የጤና መረጃዎች

የታችኛው የጀርባ አጥንት ላይ ህመም የሚያስከትለው የጀርባ አጥንት ችግር (Spondylolisthesis) በ Oblique Lumbar Interbody Fusion (OLIF) ሊታከም ይችላል

Share:

በሚራመዱበት ወቅት የሚቸገሩ ከሆነ እዲሁም ወደ እግሮች የሚዘልቅ ከባድ የጀርባ ህመም የSpondylolisthesis ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ Spondylolisthesis በሁሉም ዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል ነገር ግን ይህ ሁኔታ በቋሚነት በ Oblique Lumbar Interbody Fusion (OLIF) የቀዶ ጥገና ዘዴ ሊታከም ይችላል። ከቀዶ ጥገናው በኋላ ከ12 – 24 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ ታካሚዎቹ በእግራቸው መጓዝ ይችላሉ፡፡

በሌሎች የአከርካሪ አጥንት ችግሮች እንደሚከሰተው ሁሉ Spondylolisthesis ከባድ ህመም የሚያስከትል የአከርካሪ ህመም ነው፡፡ አረጋውያንም ሆኑ ጎልማሶች የችግሩ ሰለባ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

Spondylolisthesis ያለባቸው ታካሚዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶች አሏቸው ፣ ጀርባቸውን ሲያጎነብሱ ወይም ወገባቸውን ሲያጥፉ ወደ እግሮቻቸው የሚወርድና በአንዱ ወይም በሁለቱም እግሮች ላይ የመደንዘዝ ስሜት ይታይባቸዋል፡፡ ከእነዚህ ምልክቶች በተጨማሪ Spondylolisthesis በታችኛው ጀርባ ላይ ጭምድድ አድርጎ  የመያዝ ወይም ድርቅ የማለት ምልክት ያስከትላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች ምልክቶች ማለትም የእግር ጡንቻዎች መዛል ያስከትላል ከዚህ ጋር በተያያዘ ለመራመድ መቸገር ወይም በእግር ረዥም ርቀት ለመጓዝ ያለመቻል ችግሮችን ያስከትላል፡፡ እነዚህ ምልክቶች በታካሚው የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ፣ ከፍተኛ ሥቃይ የሚያስከትሉና ከ2 ሳምንታት በላይ የሚቆዩ ናቸው፡፡

በቬጅታኒ ሆስፒታል በአከርካሪ ቀዶ ጥገና ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ስፔሺያሊስቶች ውስጥ አንዱ የሆኑት Dr. Chaiyos Chaichankul እንደተናገሩት Spondylolisthesis የሚከሰተው የአከርካሪ ዲስኮች (ኢንተር-ቬርቴብራል ዲስኮች) ሲፈነዱ ወይም ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸውና በዲስኮቹ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሲፈስ ወይም ከቦታው ተንሸራትቶ ነርቩን በሚጫንበት ወቅት ነው፡፡ የአከርካሪ ዲስኮች በእያንዳንዱ አከርካሪ አጥንት መካከል ይገኛሉ፡፡ ዲስኮች ሃይልን በማመቅ በአከርካሪው በኩል የሚያልፈውን ጫና ለመቀነስ እና እንድንቀሳቀስ የሚረዱን ከጄሊ መሰል ንጥረነገሮች የተሰሩ ናቸው፡፡ አከርካሪ በጣም ከፍተኛ ጫና በሚደርስበት ወቅት ወይም በሚጎዳበት ጊዜ በአከርካሪ አጥንት መካከል የሚገኙ ዲስኮች በቀላሉ ሊጎዱ ወይም ሊቀደዱ ይችላሉ፡፡

Spondylolisthesis ሁለት ዋና ምክንያቶች አሉት። የመጀመሪያው ብዙውን ጊዜ በአረጋውያን ላይ ይከሰታል ፣ በብዛት በህብለ ሰረሰር ማርጀት ምክንያት በተለይም በአከርካሪዎች መገጣጠሚያ እና ዲስኮች ውስጥ ይከሰታል ይህም አከርካሪ ላይ መዛባት ያስከትላል፣ ይህን ተከትሎ አከርካሪዎቹ ከቦታቸው እንዲንሸራተቱ እና ነርቮቹን እንዲጭኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ሁለተኛው በወጣቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን በዋናነት ከውልደት ጀምሮ ሰረሰርና ህብለ ሰረሰር ላይ የአፈጣጠር ችግር ሲኖር (Spina Bifida) የሚከሰት ችግር ነው፣ ከውልደት ጀምሮ ወይም በከባድ የአከርካሪ ጉዳት ምክንያት የሚከሰት የአከርካሪ አጥንት ችግር ነው፡፡ ይሁን እንጂ የአኗኗር ሁኔታም እንዲሁ Spondylolisthesis እንዲፈጠር ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ከመጠን ያለፈ ክብደት፣ ከባድ ነገሮችን አዘውትሮ ማንሳት፣ ልክ ያልሆነ አቀማመጥ፣ ድንገተኛ ልክ ያልሆነ የሰውነት እንቅስቃሴ፣ እና አከርካሪያችን ላይ በቀጥታ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ከባድ ስፖርቶችን መስራት፡፡ Dr. Chaiyos እንዳሉት እነዚህ ምክንያቶች ከSpondylolisthesis በስተጀርባ ያሉ ችግሩን የሚያባብሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡

Spondylolisthesis የሚደረግ ምርመራ እና ሕክምና ሐኪሙ የችግሩን መንስኤ ለማዎቅ ያለፈ የታካሚውን ታሪክ በመጠየቅ ይጀምራል፣ ከዛም አካላዊ ምርመራ እና የበሽታውን ክብደት ለማዎቅ የራጅ እና ኤምአርአይ (MRI) ምርመራዎችን ያደርጋል፡፡ ችግሩ ቀለል ያለ ከሆነ ሐኪሙ መድሃኒትና ከ6 – 8 ለሚሆን ተከታታይ ሳምንታት የሚደረግ ፊዚዮቴራፒ በማቀናጀት በሽተኛውን ያክማል፡፡ ይሁን እንጂ ምልክቶቹ ካልተሻሻሉ ወይም በታካሚው የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድር መጠን ከባድ ከሆኑ ሐኪሙ ዲስክን የመተካት ቀዶ ጥገና እንዲደረግ ይመክራል፡፡ ምናልባት በሽተኛው የአከርካሪ አጥንት መዛባት ወይም መጣመም (ስኮሊዎሲስ) ካለበት ሐኪሙ Oblique Lumbar Interbody Fusion (OLIF) የተባለውን ሰውነት ላይ ብዙም መቀደድ የማያስፈልገውን (minimally invasive surgery) አከርካሪን የመጠገን (spinal fusion) ቀዶ ጥገና እንደ አማራጭ ሊወስድ ይችላል። አሰራሩ የተጎዳውን ዲስክ በሰው ሰራሽ ዲስክ ለመተካት በጎን በኩል ትንሽ መቅደድ የሚያስፈልገው እና የአከርካሪ ቅርፅ እና የነርቭ ጫናውን ወደነበረበት ለመመለስ ዲስክ በሚተካበት ወቅት ሰረሰርን ለማስተካከል የሚያገለግል አያያዥ መሳሪያ (lumbar fusion peek cages) ይጠቀማል። ይህ አይነቱ የቀዶ ጥገና ዘዴ ትንሽ መሰንጠቅ ብቻ ያስከትላል እንዲሁም በአቅራቢያው ባሉ ሕብረ ሕዋሳት እና ጡንቻዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት፣ የደም መፍሰስን፣ እንዲሁም ተያያዥ ችግሮችንና የነርቭ ጉዳትን ይቀንሳል። በተጨማሪም ከቀዶ ጥገና በኋላ በነርቭ ላይ የሚከሰት የስጋ ሽፋን የመከሰት እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ህመምተኛው ከቀዶ ጥገናው በኋላ ከ12 – 24 ሰዓታት ባለ ጊዜ ውስጥ በእግሩ መራመድ ይችላል። ሌላኛው ከሁሉም በላይ ጠቃሚው ነገር ደግሞ ለማገገሚያ የሚወስደው ጊዜ በሆስፒታሉ ውስጥ 1 ሌሊት መተኛት ብቻ መሆኑ ነው፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 2.6 stars
    2.6 / 5 (6 )
  • Your Rating

Related Posts