የጤና መረጃዎች

በእርግዝና ወቅት የአልትራሳውንድ ጠቀሜታ

Share:

የመጀመሪያ የእርግዝና ክፍለጊዜ

 • እርግዝናው መከሰቱን ለማረጋገጥ
 • እርግዝናው ማህጸን ውስጥ ወይም ከማህጸን ውጪ መከሰቱን ለማረጋገጥ
 • የጽንሱን እድሜ ለማወቅ
 • ጽንሱ የልብ ምት እንዳለው ለማረገጋገጥ
 • አካላዊ ግድፈት ካለ ለማየት
 • ዳውን ሲንድረም የተባለው ህመም የመከሰት እድሉን ለማወቅ
 • በማህጸን እና እንቁልጢ አካባቢ የሚከሰቱ ያልተለመዱ ሁኔታዎችን ለመለየት

ሁለተኛው የእርግዝና ክፍለጊዜ

 • የጽንሱን አእምሮ ጤንነት ለማረጋገጥ
 • የጽንሱን የፊት ገጽታ አካላት ለማረጋገጥ
 • የጽንሱን የውስጥ አካላት ለማየት( ልብ፤ሳምባ፤አንጀት፤ጉበት፤ኩላሊት፤የሽንት ፊኛ)
 • የእግርና የእጅ እድገትን ለመቆጣጠር
 • የጀርባ እና አከርካሪ አጥንትን አቀማመጥ ለማየት
 • የጽንሱን ጾታ ለመለየት

ሶስተኛው የእርግዝና ክፍለጊዜ

 • የህጻኑን ክብደት ለማረጋገጥ
 • የህጻኑን አመጣጥ እና የእንግዴ ልጁን አቀማመጥ ለማወቅ
 • በመጨረሻው የእርግዝና ክፍለጊዜ የሚፈጠሩ ጤነኛ ያልሆኑ እድገቶች ካሉ እሱን ለመለየት
 • ሀኪሙ ጤነኛ ያልሆነ የጽንስ እድገት እንዳለ ከጠረጠረ ይህን ለመለየት ዶፕለር በተባለ መሳሪያ የደም ስሩን ጤንነት መመርመር
 • የሽርት ውሃ መጠንን ለመለካት

እንደሚታወቀው እርግዝና ለሁሉም የቤተሰብ አባላት አስደሳች ዜና ቢሆንም እያንዳንዱ እርግዝና በራሱ በጽንሱም ሆነ በእናትየው ላይ አደጋ ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡ ስለዚህም አንዲት ሴት ይህንን መልካም ዜና እንደሰማች በቀጥታ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ክትትሏን መጀመር ይኖርባታል፡፡ሀኪም የሚለውን ምክር መስማት በየጊዜው የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ቀጠሮ መከታተል እንዲሁም ሌሎች በሀኪም የሚታዘዙ ምርመራዎችን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የWomen’s Health ማዕከልን ያነጋግሩ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

 • Readers Rating
 • Rated 3.6 stars
  3.6 / 5 (4 )
 • Your Rating

Related Posts