የጤና መረጃዎች

የአንጎል ውስጥ ደም ዝውውር በሽታ (Cerebrovascular disease or Stroke) ያለባቸው ታካሚዎች በሮቦት በታገዘ ሪሃብሊቴሽን ማገገም ይችላሉ

Share:

በሮቦት በሚታገዘ የእርምጃ ሥልጠና የአንጎል ውስጥ ደም ዝውውር በሽታ (cerebrovascular disease or stroke) ላለባቸው ሕመምተኞች ችግሩ ሳይገድባቸው የተሻለ ቀጣይ ህይወት እንዲኖራቸው ያስችላል።

Ischemic stroke የታይላንድ ዜጎች ላይ በብዛት ይገኛል። ሕመሙ በሁለት ዓይነት ይከፈላል፦ thrombotic stroke ይህም በደም ሥሮች ውስጥ ስብ እና ኮሌስትሮል በመከማቸቱ ምክንያት የደም ወሳጅ ቧንቧዎች መጥበብ እና በመጨረሻም የደም ፍሰት ይቀንሳል። embolic stroke የሚከሰተው የረጋው ደም ከማንኛውም የሰውነት ክፍል ተሰባብሮ ወደ አንጎል ተጉዞ የደም ወሳጅ ቧንቧ ሲዘጋ ነው። እንዲሁም የደም መርጋቱ ሲጨምርና ያነን ተከትሎ ወደ አንጎል የሚሄደውን የደም ቧንቧ በመዘጋቱ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። cerebral aneurysm ይህ ደግም የሚከሰተው ደካማ የደም ሥሮች ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር ሲጣመሩ የደም ወሳጅ ግድግዳ መወጠር እና መፈንዳትን ያስከትላል ወይም ደግሞ በደም ሥሮች ውስጥ በሚገኙ ቅባቶች ክምችት ምክንያት የደም ሥሮችን መፈንዳት ሊያስከትል የሚችልበት አጋጣሚያ አለ።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የፊዚካል ሜዲስን እና የሪሃብሊቴሽን ስፔሻሊስት የሆኑት Dr. Pheeravut Tantisuvanitchkul እንደሚሉት የአንጎል ውስጥ ደም ዝውውር (cerebrovascular) ሕመም ያለባቸው በሽተኞች ወደ አንጎላቸው የሚሄደውን የደም ፍሰት እንንዲቋረጥ ስለሚያደርግ የነርቭ ሥርዓታቸውን ተግባራ ወደ ማጣት ያመራቸዋል። ለምሳሌ ግማሽ አካላችን ወይም ፊታችን ላይ እንዲሁም እግሮቻችን እና እጆቻችን ላይ መደንዘዝ ወይም ድክመት፣ የንግግር መጎተት፣ የፊት መውረድ፣ dysphagia ወይም የመዋጥ ችግር፣ ድንገተኛ ራስ ምታት ወይም ማዞር፣ የእይታ ብዥታ፣ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የእይታ መጥፋት፣ አንደኛው ዐይን በድንገት መታወር እና የሚዛን መሳት በስትሮክ ህመምተኞች ውስጥ ከሚከሰቱ ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ናቸው። ማንኛውም ያልተለመደ ሁኔታ ከተከሰተ ሕመምተኞች አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ማግኘት አለባቸው ምክንያቱም ስትሮክ ከባድ እና ለሕይወት አስጊ የሆነ በሽታ ሲሆን ወደ paresis፣ ሽባነት ወይም መንቀሳቀስን ወደ ማሳጣት ሊያመራ ይችላል።

“ብዙ ችግሮችን ያለፉ ነገር ግን አሁንም ድረስ ፓራላይዝ የሆኑ አብዛኛዎች የስትሮክ ሕመምተኞች በመጀመሪያዎቹ ከ3-6 ባሉት ወራት ሙሉ በሙሉ የማገገሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ህመምተኞችን ወደ መደበኛው ህይወታቸው እንዲመለሱ የሚያስችላቸው ወርቃማ ጊዜ ተደርጎ ይቆጠራል። ስለሆነም የአንጎል ውስጥ ደም ዝውውር (cerebrovascular) ህመምተኞች ትክክለኛ፣ አግባብነት ያለው እና ጊዜውን የጠበቀ የማገገሚያ ክትትል ማግኘትታቸው በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ በአካልም ሆነ በአእምሮ ደህንነት ረገድ በተቻለ መጠን ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ያስችላቸዋል ሲሉ Dr. Pheeravut ያብራራሉ።

በቬጅታኒ ሆስፒታል ዘመናው የሪሀብሊቴሽን ማዕከል የፊዚካል ቴራፒ እና የሪሃብሊቴሽን ህክምናን ውጤታማነት ለማሳደግ በሮቦት የታገዘ የአንጎል ውስጥ ደም ዝውውር በሽታ (cerebrovascular disease or stroke) ለሚሠቃዩ ሕመምተኞች የሚጠቅም የእርምጃ (gait) ሥልጠና መስጫ ቴክኖሎጂዎችን አስተዋውቋል።

ማዕከሉ በየአንጎል ውስጥ ደም ዝውውር በሽታ (cerebrovascular disease or stroke) ምክንያት የሰውነታቸውን ሚዛን የመጠበቅ እና የመራመድ እክል ያለባቸውን በሽተኞች ከችግሩ ለመመለስ የተሰራ Lokomat የተባለ በሮቦት የሚታገዝ የእግር ጉዞ ሥልጠና መስጫ መሣሪያን አለው። ሮቦቱ የሰውነት አካሎች በተፈጥሮ እንዳለው ሆነው እንዲንቀሳቀሱ በጉልበቶች እና ዳሌ ዙሪያ ድጋፍ ይሰጣል። ታካሚዎች ዘና እያሉ እንዲሰሩ የተለያዩ የጨዋታ ዓይነቶች በሥልጠናው ውስጥ ተካትተዋል። ይህም በስልጠናው ወቅት እያከናወኑ ያሉትን ለውጥ እዘያው ላይ እንዲያዩና በሪሃብሊቴሽን ፕሮግራሙ እንዲቀጥሉ ያበረታታል።

C-Mill ተግባባራዊ የእርምጃ እና የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ ስልጠና ማሽን በእውነተኛ ምናባዊ ኢንቫይሮሜንት ውስጥ የተጎዳ የእግር እንቅስቃሴን ወደነበረበት ለመመለስ የሚረዳ ሮቦት ነው። ለምሳሌ በተለያዩ ቦታዎች መራመድ እንዲሁም ታካሚዎች በእውነተኛ የህይወት እንቅስቃሴዎች ላይ ዝግጁ እንዲሆኑ መሰናክሎችን የማስወገድ ስልጠና። ማሽኑ የሰውነት ሚዛንን የመጠበቅ እና የመራመድን ስልጠናን ያቀላጥፋል እንዲሁም ለእያንዳንዱ በሽተኛ ተስማሚ በሆነ አነቃቂ ኢንቫይሮመንት ውስጥ በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ቨርቹዋል ጌሞች ላይ በማሰልጠን የእግር ጉዞ ፍጥነትን ያስተካክላል። ይህ መደረጉ አሰልቺ እንዳይሆንና በስልጠና ወቅት የሚፈጠረውን ጫና እና ጭንቀቱት ይቀንሳል። በተጨማሪም ግባቸውን ለማሳካት በፕሮግራሙ እንዲቀጥሉ ያነሳሳቸዋል። ይህ ቴክኒክ ነገሮችን አይቶ የመለየት፣ ተግባር-ተኮር ክህሎት የሚፈልጉ እንቅስቃሴዎችን ለማከናዎን፣ የተወሳሰቡ ተግባራትን ለማከናዎን እና ሥራችን በምንመራበት ወቅት ለሚኖረን የውሳኔ አሰጣጥ ችሎታ የሚኖረንን ትኩረት ያሻሽላል።

KEEOGO ህመምተኞች በልበ ሙሉነት እንዲራመዱ እና ረዥም ርቀት እንዲጓዙ የሚያስችል ስማርት ፓወር  ኦርቶሲስ የእግር ጉዞ ድጋፍ ሰጪ መሣሪያ ነው። የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ ካለመቻል እና የጡንቻ ድክመት ወይም ህመም ጋር ተያይዞ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ውስጥ የሚገጥሟቸውን ውስንነቶች እንዲያሸንፉና ራሳቸውን ችለው እንዲንቀሳቀሱ ያስችላቸዋል። ህመምተኞቹ ረዘም ላለ ጊዜ እና ርቀት መራመድ እንዲችሉ ያስችላቸዋል። ማሽኑ ደረጃ መውጣት እና መውረድ እንዲችሉ፣ ወጣ ገባ በሆነ መሬት ላይ መራመድ እንዲችሉ፣ ቁጭ ብድግ መስራት እና በቀላሉ ከወለል ላይ መነሳት እንዲችሉ ይረዳቸዋል።

የሪሃብሊቴሽን ፕሮግራሞች በባለሙያዎች የተነደፉና ለእያንዳንዱ ህመምተኞች ከፍላጎቶቻቸው ጋር እንዲስማሙ ሆነው የታቀዱ ናቸው። በዋናነት በስልጠናው ወቅት እንደ ታካሚው ክሊኒካል ሁኔታ የሪሃብሊቴሽን ፕሮግራሞች የሚስተካከሉ ሲሆን ይህም አጥጋቢ የሕክምና ውጤቶች እንዲመጣ እና በተቻለ መጠን ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ የሚረዳቸው እንዲሁም ጥሩ ቀጣይ ህይወት እንዲኖራቸው የሚያግዝ ፕሮግራም ነው።

  • Readers Rating
  • Rated 4.5 stars
    4.5 / 5 (3 )
  • Your Rating