Patient Rights & responsibilities

የታካሚዎች መብት አና ግዴታ መመሪያ ደንብ

ይህ ደንብ የተዘጋጀው ታካሚዎች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥና ከህክምና ባለሙያዎች ጋር የሚኖራቸውን ትብብር ጥቅም በማስተዋል ነው:: ስለዚህም የሜዲካል ካውንስል፣ የነርሲንግና የአዋላጅ ነርስ ክፍል፣ የመድሀኒት ክፍል፣ የጥርስ ህክምና ክፍል፣ የአካል ቴራፒ ክፍል፣ የሜዲካል ቴክኖሎጂ ክፍል እንዲሁም የማዳን ጥበብ ኮሚቴ ይሄንን የታካሚዎች መብትና ግዴታ መመሪያ ደንብ እንደሚከተለው ያሳውቃሉ:

የታካሚዎች መብት መመሪያ ደንብ

  1. ማንኛውም ታካሚ በታይላንድ ህገመንግስት እንደተገለፀው የሜዲካልና ጤና እንክብካቤ አገልግሎቶችን በባለሙያ ደረጃ ያለምንም አድልኦ የማግኘት መሰረታዊ መብት አለው::
  2. የሜዲካልና ጤና እንክብካቤ አገልግሎት የሚፈልጉ ታካሚዎች ድንገተኛ ህክምና የሚጠይቅና ለህይወት አስጊ ደረጃ ላይ ካልሆኑ በቀር ስለ ህመማቸው, ስለ ህክምና, ስለ ሙከራ(ኤግዘሚኔሽን)፣ ስለ ሙከራው/ምርመራው ጥቅምና ጉዳት የህክምና አገልግሎቱን ለመቀበል ወይም ለመቃወም እንዲረዳቸው እውነተኛና በቂ መረጃ ታካሚው በሚረዳው ቋንቋ ከሜዲካል ሰራተኛ የማግኘት መሰረታዊ መብት አላቸው::
  3. በአደገኛ ሁኔታ, ከሞት አፋፍ, እንዲሁም አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ያሉ ታካሚዎች እንዳስፈላጊነቱ በፈቃዳቸውም ሆነ ያለፍቃዳቸውም ካሉበት ችግር በፍጥነትና በቶሎ እረፍት እንዲያገኙ በህክምና ሰራተኞች መታገዝ አለባቸው::
  4. ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጧቸውን ሰራተኞች ስም፣ የአባት ስም፣ እንዲሁም የትምህርት ደረጃና አይነት የማወቅ መብት አላቸው::
  5. የህክምና አገልግሎት ከሚሰጠው ዶክተር ውጭና በሌላ የህክምና ስፔሻሊቲ ያለውን ሁለተኛ ወገን ሀሳብ መጠየቅ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ወይም እንክብካቤ የሚያገኝበትን ቦታ መቀየር የታካሚው መብት ነው:: ይህ የሚሆነው ባሉት የታካሚዎች መብት መመሪያ መሰረት ነው::
  6. ታካሚው የግል የህክምና መረጃዎቹ/መረጃዎቿ በሚስጥር እንደሚጠበቅለት የማወቅ መብት አለው:: ይህ የማይሆንበት ብቸኛ ምክንያት በታካሚው ፈቃድ ወይም ህጋዊ በሆኑ መንገዶች ብቻ ነው:;
  7. ታካሚው በሚያገኘው ህክምና እና በሚደረገው ምርምር ያለውን ተሳትፎ በተመለከተ እንዲሁም ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ጉዳቶች የተሟላና ጊዜያዊ መረጃ የማግኘትና ይህንን ግምት ወስጥ በማስገባት በምርምሩ ላይ የመቀጠል ወይም ያለመቀጠል እንዲወስን እንዲረዳው በህክምና ሰጭው አማካኝነት የማወቅ መብት አለው::
  8. ታካሚው ህክምና መረጃው ላይ እንደተቀመጠው ስለሚያገኘው የህክምና አገልግሎት የተሟላና ጊዜያዊ መረጃ የማወቅና የመጠየቅ መብት አለው:: ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚገኘው መረጃ የሌሎች ታካሚዎችን የግል መረጃና መብት የሚፃረር መሆን የለበትም::
  9. ታካሚው ከ18 አመት በታች ከሆነ ወይም የአዕምሮ/የአካል ችግር ካለበት እና የራሱን/የራሷን መብት ማስጠበቅ በማይችልበት ሁኔታ ታካሚው እናት/አባት ወይም ህጋዊ ተወካይ መብቱን መጠቀም ይችላሉ::

የታካሚው ሀላፊነቶች/ግዴታዎች

  1. ታካሚዎች የስምምነት ፎርም ከመሙላታቸው በፊት ወይም የህክምና ምርመራውንና አገልግሎቱን ከመቃወማቸው በፊት ስለ ህክምናው እውነተኛና በቂ መረጃ እንዲሁም ጉዳት መጠየቅ አለባቸው::
  2. ታካሚው የህክምና አገልግሎት በሚያገኝበት ጊዜ ስለራሱ ማንነት እና እውነት እንዲሁም የጤንነት ሁኔታው ለህክምና ሰራተኞች ማሳወቅ አለበት::
  3. ታካሚው ከህክምና ሰጭው ሰራተኛ ጋር መተባበርና ስለሚያገኘው የህክምና አገልግሎት መከታተል አለበት:: ታካሚው ይሄንን ማድረግ የማይችል ከሆነ እባክዎ ለህክምና አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች ያሳውቁ::
  4. ታካሚዎች የሆስፒታሉን ህግና ደንቦች መከተል እንዲሁም መተባበር አለባቸው::
  5. የህክምና አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞችን፣ ሌሎች ታካሚዎችን እና ጎብኝዎችን በጨዋነትና በክብር ያስተናግዱ:: ምንም አይነት ረብሻዎችን ከመፍጠር ይቆጠቡ/ያስወግዱ::
  6. የታካሚውን መብት ያሳውቁ እንዲሁም ማስረጃውን ለሆስፒታሉ ሰራተኞች ያሳዩ::
    Here
  7. ታካሚዎች ስለሚከተሉት የሜዲካል እውነታዎች ማወቅ አለባቸው:

7.1. በደንብና በስነ ምግባር መሰረት የሚሰሩ የሜዲካል ሰራተኞች በህጉ መሰረት ጥበቃ ያገኛሉ:: ውሸት ከሆነ ውንጀላ የመጠበቅ መብት አለው/አላት::
7.2 ሜዲካል ፕራክቲስ(የህክምና አገልግሎት) ማለት በዘመኑ ጊዜያዊ እውቀት የተረጋገጠ እንዲሁም ለታካሚዎች ከጉዳት ይልቅ ጥቅም የሚሰጥ ዘመናዊ መድሀኒት ማለት ነው::
7.3 የህክምና አገልግሎት ለሁሉም አይነት በሽታዎች ወይም ሁኔታዎች ፍፁም የሆነ የህክምና ምርመራ, መከላከያ እና እንክብካቤ ላይሰጥ ይችላል::
7.4 የትኛውም የህክምና አገልግሎት የበለጠ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት የሚፈጥርበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል:: በተጨማሪም የህክምንም አገልግሎት ሰጭዎች በየትኛውም አይነት ጥንቃቄ የተሞላበት ሁኔታ ቢሰሩ እንኳን ያልተጠበቀ ጉዳት ሊደርስ ይችላል::
7.5 የትኛውም ማጣሪያ, ምርመራ,እንዲሁም የክትትል አገልግሎት በቴክኖሎጂ እጥረት እንዲሁም በሌሎች መቆጣጠር በማይቻሉ ሁኔታዎች ምክንያት ስህተት ሊፈጠር ይችላል::
7.6 የህክምና አገልግሎት ሰጭዎች የሜዲካል እውቀታቸውን, ችሎታቸውን, ያለውን ውስንነት, አላማ እንዲሁም ሁኔታዎች መሰረት የህክምና አገልግሎቱን በተመለከተ የራሳቸውን ግምታዊ ውሳኔ እንዲሰጡ ይፈቀድላቸዋል:: ይሄም ታካሚውን ማማከርና እንዲሁም ዝውውሩ የታካሚውን መብትና ጥቅም በጠበቀ መልኩ መሆኑ መረጋገጥ አለበት::
7.7 ለታካሚዎች ጥቅም ሲባል በፍላጎታቸው መሰረት የህክምና አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች ለታካሚው ሀሳብ መስጠት ወይም ወደሌላ ክሊኒክ ለተገቢ ህክምና እንዲዘዋወር ሊያደርጉ ይችላሉ:: በዚህ ሁኔታ ታካሚዎች አጣዳፊና ህይወት እስጊ ሁኔታ ላይ መሆን የለባቸውም::
7.8 የህክምና አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች የሜዲካል መረጃ እና እውነት እንዳያውቁ ማድረግ በህክምና አገልግሎቱ ላይ መጥፎ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል::