የጤና መረጃዎች

የካንሰር ክትባት ተስፋዎችን ወደ ደረጃ -4 የካንሰር ታማሚዎች ማምጣት

Share:

በተለምዶ ሰውነታችን ነጭ የደም ሴሎች ያሉት ሲሆን ይህም የውጭ ሴሎችን የሚያጠፋው የበሽታ መከላከያ አካል ነው። ለምሳሌ የታመሙ ሴሎች፣ የባክቴሪያ ሴሎች እና የቫይረስ ሴሎች። ይሁን እንጂ አንዳንድ የካንሰር ሕዋሳት በነጭ የደም ሴሎች እንዳይወድሙ የሚከላከሉበት ዘዴ አላቸው። ስለዚህ ኢሚውኖ ቴራፒ (Immunotherapy) ህክምና ካንሰርን ለማከም ያንን ዘዴ በመግታት እና የሰውነትን ወይም የነጭ የደም ሴሎችን በሽታ የመከላከል ስርዓት በማሳደግ የካንሰር ሕዋሳትን ለመዋጋት አስችሏል።

የበሽታ መከላከያ መድሐኒቶች ቢሰጡም ነጭ የደም ሴሎች የካንሰር ሕዋሳትን ካላወቁ የካንሰር ሕዋሳትን የማጥፋት ተግባራቸውን ማከናወን አይችሉም። የካንሰር ክትባት ካንሰርን በማከም ረገድ የበለጠ ወሳኝ ሚና መጫወት የመጣው እዚህ ላይ ነው

ከታካሚ እጢ (tumor) የተገኙ የካንሰር ፕሮቲኖች የሚወጡት ግላዊ የሆነ የካንሰር ክትባት ለማምረት ነው። የካንሰር ክትባት ነጭ የደም ሴሎች የታካሚዎችን የካንሰር ሕዋሳትን ለይተው እንዲያውቁ እና ለማጥፋት ዝግጁ እንዲሆኑ ለማበረታታት ይረዳል። የካንሰር ክትባት ከኢሚውኖቴራፒ ጋር በጥምረት ጥቅም ላይ ሲውል ነጭ የደም ሴሎችን የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲሠሩ ያደርጋል።

ለጥያቄዎች፣ ወይም ቀጠሮ ለመያዝ በሚከተሉት አድራሻዎች መልዕክት ይላኩልን ወይም ይደውሉልን፣ የአማርኛ የስልክ መስመር በ +66 (0) 90-907-2560 ወይም ኢሜል [email protected]

  • Readers Rating
  • Rated 4.5 stars
    4.5 / 5 (1 )
  • Your Rating