የጤና መረጃዎች

በአመታዊ ምርመራ ጤንነትዎን ያረጋግጡ – Ensure Your Health with Annual Health Checkup

Share:

ዕድሜዎ እየገፋ ሲሄድ ጤናዎ ላይ ለውጥ ይኖራል፡፡ በተለያዩ የሕይወትዎ ደረጃዎች ውስጥ ለተለያዩ በሽታዎች የበለጠ ተጋላጭ ይሆናሉ። እነዚህም በርካታ የካንሰር ዓይነቶችን ፣ የደም ግፊት ፣ የስኳር በሽታ እና የደም ቧንቧ መጥበብ (arteriosclerosis) ችግሮችን ያጠቃልላል። ሁሉም ሰው ዓመታዊ የጤና ምርመራ የማድረግ ልማድ(Annual health checkup) ሊኖረው ይገባል እንዲሁም የራስዎን እና የቤተሰብዎን መልካም ጤንነት ለመጠበቅ ይሄን ተግባር በህይወት ዘመንዎት በቁርጠኝነት ከሚያከናውኗቸው ተግባራት ውስጥ ማካተት አለብዎት።

አብዛኛዎቹ ባንኮክ ውስጥ ያሉ ሆስፒታሎች ዕድሜዎትን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ ዓመታዊ የጤና ምርመራዎችን ያቀርባሉ። እነዚህ ፆታ እና የዕድሜ-ተኮር ዓመታዊ የጤና ምርመራዎች ለእርስዎ የዕድሜ ደረጃ ጤንነትዎ በጣም ጥሩ ከሚባለው ደረጃ ላይ እንዲገኝ ለማድረግ ታቅደው የተዘጋጁ ናቸው (Gender & Age-specific annual health checkups)፡፡ ለታዳጊዎች የሚደረጉ የጤና ምርመራዎች ዋነኛ ትኩረታቸው ዋና ዋና የሰውነት ክፍሎቻቸው በመደበኛነት እንደሚሰሩ የማረጋገጥ፣ ቅድመ መከላከል ህክምናዎች እና ህመምተኞች ምንም አይነት የሚያስጨንቅ ምልክት እንዳያሳዩ ማረጋገጥ ላይ ነው፡፡

ዶክተርዎ በእያንዳንዱ ምርመራ ወቅት የተሟላ በሰውነት ውስጥ ያለ የስብ መጠን (lipid profile) ምርመራ ያካሂዳል። ይህም ጥሩ ኮሌስትሮል (HDL) እና መጥፎ (LDL) ኮሌስትሮልዎን እንዲሁም የትራይግሊሰሪድ ደረጃ የሚመረምር ሲሆን ዕድሜዎ እየገፋ ሲሄድ የስትሮክ ፣ የልብ ህመም እና የደም ቧንቧ መጥበብ ተጋላጭነትዎን ቀድመው ለማወቅ ይረዳል፡፡

የጤና ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ መገኘት – Getting Ahead of Health Problems

ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ከእድሜ ጋር በሚዛመዱ በሽታዎች እና ሁኔታዎች ችግር የሌለብወት ቢሆንም ሐኪሙ ስለ አኗኗር ሁኔታዎ እና ስለቤተሰብዎ የህክምና ታሪክ ይጠይቃል፡፡ ለወደፊት ለእነዚህ ችግሮች ከፍተኛ የመጋለጥ እድል እንዳለዎት ወይም እንደሌለዎት እርስዎ የሚሰጧቸው መልሶች ይነግራቸዋል። በመልሶችዎ እና በአመታዊ የጤና ምርመራ ውጤቶችዎ ላይ በመመርኮዝ ሐኪሙ በኑሮ ዘዴዎት ላይ አንዳንድ ለውጦችን እንዲያደርጉ ዶክተሩ ሊመክር ይችላል፡፡

እነዚህን ምክሮች ማዳመጥ እና ልብ ማለት ተገቢ ነው። ዶክተሩ ምክሮችን የሚሰጠው ገለልተኛ እና ክሊኒካዊ ከሆነው ምልከታ አንፃር የሳይንስ እና የሕክምና ዕውቀት ላይ ተመስርተው ነው፡፡

የዓመታዊ ምርመራዎች እድገት – Progression of Annual Health Checkups

በመካከለኛው የእድሜ ክልል ሲሆኑ ከመከላከል እና አጠቃላይ የጤና ምርመራ ከማድረግ ትኩረቱ የተለያዩ በሽታዎች እና የጤና ችግሮች መኖራቸውን ወደ መለየት ይቀየራል፡፡ ከ35 ዓመት እድሜ በኋላ ያሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ከደም ውስጥ ያለ ካንሰርን ለመለየት ያነጣጠረ የጠቅላላ የካንሰር ላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

እነዚህ ጠቅላላ ምርመራዎች እንደ ዕድሜዎ መጠን እየሰፉ ይሄዳሉ። አብዛኛዎቹ በሽታዎች እና ሥር የሰደዱ ችግሮች በሴቶችም ሆነ በወንዶች ላይ የሚከሰቱት ከ35 እስከ 60 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ነው፡፡ ለሴቶች የቤተሰቡን ያለፈ የህክምና ታሪክ መናገር ለዶክተርዎ አመታዊ የማሞግራም ምርመራ መጀመር ያለብዎትን ዕድሜ ለመወስን ይረዳዋል፣ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ዶክተሮች ሴቶች ከ50 ዓመት ጀምሮ እንዲጀምሩ ይመክራሉ፡፡

ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች ደምዎት ይመረመራል፣ እንዲሁም በርካታ የጉበት ምርመራዎች እና የካንሰር አመላካች ምርመራዎች ያደርጋሉ፡፡ እድሜዎ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ዶክተሩ የሆርሞንዎን መጠንና የቫይታሚን፣ የማዕድን፣ እና የካልሲየም መጠንን በትኩረት ይከታተላል፡፡ በተፈጥሮ እርጅና ሂደት ምክንያት የሚከሰቱትን መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ለመተካት ተጨማሪ ምግቦች ወይም የሆርሞን ቴራፒን ሊያዝልዎት ይችላል፡፡

በሰውነት ውስጥ ያለ የካልሲየም መጠን መቀነስ ወደ አጥንት መሳሳት ችግር ሊያመራ ይችላል። ሐኪሙ የአጥንትዎን ጥንካሬዎን ወደ ሰውነት ምንም አይነት መሳሪያ ማስገባት ሳያስፈልግ ኤክስሬይ በሚመስል የDEXA ስካን አማካኝነት የአጥንትን ጥንካሬዎትን እና የአጥንት መሳሳት ችግሮችን በትክክል ይለካል፡፡አናግራም ዴክሳ (anagram DEXA) ማለት ባለ ሁለት ኃይል ኤክስ-ሬይ የሚያልፈውን የጨረር መጠን የሚለካ (absorptiometry) መሳሪያ ነው፡፡

ይህ የዕድሜ ክልል ዶክተሩ ለልብ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥበት ነው፡፡ የደም ቅዳ (coronary artery) በሽታን ለመመርመር ሐኪሙ የተለያዩ የልብ ምርመራዎችን ማለትም የልብ ተግባርን የሚያፋጥኑ ተግባራትን እያከናወንን የሚደረግ ምርመራ (stress test)፣ EKG እና CCTA ጨምሮ የተለያዩ የልብ ምርመራዎችን ሊያደርግ ይችላል፡፡

አንድ ቦታ ላይ ሁሉንም ምርመራዎች የሚያገኙበት ማዕከል (One-Stop Health Checkup Center) በባንኮክ

በአመታዊ የጤና ምርመራዎ ወቅት የሚሰጡ ምክሮች ሕይወትዎን ሙሉ ጤናማ በሆነ መንገድ እንዲጓዙ ይረዳዎታል፡፡ ለሕይወትዎ አስጊ የሆነ በሽታ ቢገኙ እንኳን ዓመታዊ ምርመራ ማድረግዎ ሙሉ በሙሉ የመዳን እድልዎን ከፍ ያደርገዋል፡፡ ቀድሞ በሽታውን ማወቅ እና ህክምና መጀመር ሳይታወቁ ለረዥም ጊዜ ከቆዩ ባልታሰበ ሁኔታ ህይወትዎን ሊቀጥፉ ከሚችሉ የካንሰር እና ሌሎች በሽታወችን ማሸነፍ የምንታገልበት እድል ይሰጠናል። ቬጅታኒ ሆስፒታል በእያንዳንዱ የሕይወትዎ ደረጃዎት ላይ የእርስዎን እንዲሁም የቤተሰብዎን ጤንነት መከታተል የሚያስችል አንድ ቦታ ላይ ሁሉንም ምርመራዎች የሚያገኙበት ማዕከል (One-Stop Health Checkup Center) አዘጋጅቷል፡፡ በቬጅታኒ ሆስፒታል ዶክተሮች እና ሰራተኞች ለአመታዊ የጤና ምርመራዎች አዳዲስ ቴክኒኮችን እና ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመጠቀም የእርስዎን እና የሚወዷቸውን ሰዎች ጤና እና ደስታን ጠብቆ ለማቆየት የሚረዱ ምርመራዎችን ያደርጋሉ፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (1 )
  • Your Rating




Related Posts