት ይኖርብዎታል።

  • Readers Rating
  • Rated 4.9 stars
    4.9 / 5 (6 )
  • Your Rating