የጤና መረጃዎች

በልጆች ላይ የሚከሰት የአከርካሪ መዛባትን (ስኮሊዎሲስ : Scoliosis) ለማከም አዲስ የቀዶ ጥገና ዘዴ

Share:

ስኮላዮሲስ (Scoliosis)  በብዙ በሰዎች ላይ የሚከሰት የአከርካሪ አጥንት በሽታ ነው። 80 ከመቶ የሚሆኑት የችግሩ ተጠቂ ሰዎች ምክንያቱ የማይታወቀ (idiopathic) የአከርካሪ መዛባት (ስኮሊዎሲስ : Scoliosis) ሲሆን ሌሎች 20 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ በዘር ውርስ ፣ ባልተለመደ የጡንቻ ነክ በሽታዎች ምክንያት ወዘተ የሚመጣ ነው።

የቬጂታኒ ሆስፒታል የአከርካሪ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ቲናኮርን ፕልዩምቪታያፖርን እንደገለጹት ምክንያቱ የማይታወቀ የአከርካሪ መዛባት (idiopathic scoliosis) የሚከሰተው ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 18 ዓመት ላይ ባሉ በጨቅላ ህፃናቶችና በታዳጊዎች ላይ ነው ፡፡ ይሁን እንጅ በብዛት የሚከሰተው ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 15 አመት በሆኑት ላይ ነው። እንዲሁም ሴት ህፃናት ከወንዶች የበለጠ የችግሩ ተጠቂ ናቸው ንፅፅሩም 10 ለ 1 ነው፡፡

ዶክተር ቶኒናርት እንደተናገሩት “አብዛኛዎቹ ህመምተኞች የተዛነፉ ትከሻዎች ወይም ዳሌዎች አሏቸው። የተወሰኑት ደግሞ ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ማለትም ሥር የሰደደ የጀርባ ህመም፣ ወይም የነርቭ እና የጡንቻ ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል። ለidiopathic scoliosis ህክምና ሐኪሙ የታካሚውን የህመም ምልክቶችንና የራጅ ምርመራወችን መከታተል ይቀጥላል፣ ህመምተኛው የጀርባ ድጋፍ ሰጭ (back braces) እንዲለብስ ማድረግና ህመሙን መቆጣጠር፣ እንዲሁም የአከርካሪ አጥንቱን ለማቃናት የአከርካሪ ቀዶ ሕክምና ይደረጋል”፡፡

Idiopathic scoliosis ላለባቸው ህመምተኞች ከሚደረጉ የተለመዱና ሐኪሞች በብዛት ከሚጠቀሟቸው የአከርካሪ አጥንት ህክምና አይነቶች Deformity እና የአከርካሪ መዛባትን የማስተካከል ቀዶ ህክምና በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ቀዶ ጥገናው የአከርካሪዎችን አንጓወች በቋሚነት በማያያዝ ቀጥ ለማድረግና የአከርካሪ አጥንቶቹን መጣመም ለመቀነስ የሚደረግ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የብረት screws, rods, እና plates በመጠቀም ይከናወናል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ቀዶ ጥገና የሚከተሉትን ጉዳቶች ያስከትላል የመጀመሪያው እንቅስቃሴዎችን መገደብ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ መሃል ጀርባ ላይ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ ማለፉ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ Anterior Vertebral Body Tethering Procedure (AVBT) የተባለ አዲስ የአከርካሪ ቀዶ ጥገና ዘዴ አለ። ይህ ዘዴ  ስኮላዮሲስ (Scoliosis) ለማከም fusion less ዘዴን ከሞጁሌሽን ቴክኒክ (የሚጎብጠውን የአጥንቱን ክፍል እድገቱን በማዘግየት በትክክለኛ ሂደት እንዲያድግ የማድረግ ህክምና ነው) ጋር በማቀናጀት የሚከናወን ህክምና ነው፡፡ በዚህ የህክምና ሂደት የአከርካሪው የእድገት ፍጥነት በጤናማ መልኩ ይሆናል፡፡ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ የአከርካሪውን መጉበጥ ለማስተካከል ጠንካራ ተጣጣፊ ኬብል/ፖሊመር (Polyethylene-terephthalate) ይጠቀማል። ከባህላዊው የአከርካሪ ቀዶ ጥገና ሂደት ጋር ሲነፃፀር በቀላሉ ይተጣጠፋል። ከዚህም በተጨማሪ ሕመምተኛው በቀዶ ጥገና ወቅት ብዙም ጉዳት ስለማይደርስበት ለማገገም የሚወስድበት ጊዜ ፈጣን ይሆናል። እንዲሁም ህመምተኛው ከቀዶ ጥገናው በኋላ ከ 6 እስከ 8 ሳምንታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ስፖርታዊ እንቅስቃሴወችን ማድረግ ይችላል ፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 3.8 stars
    3.8 / 5 (3 )
  • Your Rating




Related Posts