የቬጂታኒ ሆስፒታል የሴቶች የጤና ማዕከል ከማህጸን እና ጽንስ ጋር የተያያዙ ችግሮቸን እጅግ በተካኑ እና የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ስፔሻሊስት ሀኪሞች የተሟላ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የማህጸን እና ጽንስ ምርመራ ፤ የሴት መራቢያ አካላትን የሚያጠቃ ካንሰር ምርመራ እና ሕክምና ይሰጣሉ፡፡
የሆስፒታላችን ሀኪሞችም እነዚህን እና የመሳሰሉትን የጤና እክሎች መፍትሄ ለመስጠት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁን ለመመለስ ዝግጁ ናቸው፡፡
የሆስፒታላችን ሀኪሞችም እነዚህን እና የመሳሰሉትን የጤና እክሎች መፍትሄ ለመስጠት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁን ለመመለስ ዝግጁ ናቸው፡፡
አገልግሎቶች
- ከማህጸን ጋር የተያያዙ ችግሮች ህክምና ለምሳሌ የማህጸን ፈሳሽ፤ከማህጸን የሚፈስ ደም፤ እንዲሁም የወር አበባ መዛባት ህክምና
- ያልተለመደ የሆድ ውስጥ እባጭ እና የሴት ብልት ዙሪያ የሚወጣ እባጭ ህክምና
- የማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ፤ የሴቷ የመራቢያ አካል ካንሰር ህክምና
- የጽንስ ክትትል
- በተፈጥሮ መንገድም ሆነ በቀዶ ጥገና የማዋለድ አገልግሎት
- የድህረ ወሊድ አገልግሎት
- የእንቁላል መውረጃ ትቦን በጊዜያዊነት ወይም በዘላቂነት ማስቋጠር ህክምና
- በእድሜ ወይም በወሊድ ምክኒያት የመጣ የብልት መስፋትን የማስተካከል ህክምና
- በላፓራስኮፒ የታገዘ ቀዶ ጥገና
- የእርግዝና መቆጣጠሪያ እንዲሁም የቤተሰብ ምጣኔ የማማከር አገልግሎት
- የቅድመ ጋብቻ የማማከር አገልግሎት
- የአባላዘር በሽታዎች ህክምና
- ዩሮ ጋይናኮሎጂካል እና ሪኮንስትራክቲቭ ፐልቪክ ሰርጀሪ
ተጨማሪ አገልግሎቶች
- የግል ማማከሪያ እንዲሁም የአካላዊ ምርመራ ክፍል
- የአልትራሳውንድ ምርመራ
- ማሞግራፊ እና የባዮፕሲ አገልግሎት
- የማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ማዕከል
- ኮልፖስኮፒ(Colposcopy)
- ለሚወልዱ እናቶች ንጹህና ምቾታቸውን ያሟላ የማዋለጃ ክፍል
- አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጽንስ ጤንነት መከታተያ መሳሪያ
- የጨቅላ ህጻናት ህክምና ክፍል (NICU)
- የነፍሰጡር እናቶች ክትትል ክፍል
የአገልግሎት ሰዓታት
ሰኞ - እሁድ : 08.00 am - 08.00 pm
ቦታ
የሴቶች ጤና ማዕከል፣ 2ኛ ፎቅ ፣ ቬጅታኒ ሆስፒታል
ቀጠሮዎች እና ጥያቄዎች
ይደውሉ: (+66)2-734-0000 ext. 3200, 3204
