የጤና መረጃዎች

ስለ ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ – How well do you know about cancer?

Share:

ካንሰር (Cancer) በሰው አካል ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ እና ባልተለመደ የሕዋሳት መባዛት ምክንያት የሚከሰት በሽታ ሲሆን በመጨረሻም የካንሰር እጢ ይፈጥራል (Cancer Tumor)፡፡ ካንሰር ከተጠቃው የአካል ክፍል በመነሳት በአቅራቢያው ወዳሉ የአካል ክፍሎች ወይም ወደሌሎች የአካል ክፍሎች ካንሰሩ እንደ ጀመረበት ቦታና እንደ ካንሰር አይነቱ የሚወሰን ቢሆንም በደም ዝውውር እና በሊንፋቲክ ስርዓት ውስጥ ሊሰራጭ ይችላል፡፡

የካንሰርዓይነቶች – Types of Cancer:

  1. ካርሲኖማ፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው ከሰውነታችን አካላት ላይ ነው
  2. ሳርኮማ፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው ከሕብረ ሕዋሶች (tissues) ነው
  3. የደም ካንሰር (ሉኬሚያ)፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው በአጥንት መቅኒ ውስጥ ካሉ የደም ህዋሳት ነው
  4. ሊምፎማ እና ማይሎማ፦ ይህ የካንሰር አይነት ከሊምፍ ኖድ እና የበሽታ መከላከያ ስርዓት (immune system) የሚመነጭ ነው
  5. የማዕከላዊ ሥርዓተ ነርቭ ካንሰር፦ ይህ ዓይነቱ ካንሰር የሚመነጨው ከአንጎል እና ከአከርካሪ አጥንት መቅኒ ነው

ለካንሰርየሚያጋልጡየተለመዱምክንያቶች – Common Causes of Cancer:

  1. እርጅና
  2. ሲጋራ ማጨስ
  3. ለፀሐይ ብርሃን ወይም አልትራቫዮሌት ጨረር መጋለጥ
  4. ለጨረር መጋለጥ
  5. አልኮሆል መጠጥ
  6. ለኬሚካል መጋለጥ
  7. ቫይረሶች እና ባክቴሪያዎች
  8. የኢስትሮጅን ሆርሞን መዛባት
  9. ዘረመል
  10. የለችግሩ አጋላጭ ባህሪያት (ለምሳሌ ጤናማ ያልሆነ አበጋገብ፣ በቂ ያልሆነ እንቅልፍ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እጥረት፣ ጭንቀት፣ ወዘተ)

ለበለጠመረጃበቬጂታኒሆስፒታልየካንሰርማዕከል (Life Cancer Center) በስልክቁጥር + 66 (0) 2-734-0000 Ext. 4500, 4501 ወይም +66 (0) 90-907-2560 (የአማርኛመስመር) ያነጋግሩ.

  • Readers Rating
  • Rated 2.6 stars
    2.6 / 5 (7 )
  • Your Rating