በህጻናት ላይ የሚታይ ማንኮራፋት አንዳንዴ የህመም ምልክት ሊሆን እንደሚችል ያውቃሉ ?

የጤና መረጃዎች
Featured Image

ለህጻናት የእንቅልፍ ጊዜያቸው ዘና የሚሉበት እንዲሁም ፍጹም እረፍት የሚያደርጉበት ሰዓት ሲሆን በእንቅልፍ ጊዜ የሚከሰት የትንፋሽ ማጠር ግን ህጻናቱ የአየር ቧንቧ መዘጋት እንዲገጥማቸው በማድረግ የአተነፋፈስ መስተጓጎልን ያስከትላል በዚህን ወቅት ደግሞ ሳምባ እና ልብ ላይ ጫና ስለሚፈጠር በወጣትነት ጊዜ ለሚከሰት የደም ግፊት እና የልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

ህጻኑ/ኗ የዚህ ህመም ተጠቂ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

ይህን ችግር ለማወቅ ሀኪሙ በቅድሚያ የህጻኑን የጤና ሁኔታ ከወላጆች በሚገባ ከጠየቀ በኋላ ከችግሩ ጋር ተያያዥነት ሊኖራቸው የሚችሉ እንደ የቶንሲል እንዲሁም አዲኖይድ ማበጥ ካለ አካላዊ ምርመራ ያደርጋል በመቀጠልም የህጻኑን የእንቅልፍ ሁኔታ ለመገምገም ፖሊሶሞኖግራፊ የተባለው ምርመራ ይደረግለታል፡፡ይህ ምርመራም በእንቅልፍ ሰዓት የሰውነታችንን ለውጦች በተለይም የኦክስጂን መጠንን ለመለካት ፤ ወደ አንጎል የሚተላለፉ መልእክቶችን ለመመርመር ፤የልብ ምት ሁኔታን ለማየት ፤እንዲሁም ሌሎች ከ20 በላይ የተለያዩ ምርመራዎችን በአንድ ማታ ለመስራት ይረዳል፡፡

የህክምና አማራጮች

ወደ ህክምና አማራጮቹ ስንሄድ አነስተኛ የእንቅልፍ ችግር በመድሃኒት መታከም የሚችል ሲሆን ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ያለ ችግር ግን በመድሃኒት እርዳታ የመታከም እድሉ አነስተኛ ስለሆነ ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ቀዶ ጥገናው ቀለል ያለ እና ብዙ ውስብስብ ያልሆነ ለማገገምም ከ2-3 ቀን ብቻ የሚፈጅ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በልጆች ላይ የሚፈጠር ማንኮራፋት በጣም የተለመደ ነገር ቢሆንም ብዙ ችላ ከተባለ ወደ ውስብስብ ችግር በማደግ ህይወትን ሊቀጥፍ ይችላል፡፡ስለዚህ ሁልጊዜም ቢሆን የልጅዎን እንቅልፍ ሁኔታ በመከታተል የተለየ ችግር ካስተዋሉም ወደ ህጻናት ስፔሻሊስት ዘንድ በመሄድ ማማከር ሊፈጠር ከሚችለው አደጋ ይጠብቃል፡፡

Readers’ Rating

0.0 out of 5 stars (based on 0 reviews)