የጤና መረጃዎች

“ቀይ ሥጋ – በፋብሪካ የተቀናበሩ ምግቦች” የአንጀት ካንሰር (Colorectal cancer) ተጋላጭነትን ይጨምራሉ

Share:

ምን ያህሎቻችን በዕለት ተዕለት ምግባችን ውስጥ ለኮሎሬክታል ካንሰር አጋላጭ ነገሮችን አብረን እንደምንጠቀም  እናውቃለን በተለይ ደግሞ ቀይ ሥጋ እና የተቀነባበሩ ምግቦችን ስንጠቀም? ለምንበላው ምግብ በቂ ትኩረት ሳንሰጥ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንቀጥላለን፡፡ በዋናነት ተጋላጭነትን የሚጨምሩ የተቀነባበሩ ምግቦች Nitrosamine የተባለ ውህድ ይይዛሉ ይህ የኬሚካል ውህድ በሰው አካል ውስጥ ሲከማች የካንሰር ህዋስ የመፍጠር አቅም ያላቸው ውህዶችን ይፈጥራል እንዲሁም ውስጣዊ አካላት ላይ ከሌሎች አስተዋፅኦ ያላቸው ነገሮች ጋር ኬሚካል ሪያክሽን ይፈጥራል።

እንደ BBQ እና የኮሪያ ኩዚን ያሉ የቡፌ አይነት ምግቦች በአሁኑ ጊዜ በሰዎች ዘንድ በሰፊው ተወዳጅ እና በከፍተኛ ሁኔታ የደንበኞች ምርጫ ሆነዋል፡፡ ይሁን እንጂ ቀይ ሥጋን በመብላት የሚከሰተው ጉዳት የአሳማ ስጋ ይሁን፣ የበሬ፣ የበግ ወይም የፍየል ሥጋ በከፍተኛ ሙቀት ሲበስሉ፣ በጣም ሲጠበሱ ወይም ሲቀቀሉ በብዙዎቻችን ዘንድ ችላ ሲባል ይስተዋላል፡፡ ምግብ በጣም በከፍተኛ ሙቀት በሚበስልበት ጊዜ አንዳንድ ኬሚካሎች የሚመነጩ ሲሆን እነዚህም በአንጀት ውስጥ ያሉትን ህዋሳት ይጎዳሉ ለወደፊትም በአንጀት ካንሰር የመያዝ እድልን የበለጠ ይጨምራሉ፡፡ ቀይ ሥጋን በከፍተኛ ሙቀት ማዘጋጀት Polycylic Aromatic Hydrocarbons (PAHs) እና Heterocyclic Aromatic Amines የተባሉ ንጥረነገሮች እንዲፈጠሩ ያደርጋል እነዚህ ሁለቱ ካንሰር አምጭ ውህዶች ሲሆኑ ለኮሎሬክታል ካንሰር ያጋልጣሉ፡፡

የአንጀት ካንሰር (Colorectal Cancer) ተጋላጭነት እያንዳንዱ ሰው እንደሚወስደው የቀይ ሥጋ መጠን ሁሉ ይለያያል፡፡ በቀን 100 ግራም ቀይ ሥጋ መመገብ በኮሎረክታል ካንሰር የመያዝ እድልን በ17% እንደሚያሳድግ የተረጋገጠ ሲሆን በቀን 50 ግራም የተቀነባበረ ምግብ መመገብ አደጋውን በ18% የበለጠ እንደሚያፋጥነው ታውቋል፡፡

ስለዚህ የተጠበሱ እና BBQ ምግቦች ብቻ የኮሎሬክታል ካንሰር መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ መገመትን ሙሉ በሙሉ ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡ በተለያዩ የምግብ አዘገጃጀት ዘዴዎች የተዘጋጀ ቀይ ሥጋ እና የተቀነባበረ ስጋ መጠቀም የችግሩ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡

በቬጂታኒ ሆስፒታል የኮሎሬክታል ቀዶ ጥገና ሃኪም Dr. Sukit Pattarajierapan በቀን ውስጥ እንድንጠቀም የሚመከረው የቀይ ስጋ እና የተቀነባበሩ ምግቦች መጠን ከ50-100 ግራም ያህል መሆን አለበት ይላሉ፡፡ ቀይ ሥጋን እና የተቀነባበሩ ምግቦችን ለመተካት እንደ እንቁላል፣ ባቄላ እና ቶፉ ያሉ ሌሎች የፕሮቲን ምንጮችን መጠቀም የተሻለ ነው፡፡ በተጨማሪም በቀን ቢያንስ እስከ 400 ግራም ድረስ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን መመገብ በኮሎሬክታል ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል፡፡

የሆነ ሆኖ የቀይ ሥጋን እና የተቀነባበረ ስጋን የመመገብ ልማድ እኛ ልናስወግደው የማንችለው የአኗኗራችን አካል ስለ ሆነ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም አጋላጭ የሆነ የአመጋገብ ባህሪ ያላቸው እና ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች በአንጀት እና ሬክተም ውስጥ የፖሊፕ መኖር ወይም ለውጦች ካሉ ለማየት፣ ያልተለመዱ ነገሮች ወይም አዳዲስ ክስተቶችን ለማዎቅ የኮሎኖስኮፒ ምርመራን እንዲያደርጉ በጥብቅ ይመከራል፡፡ ፖሊፕስ (በአንጀት ውስጥ የሚከሰቱ እባጮች)ለወደፊቱ ወደ ኮሎሬክታል ካንሰር የመቀየር እድል አላቸው፡፡ ዘመኑ ካፈራቸው ቴክኖሎጂዎች ኮሎኖስኮፒን በመጠቀም የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ከ2 ሚሊ ሜትር በታች መጠን ያላቸው ቢሆኑም እንኳን በመጀመሪያው ደረጃ ያሉ ፖሊፕሶችን መለየት ይችላል፡፡ በኮሎኖስኮፒ ሂደቱ ወቅት ፖሊፕ አንጀት ውስጥ ከተገኘ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ የኮሎሬክታል ካንሰር እንዳይከሰት ለመከላከል ወዲያውኑ በጥንቃቄ ፖሊፕሱን ያስወግዳል፡፡

በአንጀት ውስጥ ካንሰራማ የሆነ ፖሊፕ መኖሩ ቀድሞ ለታወቀላቸው ሕመምተኞች ለተወሰኑት በቴክኖሎጂ በመታገዝ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ምንም ውጫዊ ጠባሳ ሳይተዉ የላፓራስኮቲክ ቀዶ ሕክምና በማድረግ ታካሚዎችን ማከም ይችላል፡፡ በተጨማሪም ይህ የህክምና ዘዴ ውስብስብ ችግሮች የማጋጠም እድሉ ከከባድ ቀዶ ጥገናዎች ያነሰ እና በቶሎ የማገገም እድል ያለው፣ ህመምተኛው በፍጥነት ወደ ቀደመው ህይወቱ እንዲመለስ የሚያስችል ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ኮሎኖስኮፒ መከናዎን ያለበት በኮሎሬክታል ቀዶ ጥገና ሐኪም ብቻ መሆን አለበት፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (2 )
  • Your Rating