የጤና መረጃዎች

የካንሰር ተጋላጭነታችን ለማወቅ፣ ለመከላለል እና ትክክለኛ ህክምና ለማድረግ የሚደረግ የጀነቲክ (ዘረመል) ካንሰር ምርመራ

Share:

ዘረመሎች ለብዙ የካንሰር ዓይነቶች እድገት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። በአሁኑ ጊዜ የሚደረጉ የጄኔቲክ ምርመራዎች ለካንሰር ያለንን ተጋላጭነት ለማወቅ እና የአኗኗር ዘይቤያችን ለማስተካከል ይረዱናል። የጄኔቲክ ምርመራ ለካንሰር ሕመምተኞች ትክክለኛ የሕክምና እቅድ ለማውጣት ያገለግላሉ በዚህም ምክንያት ጤነኛዎች የሰውነት ሕዋሳት በሕክምናው አይጎዱም።

የቬጅታኒ ሆስፒታል የካንሰር ሃኪም የሆኑት Dr. Natchadol Kittiwararat በአጠቃላይ በሰውነታችን ውስጥ ካሉት 20,000 ዘረመሎች ውስጥ 500 ያህሉ ከካንሰር ጋር የተያያዙ ጂኖች እንደሆኑ ያስረዳሉ። በዋናነት በሁለት ትልልቅ መደቦች ይከፈላሉ። የመጀመሪያው ኦንኮጂን (oncogenes) ሲሆን ይህም ሴሎች ከቁጥጥር ውጭ እስኪሆኑ ድረስ እንዲያድጉ እና እንዲባዙ ያደርጋል። ሁለተኛው ቡድን tumor suppressor ጂኖች ሲሆኑ የተጎዳውን DNA ለመጠገን እና የሴሎችን መባዛትን የሚያዘገዩ መደበኛ ጂኖች ናቸው። እነዚህ ጂኖች በትክክል ስራቸውን ሳይሰሩ ሲቀሩ ሴሎች ከመጠን በላይ በመባዛት በመጨረሻም ወደ ካንሰር ያመራሉ። 

አብዛኛው ሰው ካንሰራማ ጂኖች ይዞ ይወለዳል፣ እነዚህ ጂኖች በተለየ ሁኔታ ህዋሳቶቹ ሚውቴሽን (ለውጥ) አድርገው ወደ ካንሰርነት ካልተቀየሩ በስተቀር በመደበኛነት ወደ ካንሰርነት አያመሩም። ካንሰርን የሚያስከትሉ ሁለት ዓይነት ሚውቴሽን አሉ። እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ 

ጀርምላይን ሚውቴሽን (Germline mutation) ፡- ይህ አይነት የጀነቲክ መዛባት ፅንስ ከመፈጠሩ በፊት መታወቅ ይችላል። ጤናማ የልሆኑ ጂኖች ከእናት እንቁላል እና ከአባት የዘር ፍሬ ወይም ስፐርም ይወረሳሉ። የዘረመል መዛባት ያለበት ሰው ጂኖቹን ለተዋረድ ዘሮቹ ሊያስተላለፍ ይችላል። BRCA የሚባለው ሚውቴሽን የጡት ካንሰርን የመያዝ እድላችን ከ 60% በላይ እንዲሁም የማህፀን ካንሰርን ከ 50% በላይ ከፍ ያደርገዋል። ይሁን እንጂ BRCA ጂኖች ላይ የሚከሰት ሚውቴሽን የቻይና ዝርያ ካላቸው ላይ እምብዛም አይከሰቱም። ከነሱ መካከል የሚከሰተው ከ 5% ያነሰ ነው። በሌላ በኩል ከ80% በላይ የሚሆኑት የአይሁድ ዝርያ ያላቸው የBRCA ጂን ሚውቴሽን አላቸው። የጀርምላይን ሚውቴሽን ያለባቸው ሰዎች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ካንሰር ይያዛሉ። ለምሳሌ የጡት ካንሰር በአብዛኛው ከ45 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ይገከሰታል ይሁን እንጂ ጀርምላይን ሚውቴሽን ያለባቸው ሰዎች በ20ዎቹ እና 30 ዎቹ ውስጥ እያሉ በተመሳሳይ ካንሰር የመያዝ እድል አላቸው። ካንሰሩ በሁለቱም ጡቶች ላይ የመከሰት አዝማሚያ ያለው ሲሆን ሌሎች የካንሰር አይነቶችም የመፈጠር እድል ይኖራቸዋል እንዲሁም ብዙ የቤተሰቡ አባላትም ችግሩ ሊኖርባቸው ይችላል። 

ሶማቲክ ሚውቴሽን (Somatic mutation) ፡- ይህ አይነት የዘረመል ሚውቴሽን የሚከሰተው ፅንሱ ከተፈጠረ በኋላ ነው። ሚውቴሽኑ ውጫዊ በሆኑ እንደ ኤክስሬይ ጨረር፣ ማጨስ እና ለአንዳንድ ኬሚካሎች ባለን ተጋላጭነት ምክንያት ሊከሰት ይችላል። እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ጂኖችን እንዲጎዱ እና በፊት ከነበራቸው አወቃቀር እንዲቀየሩ ሊያደርጋቸው ይችላል። ወይም ከተለመደ የሰውነት ህዋሶች እራሳቸውን በማባዛት ሰውነታቸውን ለመጠገን ከሚደረገው መባዛት በተለየ ከቁጥጥር ውጭ እንዲባዙ እና የካንሰር ጂኖች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ። ሶማቲክ ሚውቴሽን በብዙ ሰዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን የሰዎች እድሜ እየገፋ ሲሄድ የመታየት አዝማሚያ አላቸው። ጤናማ ያልሆኑ ጂኖቹ ግን ከቤተሰቦች ወደ ልጆቻቸው ወይም ለነሱ የተዋረድ ዘሮች አይተላለፉም። 

የጄኔቲክ ካንሰር ምርመራ በሰውነት ውስጥ ካሉ ብዙ ካንሰራማ ጂኖች መካከል በወሊድ ጊዜ ከወላጅ ወደ ልጅ በመተላለፍ የሚከሰትን የካንሰር ተጋለጭነት እድል ቀድሞ ለመገመት የሚደረግ ምርመራ ነው። ምርመራው በደም ምርመራ፣ በምራቅ ወይም አፍ ላይ ካሉ ሴሎች ላይ በተወሰደ ናሙና ሊከናወን ይችላል። ይሁን እንጂ የደም ምርመራ ከሌሎች በተሻለ ትክክለኛ እና በጣም አስተማማኝ ነው። የጄኔቲክ ካንሰር ስጋት ከሌለብዎት ጤናዎትን መጠበቅ አሁን ባለው እድሜዎት ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ነገር ግን ሌሎች ለካንሰር ሊያጋልጡን የሚችሉ ምክንያቶችን ለምሳሌ ምግብን እንዳይበላሽ ማቆያዎች የተጨመሩባቸውን ምግቦችን መመገብ፣ የተጠበሱ ወይም ጣዕማቸውን ለመጨመር በተለየ ጭስ ውስጥ ሆነው የበሰሉ ስጋዎችን መመገብ፣ አዘውትሮ አልኮል መጠጣት ወይም ሲጋራ ማጨስ፣ እንዲሁም ለኬሚካሎች አዘውትሮ መጋለጥ እና የመሳሰሉትን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች በጄኔቲክ ለውጥ ምክንያት ከሚኖረን ተጋላጭነት ይልቅ ለካንሰር የማጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።

ችግሩ እንዳለ ከታወቀ ምርመራው የአኗኗር ዘይቤያችን ለመለወጥ ይረዳናል ወይም ካንሰር ከመፈጠሩ በፊት የቀዶ ጥገና ህክምናን አስፈላጊነት ለመወሰን ይረዳል። ለአንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች የመጋለጥ እድልን የሚቀንሱ መድሃኒቶች ለመውሰድ፣ በአካባቢያችን ያሉ ችግሩን ሊያባብሱ ወይም ተጋላጭነትን ለጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን ለማስወገድ እንዲሁም አንዳንድ ጎጂ ልምዶቻችን ለመቀየር ይረዳል። ለምሳሌ የBRCA ጂን ሚውቴሽን መኖሩ ሲታወቅ ሁለቱንም ጡቶች በቀዶ ጥገና በማስወገድ እና በሰው ሠራሽ መተካት የጡት ካንሰርን የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል። ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ሰዎች በዘር ለሚተላለፍ ሚውቴሽን የሚደረግ የዘረመል ካንሰር ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል። 

• ከአሁን በፊት በካንሰር ተይዘው የሚያውቁ ወይም ከ50 አመት በታች እድሜ ላይ እያለ ካንሰር ተይዞ የሚያውቅ የቤተሰቡ አባል ከነበረ 

• በቤተሰብ ውስጥ በዘር የሚተላለፍ የካንሰር ጂን እንዳለ ከታወቀ 

• በጡት ካንሰር የተያዙ ወንዶች 

• ብዙ አይነት የካንሰር በሽታዎች ያሉበት ሰው 

• በዘር ለሚተላለፍ ካንሰር ሊኖረው የሚችለውን ተጋላጭነት ማወቅ ለሚፈልግ ሰው 

• የቤተሰብ እቅድ ለማቀድ ለሚፈልጉ እና ልጅ ለመውለድ እየተዘጋጁ ላሉ ሰወች 

በካንሰር እንደተያዙ ለተረጋገጠ ታካሚዎች የጄኔቲክ ካንሰር ምርመራው የሚደረገው በቲሹ ባዮፕሲ ወይም በፈሳሽ ባዮፕሲ ናሙና በመውሰድ ይሆናል። ፈሳሽ ባዮፕሲ ከተለያዩ የአካል ክፍሎቻችን የመጡ በደም ውስጥ የሚገኙ የካንሰር ሕዋሳትን ለመለየት የሚደረግ ምርመራ ነው። አሁን ላይ በጄኔቲክስ ምርመራ ቴክኖሎጂዎች እድገት ምክንያት አንድ ጂን ላይ ያተኮረ ምርመራ (single gene testing) ማድረግ ከአሁን በኋላ አያስፈልግም። ነጠላ የጂን ምርመራ (single gene testing) የሚካሄደው ጤናማ ያልሆነው ጂን እስኪገኝ ድረስ እያንዳንዱን ጂን በአንድ ጊዜ የሚመረመርበት ሂደት ነው። አንዳንድ ጊዜ ለሙከራ የሚሆን በቂ ናሙና ላይኖር ስለሚችል በድጋሜ ከታካሚው ተጨማሪ ቲሹዎች እንዲወሰዱ ይደረጋል። ይህ ሂደት የህክምናውን እቅድ ለማውጣት በሚደረገው የመረጃ መሰብሰብ ሂደት እጅግ ብዙ ጊዜ እንዲወሰድ ያደርገዋል። በአሁኑ ጊዜ ከ500 በላይ ጂኖች በአንድ ጊዜ ሊመረመሩ የሚችሉበት Multigene Panel Testing (NGS) አለን። ይህ ሂደት ቲሹ ናሙናዎችን ወደ ብዙ ክፍሎች የመከፋፈል ሂደትን ያስወግዳል እንዲሁም ለምርመራ የሚወሰደውን ጊዜ ይቀንሳል። የ Multigene Panel Testing ዶክተሩ ምርመራውን በትክክል ገምግሞ ትክክለኛ የሕክምና ዕቅድ ማውጣት እንዲችል እና ለታርጌትድ ቴራፒ መድሃኒቶች በሽታው የሚሰጠውን ምላሽ መገምገም እንዲችል ያግዘዋል። ባጠቃላይ የመልቲጂን ፓነል ምርመራ በወሊድ ጊዜ ወይም ከተወለዱ በኋላ በዘር የሚተላለፍ ካንሰርን ጨምሮ ሁሉንም የካንሰር አይነቶች ለመመርመር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። 

“የካንሰር ቅድመ መከላከል እና ህክምና መዘመን ታካሚዎች በጣም ውጤታማ እና ትክክለኛ ህክምና እንዲያገኙ ብሎም በሰውነት ውስጥ ያሉ ጤነኛ ሴሎችን ሳይጎዱ እና በካንሰር ህክምናው የጎንዮሽ ጉዳት ሳይደርስባቸው ህክምና ማድረግ እንዲችሉ አስችሏል። በቤተሰብ ውስጥ የካንሰር ታሪክ የነበረባቸው እና ሊኖራቸው የሚችለውን በካንሰር የመያዝ እድል ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች ከዘረመል ምርመራ በኋላ ምንም አይነት ችግር ካልተገኘ ስጋታቸው ይቀረፍላቸዋል። ይሁን እንጂ ችግሩ ከተገኘም ቀድሞ ስለሚታወቅ ለወደፊቱ እቅድ ለማውጣት ይረዳል ሲሉ Dr. Natchadol ያብራራሉ።ለበለጠ መረጃ በቬጂታኒ ሆስፒታል የሚገኘውን የቬጂታኒ ካንሰር ማዕከልን (Life Cancer  Center) ይጎብኙ። ስልክ ቁጥር 02-734-0000 Ext. 272 የኢትዮጵያ ደንበኞች አገልግሎት ቁጥር፦(+66)9-090-72560

  • Readers Rating
  • Rated 2.3 stars
    2.3 / 5 (5 )
  • Your Rating