የጤና መረጃዎች

ብዙ ሰዓት ስክሪን ላይ ማሳለፍ ለአከርካሪ አጥንት ጉዳት እንደሚያጋልጥ ያውቃሉ ?

Share:

አጥንት ጉ ዛሬ ዛሬ ቴክኖሎጂ ያመጣቸው ስማርትፎኖች ጊዜያችንን እየወሰዱ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው አብዛኛዎቻችን ብዙ ሰዓታችንን የምናጠፋው ስክሪን ላይ መሆኑም ይታወቃል ታዲያ ይህ ልማድ ጤናችንን ለከፋ ሁኔታ የሚያጋልጥ እንደሆነስ የምናውቅ ምን ያክሎቻችን ነን

በየደቂቃው ጎንበስ ቀና በማለት ስልካችንን የማየት ልማድ አንገታችን ላይ ጫና በማሳደር Cervical Spondylosis ለተባለው ህመም ተጋላጭ ያደርገናል ይህ የጤና እክል በአብዛኛው በቴክኖሎጂ በለጸጉ በሚባሉ ሀገራት የሚኖሩ ሰዎች ላይ በስፋት ሲስተዋል ከዚህ በተጨማሪም የእድሜ መጨመር የአከርካሪ አጥንትን ጥንካሬ ስለሚያሳጣ ለዚህ ችግር ይበልጥ ተጋላጭ ያደርገናል

የህመሙን ምልክቶች ስንመለከት

  • ምክኒያቱ ያልታወቀ የጸና የአንገት ህመም አንዳንዴ ደግሞ ወደ ትከሻ እና ክንድ የሚሄድ ህመም
  • በክንድ እና በእጆች ላይ የሚሰማ እንደ መርፌ የመውጋት ወይም የመደንዘዝ ስሜት
  • የጡንቻ መዛል እንዲሁም ሚዛንን የመሳት ስሜት ባስ ሲልም ሽንት እና ሰገራ መቆጣጠር ያለመቻል ስሜት ይገኙበታል

በአነስተኛ ቅድ የሚሰራ cervical spondylosis ህክምና

የዚህ ህመም ህክምና እንደ በሽታው የጉዳት መጠን የሚለያይ ሲሆን ብዙ ያልባሰ ችግር ከሆነ ሀኪሙ ህመሙን ለማስታገስ ቀለል ያለ የሰውነት እንቅስቃሴ እና የኑሮ ዘይቤ ለውጥ እንዲያደርጉ ያበረታታል ነገር ግን ህመሙ የታካሚውን የየእለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚረብሽ ሆኖ ከተገኘ ሌሎች አማራጮችን ማለትም የመድሃኒት ህክምና እንዲሁም የፊዚዮቴራፒ ህክምናን በጣም እጅግ ከባሰ ደግሞ የነርቭ ጉዳትን ለመከላከል የቀዶ ህክምና እንደአማራጭ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

አሁን ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ቀዶ ህክምና ሀኪሙ ሰውነትን መክፈት ሳይጠበቅበት በአነስተኛ ቅድ በሚከናወን (Minimally Invasive) ሲሆን ከ2-2.5 ሴንቲሜትር በሚያክል አነስተኛ ቅድ ብቻ እየተከናወነ ነው ይህም ታካሚውን ከብዙ ህመም የሚገላግል ከመሆኑም በላይ የማገገሚያ ጊዜውም እንዲያጥር ያደርጋል ማለት ነው

cervical spondylosis ህመምን ለመከላከል የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች

በየእለቱ ስንቆም ስንቀመጥም ሆነ ስንራመድ አንገታችን ላይ የሚኖረውን ጉዳት ለመቀነስ በተገቢው ሁኔታ ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ በተቻለ መጠን ጎንበስ ቀና የሚያስብለንን ነገር መቀነስ ወይም አንገታችንን በአንድ አቅጣጫ ላይ አድርገን ብዙ ሰዓት የመቆየት ልምድን መቀነስ

ሁሌም ቢሆን የአንገት ህመም በምንም ደረጃ ቢኖር ችላ ከማለት ይልቅ አስፈላጊውን ህክምና ለማግኘት ቶሎ ወደ ሀኪም ዘንድ መሄድ ያስፈልጋል፡፡

ስለ የጀርባ አጥንት ህክምና ክፍል መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (2 )
  • Your Rating
Related Posts