ዜና እና ዝማኔዎች

Currently, Vejthani Hospital has a preparation plan for COVID-19

Share:

የተከበራችሁየቬጂታኒሆስፒታልደምበኞችለኮሮናቫይረስያደረገውቅድመዝግጅትይመልከቱልየታ (Screening)

  • ትኩሳት (የሰውነት ሙቀታቸው ከ 37.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ) የሆኑ ሰዎች 
  • ሳል ፣ የጉሮሮ ቁስለት ፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ እንዲሁም የትንፋሽ ማጠር የመሳሰሉትን ከመተንፈሻ አካላት ህመም ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ምልክቶች የሚያሳዩ ሰዎች
  • የበሽታውን ምልክት ከማሳየቱ ከ14 ቀናት በፊት የበሽታው ስርጭት በስፋት ከተስተዋለባቸው ሃገራት (ቻይና፣ ሆንግ ኮንግ ፣ ማካው ፣ ታይዋን ፣ ሲንጋፖር ፣ ጃፓን ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ ጣሊያን እና ኢራን) ተጉዞ የነበረ ከሆነ ወይም ወደ እነዚህ ሃገራት ከተጓዘ ሰው ጋር በአንድ ቤት ዉስጥ አብሮ የሚኖሩ ሰዎች

የቅድመ መከላከል እቅድ 

1.      ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ሰዎች በሙሉ በቴርሞስካን መሳሪያ የታገዘ የሰውነት ሙቀት ምርመራ እንዲደረግላቸው ያመች ዘንድ በግራውንድ ፍሎር ላይ የሚገኘው (ድንገተኛ ክፍል አጠገብ) የፊት ለፊት በር ብቻ ወደ ውስጥ ለሚገቡም ሆነ ወደ ውጪ ለሚወጡ ደምበኞች አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል

  • መኪና ምድር ቤት(Basement) በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ የሚጠቀሙ ተገልጋዮች ወደ ሆስፒታሉ ለመግባት በግራውንድ ፍሎር በሚገኘው በር በኩል እንዲጠቀሙ ይደረጋል
  • በተጨማሪም መኪናቸውን በ 2ኛ ፤ 3ኛ እና 4ኛ ፎቅ በሚገኙ የፓርኪንግ ስፍራዎች ላይ ለሚያቆሙ ተገልጋዮች ሆስፒታሉ በየፎቆቹ ላይ ታካሚዎቹ ከመኪናቸው እንደወረዱ ወደ ተገቢው መግቢያ በር የሚያጓጉዙ መኪኖች ተዘጋጅተዋል

2. በበሽታው ተይዘዋል ተብለው ለሚጠረጠሩ ሰዎች በተለይም የሰውነት ሙቀታቸው ከፍተኛ የሆኑ እና ከመተንፈሻ አካላት ችግር ምልክቶችን ለሚያሳዩ ታካሚዎች የተዘጋጀ በሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚመራ ልዩ ክሊኒክ

3. በበሽታው ለተጠረጠሩ ሰዎች ብቻ መገልገያነት የሚውሉ አሳንስሮች (ሊፍቶች)

4. የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዳ እና በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎችን ለይቶ ለማቆያነት የሚውል ልዩ ክፍል

5. መጓጓዣ ሊፍቶችን እንዲሁም በሊፍት ውስጥ በእጅ ሊነካኩ የሚችሉ ነገሮችን የማንፃት ብቃታቸው ከፍተኛ በሆኑ ጸረ-ተህዋሲያን ኬሚካሎች ቶሎ ቶሎ ማጽዳት

6. በበሽታው ከተጠቁ ሰዎች ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው ለሚችሉ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ታካሚውን ለሚረዱ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመከላከያ አልባሳት እና የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት

7. ህመምተኛውን ወደ ሚገባው የጤና ተቋም የማጓጓዝ እቅድ

8. ለደምበኞች ስለበሽታው ግንዛቤን የሚያዳብሩ መልዕክቶች እንዲሁም የጤና ትምህርትን የሚተላለፉባቸው ዲስፕሌዮች


በዚህ ሂደት ውስጥ ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን

ቬጂታኒ ሆስፒታል

  • Readers Rating
  • Rated 3.5 stars
    3.5 / 5 (3 )
  • Your Rating
Related Posts