የቬጅታኒ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ማዕከል አዲስ ምዕራፍ ጀምሯል
ለጀርባ አጥንት፣ musculoskeletal እንዲሁም የአጥንት ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የሚሰጠው ሁሉን አቀፍ ህክምና በአንድ ስፔሻሊስት ብቻ የሚሰጥ ሳይሆን የበርካታ ዲሲፕሊን የህክምና ቡድን ማለትም የአጥንት ህክምና ቡድን፣ ፊዚያትሪስቶችን፣ ፊዚዮቴራፒስቶችን እና occupational ቴራፒስቶችን ያካትታል።

የዘመናችን የህክምና ቴክኖሎጂዎች ለእግር እና ቁርጭምጭሚት የሚደረጉ ቀዶ ጥገናዎች ህመምተኞች ላይ እጅግ አነስተኛ የሰውነት መቀደድ፣ ዝቅተኛ ህመም እና ፈጣን የማገገም አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችለውን የኢንዶስኮፒ እና የአርትሮስኮፒን እንደሚጠቀሙ ሆነው እየተሰሩ ነው።
በቀዶ ጥገና ሂደቱ ወቅት የቀዶ ጥገና ሐኪሙ 8 ሚሜ የሚሆን ቆዳችን ክፍል ላይ ከቀደደ በኋላ ቀጭን ተጣጣፊ 4.0 ሚሜ ወይም 2.7 ሚ.ሜ. የፋይበር ኦፕቲክ ካሜራ (ኢንዶስኮፒ ወይም አርተሮስኮፒ) እና ሌሎች መሳሪያዎች የተጎዳውን አካባቢ ምርመራ እና ሕክምናውን ለማካሄድ በተቀደደው ቦታ በኩል ይገባሉ፡፡ በሰአቱ የሚከናወነውን ተግባር በቀጥታ የኮምፒውተር ስክሪኑ ላይ ይታያል። በተጨማሪም የቀዶ ጥገና ሐኪሙ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሂደቱን ቪዲዮ መቅዳት ይችላል፡፡
Minimally Invasive Surgery ያደረጉ ህሙማኖች ክፍት ቀዶ ጥገና ካደረጉት ጋር ሲነፃፀሩ በአጥንታቸው እና በህብረ ህዋስ (tissue) ላይ የሚደርሰው ጉዳት አነስተኛ በመሆኑ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ማከናወን ጊዜ አይወስድባቸውም፣ በዚህም ምክንያት ህመምተኞቹ ፈጣን የማገገሚያ እና ለተጎዳው አካል የሚለበሰው ድጋፍ ለአጭር ጊዜ ብቻ እንዲሆን ያስችላቸዋል፡፡
Minimally Invasive surgery ከቀዶ ጥገናው በኋላ በተለይም የስኳር በሽታ ላለባቸው ህመምተኞች የኢንፌክሽን ስጋትን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ህመምተኞቹ የሆስፒታል ቆይታ ጊዜያቸው እንዲቀንስ በማድረግ የህክምና ወጪዎቻቸውን እንዲቆጥቡ ያስችላቸዋል፡፡