የጤና መረጃዎች

ሉኪሚያ ( Leukemia ) ማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል አደገኛ በሽታ ነው።

Share:

በጅምሩ ከታወቀ  የምናገኘው ህክምና ውጤታማነቱ ከፍ ያለ ነው፡፡

ሉኪሚያ ያልተለመደ መልኩ የደም ህዋሳት ከመጠን በላይ በመመረት ምክንያትየሚከሰት የነጭ የደም ሴሎች ካንሰር ነው። ይህ የካንሰር አይነት የሚከሰተው የደም ሴሎች የሚመረቱበት የአጥንት መቅኔ ውስጥ ነው ፡፡ ሰውነታችን ባልተለመደ መልኩ የደም ሴሎችን ከልክ በላይ በሚያመርትበት ጊዜ ጤናማ የደም ሴሎች እንዲቀንሱ ያደርጋል፣በዚህም ምክንያት ጤናማ ያልሆኑ የደም ሴሎች ያሏቸው ታካሚዎች የሚከተሉትን ምልክቶች ይታዩባቸዋል፦  

  • የቀይ የደም ሕዋሳት መመረት መቀነስ፦ ሰውነታችን ጥቂት  የቀይ የደም ህዋሳትን የሚያመርት ከሆነ የደም ማነስ ፣ ድካም ፣ የአቅም ማጠር ፣ሽፍታ እና ተዝለፍልፎ መውደቅ ያስከትላል ፡፡
  • ያልተለመደ የነጭ የደም ህዋስ መመረት፦ ሰውነት ባልተለመደ መልኩ ነጭ የደም ህዋሳትን የሚያመነጭ ከሆነ የበሽታ የመከላከል አቅማችን ይቀንሳል ይህም በሽተኛው በቀላሉ በኢንፌክሽን እንዲያዝ እንዲሁም ኢንፌክሽን ከተለመደው በተለየ ሊፀናበት ይችላል።  በተጨማሪም በሽታን የመከላከል አቅም በትክክል ተግባሩን በማያከናውንበት ጊዜ፣ በሳንባዎች ወይም በደም ስሮች ላይ የፈንገስ ኢንፌክሽን ሊከሰት ይችላል ፡፡  
  • ያልተለመደ የፕላትሌት መመረት:  ሰውነት ያልተለመደ የፕላትሌት የደም ህዋሳትን ካመረተ፣ የደም መፍሰስ ችግር ፣ የድድ መድማት፣ ነስር ፣በቆዳ ላይ ደም የቋጠሩ ነጠብጣቦች መታየት ወይም በቀላሉ ሰውነት መበለዝ ሊያጋጥም ይችላል።  

ከተጠቀሰው የሕመም ምልክቶች በተጨማሪ የሉኪሚያ ሕዋሳት በተለያዩ የአካል ክፍሎች ላይከተከማቹ በሽተኛው ላይየድድ እብጠት እና / ወይም የጣፊያ እብጠት / ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ።

  • Readers Rating
  • Rated 3.1 stars
    3.1 / 5 (6 )
  • Your Rating




Related Posts