የጤና መረጃዎች

የኪንታሮት /ሄሞሮይድ/ ሌዘር ህክምና

Share:

ዝቅተኛ ህመም / በፍጥነት ማገገም

  • 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ለደረሰ እና ምልክት ለሚያሳይ የኪንታሮት በሽታ የሚመከር
  • ምንም ጠባሳ የማያመጣ
  • ዝቅተኛ ህመም
  • በፍጥነት የሚያገግም
  • ተያያዥ ጉዳቱ የቀነሰ

የኪንታሮት /ሄሞሮይድ/ ሌዘር  ህክምና ዘዴ  በአሁኑ ጊዜ 2ኛ እና 3 ኛ  ደረጃ ላይ ለደረሰ እና ምልክቶች ለሚያሳይ  የኪንታሮት በሽታ የሚመከር ውጤታማ የህክምና  ዘዴ ነው:: ለ1ኛ ደረጃ ለሚገኝና ምልክቶችን ለሚያሳይ የኪንታሮት በሽታ  የህመም ምልክቶቹ በጣም ከባድ ስላልሆኑ እና በቀዶ ጥገና ቢወገድም ተመልሶ ስለሚተካ  ቀዶ ጥገና ማድረግ አይመከርም፡፡ ሐኪም በሚያዩበት ወቅትም በፊንጢጣ የሚገቡ የሰገራ ማለስለሻ መድኀኒቶችን (laxative) ሊታዘዝልን ይችላል፣ እንዲሁም የየእለት ኑሮችን እንድናስተካክል ይመከራል ለምሳሌ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር፣ በቀን እስከ 8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት እና ለሎች ችግሩን ሊያባብሱ የሚችሉ  ባህሪያትን  እንድናስወገድ ይመከራል፡፡  4 ኛ ደረጃ ላይ የደረሰ  የኪንታሮት  በሽታ  ምልክቱ ይበልጥ የከፋ እና ቀዶ ጥገና ከሌዘር ሕክምና ጋር በጋራ  ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ የኪንታሮት /ሄሞሮይድ/ ሌዘር  ቀዶጥገና ህክምና አሰጣጥ፣ በፊንጢጣ በኩል ጨረሩን  በማስገባት የታችኛውን የኪንታሮቱን ደም ወሳጅ ቧንቧ ቅርንጫፎችን ለማስወገድ የሚሰጥ ህክምና ነው፡፡ ህክምናው  ካለቀ ከ15-20 ደቂቃዎች በኋላ ህመምተኛው ወደ ቤቱ መመለስ ይችላል ስለሆነም በሆስፒታሉ ውስጥ መቆየት አያስፈልግም፡፡ በተጨማሪም  ቁስሉ ፍጥነት የሚድን  እና የሚያባክኑትንም  ጊዜ የሚቀንስ ህክምና ነው፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የGeneral Surgery Clinic ማዕከልን ያነጋግሩ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

  • Readers Rating
  • Rated 2.9 stars
    2.9 / 5 (11 )
  • Your Rating




Related Posts